TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትኩረት ለሞያሌ‼️

"መንግስት ስለ ሞያሌ ሁኔታ ምንም ትኩረት እየሰጠው አይደለም። ብዙ ጊዜ ያስቆጠረ ችግር ነው። ሰው እንደ ቄጤማ እየረገፈ፤ እንዴት አንድም ቀን እንኳን ስለሞያሌ ሁኔታ ደፍሮ #መግለጫ የሚሰጥ ጠፋ? ሞያሌ ውስጥ ያለ ሰው ኢትዮጵያዊ አይደለም እንዴ? ከሞያሌ የመጡ ጓደኞቻችን እያለቀሱ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ 13 ሰዎች ሞቱ‼️

በቦረና ዞን ሞያሌ #በደረሰው_የጸጥታ_ችግር በሰዎችና በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃ 13 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል፤ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በህብረተሰቡ ላይ ጉዳይ የሚያደርሱ አካላት ላይ መንግስት #እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በቦረና ዞን በተለያዩ ቦታዎች
ተደርጓል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ጠ/ሚር #ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ታሕሳስ 4, 2011 ተወያዩ። ውይይቱም በዋናነት የኮሚቴውን የ5 ወራት የግጭት አፈታት እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን የተመዘገበውን ለውጥ በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጋራ የሆነ አንድነትን የሚያጠናክር ተቋም መመስረቱን መንግስታቸው እንደሚያደንቅ ገልፀዋል። በተጨማሪም ጠ/ሚሩ የታዩትን መግባባቶችን ለማጠናከርና እነሱንም ለማደናቀፍ የሚሰሩ ማናቸውንም እንቅፋቶች ለመከላከል የመንግስታቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የወልቃይት እና ቀሪ ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ስኳር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኦሮሚያ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ በቡርጂና በጉጂ ማህበረሰብ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ አራት ሰዎች #መገደላቸውን ንብረት መውደሙንና የተፈናቀሉ መኖራቸውን ነዋሪዎች ለ DW ተናግረዋል። የከተማው ምክትል ከንቲባ ግን ግጭቱ መከሰቱን አምነው ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና የተፈናቀለ ግን አለመኖሩን ገልፀዋል።

©DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የአማራና የትግራይ ክልል ክለቦች በሜዳቸው የሚጫወቱበትን አግባብ በተመለከተ ዛሬ ከክለቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ተወያየ። በውይይቱ የሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ክለቦቹ #ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስምምነቱ በመሰረት ከሁለት አመት በኅላ ስሁል ሽሬ ወደ ባህርዳር በማቅና ከባህርዳር ከነማ ጋር ይጫወታል።

ምንጭ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ🔝

በሞያሌ ከተማ እንደ አዲስ በቀሰቀሰው #ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል። በርካቶች ተጎድተዋል። ንብረት ወድሟል። መንግስት ችግሩን እንዲፈታ እና በጥፋተኞች ላይም እርምጃ እንዲወስድ ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማዕከላዊ🔝

የቀድሞ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተዘግቶ #ከቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎች በጊዜያዊነት እየኖሩበት መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማረጋገጡን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላ ሀገሪቱ እየተስፋፋ ከመጣው ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ ሰፊ ጥናት እያደረገ መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገልጧል፡፡ ጦር መሳሪያዎቹ የሚመጡባቸው እና የሚመረቱባቸው ሀገሮች ያሉ ሲሆን ባብዛኛው ከሱዳን እንደሚመጡ እና ቱርክ ሰራሽ መሆናቸውንም አቃቤ ሕግ #ብርሃኑ_ጸጋዬ ተናግረዋል፡፡ ወንጀሉን ለመከላከል በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል ከሀገራቱ ጋር ለመነጋገር ዕቅድ ተይዟል፡፡ በወንጀሉ ምርመራቸው ተጠናቆ ለፍርድ ቤት ሊቀርቡ የተዘጋጁ መዝገቦች አሉ፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ከወራት በፊት ወደ ቤተ መንግስት ካቀኑ ወታደሮች ውስጥ 66ቱ ላይ ውሳኔ መተላለፉ ተገለፀ። የምስራቅ እዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል #ዘውዱ_በላይ እንደተናገሩት 66ቱ ወታደሮች በቀዳማይ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀርበው ቅጣት ተላልፎባቸዋል። በሌሎች ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ሜጀር ጀነራል #ዘውዱ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia