TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ከተማ እየተረጋጋ ቢሆንም፤ የሸቀጣ ሸቀጥና የእህል አቅርቦት ማነስ በአፋጣኝ እንዲፈታላቸው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ካማሽ ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሰላምና #መረጋጋት እየተመለሰች መሆኗንም መስክረዋል። በመንገድ እጦት በአሶሳ ከተማ የተከማቸው ከ4 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር፣ ዘይት፣ ዱቄትና ሌሎችም ሸቀጣሸቀጦች ሰሞኑን ወደ ካማሽ ዞን እንደሚጓጓዙ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #ፒያሳ_አካባቢ_ለበርካታ ዓመታት ታጥሮ የቆየውን ቦታ የፓርኪንግ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝

Barattootaafi Barsiisota yunivariitii Jimmaa Hundaaf
.
.
Waldaa Barsiisota yunivarsiitii Jimmaa irraa.

ታህሳስ 10 ከ2:30 ጀምሮ የጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች ተስተጓጉሎ የቆየው ትምህርት ሊቀጥል በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ የምክክር መድረኮች ይደረጋሉ።
@tssegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዩ የፌደራል ተቋማት አዳዲስ ሹመቶች መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

አቶ ኃይላይ ብርሀኔ ተሰማ፦ የጠቅላይ ሚስትሩ ብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ

ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ፦ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣

አቶ ሳንዳኮን ደበበ፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

ወይዘሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ ተመስገን ጥላሁን፦ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ ሙሉቀን ቀረ፦ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ ገብረመስቀን ጫላ፦ የኢትዮጵያ ካይዘን አንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ ዳኘው‼️

ፍርድ ቤቱ በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ላይ 10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።

አመልካች የፌዴራሉ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የነበረ ሲሆን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለታህሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ አዟል።

በተጠርጣሪነት የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ዳኘው የኢትዮ­ ቴሌኮም የስራ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ድርጅታቸው በሶማሌ ክልል የሞባይል ተደራሽነትን ለማስፋት የሞባይል ሲ ዲ ኤም ስራዎችን ለማከናወን የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የገባውን የውል ስምምነት ማሻሻያ በማድረግ በሌላቸው ኃላፊነት ሙሉ ክፍያ እንዲፈጽም በማድረግ ወንጀል ፖሊስ ጠርጥሯቸዋል።

በውሉ መሰረትም 201 ሚሊዮን ብር የነበረውን ውል ተጨማሪ ሳይት ለመገንባት በሚል ወደ 322 ሚሊዮን ብር ክፍያ እንዲፈም ለፋይናንስ ክፍል ደብዳቤ ጽፈዋል ብሏል።

ተጠርጣሪው ትናንት በችሎቱ ቀርበው በነበሩበት ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም ሥራውን ካለምንም ጨረታ ለሜቴክ ቢሰጥም ሜቴክ ግን ለ17 ንዑስ ተቋራጮች በመስጠት ጥራት በጎደለው ሁኔታ እንዲሰራ፣ የተከናወነው ሥራም 91 ነጥብ 8 በመቶ ቢሆንም ሙሉ ክፍያው መፈጸሙን አስረድቷል።

የተጠርጣሪው ጠበቆች በበኩላቸው በተቋማቱ መካከል ስምምነቱ በተደገበት ወቅት በሶማሌ ክልል በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሌሎች ተቋራጮች እንዳይገቡ ተደርጎ በቦርድ ውሳኔ ለሜቴክ የተሰጠ በመሆኑ ተጠርጣሪን አይመለከትም ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ተጠረጣሪው አስፈላጊውን ማስረጃ መስጠት እንደሚችሉ፣ መርማሪለመወሰን ፖሊስ ምርመራውን በትጋት ባለመስራቱ እንጂ ተጠርጣሪውን ለ35 ቀናት በእስር ሊያስቆይ የሚችል ምክንያት እንደሌለ በመግለፅ ተከራክረዋል።

ተጠርጣሪው የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩም ጠበቆቹ ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው አስረኛው ወንጀል ችሎት በተጠየቀው የተጨማሪ ጊዜና ዋስትና ጥያቄ ላይ ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ በሰጠው መሰረት ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር መሰረት ለፖሊስ 10 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ፈቅዷል።

 ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ሃላፊ እና በሙስና ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት #መላኩ_ፋንታ ከአማራ ክልል ሹመት አግኝተዋል፡፡ አቶ መላኩ ከትላንት ጀምሮ የአማራ ዐቀፍ ልማት ማሕበር (አልማ) ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል፤ ወይዘሮ ብስራት ጋሻው ጠናንም ይተካሉ፡፡ በቅርቡም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነብስ አድን ጥሪ በድጋሚ‼️ . . የአንድ ሰው ህይወት ለማትረፍ የሚያስፈልገን 125,000 ብር ብቻ ነው። ባለፉት 3 የቅስቀሳ ቀናት ብቻ ከ20,000 ብር በላይ ማግኘት ተችሏል። ከ10 ጀምሮ በመለገስ የአንድ ሰው ህይወት እናትርፍ! የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ #የዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች ቢያን 5 ሆናችሁ አስር አስር ብር በማዋጣት የእህታችሁን ህይወት ታደጉ! ለመልካም ስራ ወደኃላ እንደማትሉ…
አስቸኳይ‼️ወ/ሮ ገነት ኮማ ውስጥ ገብታለች....እሥካሁን በ5 ቀናት ሥራ የተገኘው ገንዘብ 29,000 ብር ነው። እባካችሁን የገነትን ህይወት እናትርፍ!

ቤተሠቦቿ በልብ በሚነካ መልኩ ህይወቷን የTikvahEthiopia ቤተሠብ አባላት እንዲትደጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከ224,378 የቤተሠባችን አባል 14,000 ሰው 10 ብር ቢለግሥ የሠው ህይወት ማትረፍ እንችላለን!!

1000261069575 (ገነት ገ/ህይወት)

🔹በሞባይል ባንኪንግ
🔹በአካል በመሄድ
#update የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ወይዘሮ #መሰረት_መስቀሌን ሊቀመንበርና ወይዘሮ #መስከረም_አበበን ደግሞ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ፀሀፊ አድርጎ መረጠ። የኢህዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ ሲያካሄዲ የቆየውን ጉባዔ በዛሬው ዕለት ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባዔው የስራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁት ለቀድሞዋ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የክብር አሸኛኘት አድርጓል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና~ሞያሌ‼️

ትናንት #በሞያሌ_ከተማ 13 ሰዎች ተገድለው፣ 12 መቁሰላቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ከሟቾቹ መካከል 8ቱ በቀለ ሞላ ሆቴል ውስጥ የፌደራል መከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የገደሏቸው ተብሏል፡፡ ሰዎቹ የተገደሉት የኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል እና የፌደራል ጸጥታ ሃላፊዎች እንዲሁም የቦረና ኦሮሞ እና ጋሪ ሱማሌ ጎሳ ተወካዮች ሆቴሉ ውስጥ የጋራ ምክክር ላይ ሳሉ ነው፡፡ መከላከያ ሚንስቴር እስካሁን ስለ ክስተቱ መግለጫ አልሰጠም፡፡ በከተማዋ ዛሬም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ(በዋዜማ ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አስከሬን በአሁኑ ሰዓት ከሆስፒታል ወደመኖሪያ ቤታቸው ገብቷል። አስከሬኑ መኖሪያ ቤታቸው ሲደርስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አራተኛው ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዮስን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና ወዳጅ ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቀብር ነገ ከቀትር በኋላ ይፈፀማል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሊቢያ‼️

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #በሊቢያ ህይወታቸው #ለአደጋ ተጋልጦ የነበሩ #ኢትዮጵያውያን ዛሬ ምሽት ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ አስታወቀ።

#ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊቢያ ከሚኖሩ ሌሎች በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (አይ.ኦ ኤም) ጋር በመተባበር 15 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ምሽቱን ከትሪፖሊ ወደ ሀራቸው እንዲመለሡ ይደረጋል።

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለፕሮፌሰር #አስመሮም_ለገሰ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡ ፕሮፌሰር አስመሮም በገዳ ስርዓት ላይ ባደረጉት ጥናትና ምርምር ይታወቃሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ በገዳ ስርዓት ላይ ከጻፉት መጽሐፍት Gada: Three Approaches to the Study of African Society እና OROMO DEMOCRACY: An Indigenous African Political System እንደሚጠቀሱ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለሞያሌ‼️ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️ትኩረት ለሞያሌ‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ‼️

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ሰኞ ምሽት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የተማሪዎችን ማደሪያዎች መብራት ካጠፉ በኋላ በተቀሰቀሰ ኹከት ስድስት ተማሪዎች ቆሰሉ። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በኹከቱ የሞቱ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ማግኘታቸውን አረጋግጧል። የመማር ማስተማር ሒደቱ ግን ዛሬም እንደተቋረጠ ነው።

በሀገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንፃራዊ በሆነ ሰላም የዘንድሮውን አመት የመማር ማስተማር ስራ ሲያከናውን የቆየው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በጊቢው በተፈጠረ ሁከት ሰላማዊ ድባቡን ጠፍቷል፡፡ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውም በበተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ተቋርጧል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው አለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር #አለማየሁ_ዘውዴ ትናንት ምሽት ያልታወቁ አካላት በተማሪዎች መኖርያ አካባቢዎች መብራቶች በማጥፋት ባደረጉት እንቅስቃሴ ሁከቱ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ትናንት ምሽት በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል በአንዳንድ ተማሪዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ የሚነገረው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በተማሪዎች ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት አለመድረሱን አስረድተዋል ፡፡

ዶ/ር አለማየሁ "ያልታወቁ" በሚል ለተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ መነሻ ያሏቸው አካላት በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ወይም ከዚያ ውጭ የመጡ ስለምሆናቸው ለተነሣው ጥያቄ በፀጥታ አካላት ምርመራ እየተካሄደበት ከመሆኑ ውጭእስካሁን የታወቀ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራው እንደተቋረጠ ነው፡፡ ሁከቱን በመሸሽ ግቢውን ጥለው የወጡ ተማሪዎችም ብዙ ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮቸ፣ የተማሪ ተወካዮችና የአስተዳደሩ ከፍተና የስራ ሀላፊዎች ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይት የተቋረጠው ት/ት #በአፋጣኝ ከነገው ዕለት ጀምሮ እንዲጀመር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሀላፊው ጠቅሰዋል፡፡

አንዳንድ ወገኖች እንደሚገልፁት በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ #ብሄርን መሰረት ያደረገ ገፅታን የተላበሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምዶም ታሰረ

ኢሳት(ESAT)...

"አምዶም ገብረስላሴ #ታሰረ። ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ በተካሄደው ስብሳባ አቶ በረከት ስሞኦን እና የሕወሓት ባለስልጣናትን የተቸው አምዶም ገብረስላሴ ታሰረ። ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረት #የአረና የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ በቁጥጥር ስር የዋለው መቀሌ ፕላኔት ሆቴል በተባለው አካባቢ ሲሆን፣ ሰው ደብድበሃል በሚል መታሰሩንም መረዳት ተችሏል። አምዶም መቀሌ አዲሸንዲህ በተባለ ቦታ እንደታሰረ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አምዶም ገብረስላሴ ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው ሰብሰባ የሕወሃትን ባለስልጣናት ሲተች ንግግሩ እንዲቋርጥ መደረጉም ይታወሳል።"
.
.
የአረናው #አብርሃ_ደስታ በፌስቡክ ገፁ...

"ዓምዶም #ሰላም ነው! ደሕና እደሩ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አምዶም መቀለ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ንግግር...
@tsegabwolde @tikvahethiopia