TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማዕከላዊ‼️

የቀድሞ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተዘግቶ ከቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎች በጊዜያዊነት እየኖሩበት መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አረጋገጡ።

የምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በስፍራው ባደረገው የመስክ ምልከታ ማዕከላዊ ስለመዘጋቱ የተመለከቱ ሲሆን፥ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚገኙትን የህግ ታራሚዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

በቀድሞ የማዕከላዊ የተለያዩ ክፍሎች ከቡራዩ ከተማ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እየኖሩበት መሆኑንም ነው የተመለከቱት።

የክሊኒኩን ክፍሎችና የታራሚ ምግብ ማብሰያ ቤቱን የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ለአንድ ታራሚ ብቻ ተፈቅደው የነበሩ ጠባብ ክፍሎች ክፍት መሆናቸውንም ታዝበዋል።

በምልከታውም ማዕከላዊ ከመጋቢት 28 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ መዘጋቱንና በአሁኑ ሰአት ምንም ታራሚ እንደሌለ፤ በውስጡ የነበሩ 139 የፌዴራል ታራሚዎች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረሚያ ቤት በአደራ መልክ መዘዋወራቸው ነው የተመለከተው።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚገኙትን ታራሚዎች ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ጀነራል ክንፈ ዳኘው፣ ኮሚሽነር ያሬድ ዘሪሁን፣ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ እና የቀድሞ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ታራሚዎች አያያዝን እና እየተደረገላቸው ያለውን እንክብካቤ በመመልከት በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅትም ታራሚዎች የፍትህ መጓተትና የክስ ሂደቱ ውስብስብ የመገናኛ ብዙሃን ቀድመው ፍርድ እየሰጡ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለኮሚቴው አባላት አቅርበዋል።

ሰሞኑን የተሰራጨው ዶክመንታሪ ፊልም ፍርድ ቤት ውሣኔ ባልሰጠበት ክስ ላይ ትኩረት ማድረጉ ያሳደረብን የሞራል ተፅዕኖ ቀላል አይደለም ሲሉም መናገራቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለfbc ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።


ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ🔝ለሳምንታት ጥያቄያቸውን ለተቋሙ እያቀረቡ የሚገኙት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድምፃቸውን አሰምተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በጅማ ከተማ መንገድ በማስተካከል ሥራ ላይ የነበረ ግሬደር አንድ ሰው ሲገድል፣ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

ግሬደሩ የሁለት ዓመት ህጻን የገደለውና ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው ትናንት በጊንጆ ቀበሌ በተለምዶ ኤልሻዳይ በሚባለው ሠፈር ነው፡፡

አደጋው ግሬደሩ መንገድ እየጠረገ ባለበት ወቅት ንግድ በሚካሄድበት ኮንቴይነር ውስጥ በመግባቱ እንደተከሰተ የጅማ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊከ ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ነስሩ መጫ ተናግረዋል።

የአካል ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ በጅማ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት መሆኑንም አስታውቀዋል።

የግሬደሩ ኦፕሬተር በቁጥጥር ሥር ውሎ  የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዳሴው ግድብ‼️

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለዩ ክፍተቶችን በማስተካከል
በፈረንጆቹ 2022 #እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

በዛሬው ዕለት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ #ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጥልቅ ጥናትና ምርምር ስራ ሳይከናወንለት ግንባታው በመጀመሩ ምክንያት ግንባታ ጊዜው ሊጓተት እንደቻለ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያስከተለው ጉዳት ሀገሪቷ በየዓመቱ 800 ሚሊየን ዶላር እንድታጣ አድርጓታል ተብሏል።

የግንባታው ስራው በአሁን ወቅት የሚገኝበት ደራጀም በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ወቅት ይፋ ሆኗል።

በዚህም በሳሊኒ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ምህንድስናው ስራው 82 በመቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው ደግሞ 25 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል በውይይቱ ወቅት።

በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 65 በመቶ መጠነቀቁ ተነግሯል። ከዚህ ባለፈ የግንባታው ፅህፈት ቤት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልና ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

የህዝባዊ ተሳትፎን ፣ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ባለው የሶስትዮሽ ግንኙነት እና የኃይል ሽያጭ ትስስር ላይ ትኩረት ባደረጉ አራት ጉዳዮች ላይ ውይይቱ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአትሌት #ሀይሌ_ገብረስላሴ ንብረት የሆነው ማራቶን ሞተርስ ከአንድ አመት በኋላ በኤሌትሪክ የሚሰሩ የቤት መኪኖችን በመገጣጠም በኢትዮጰያ ገበያ ሊያቀርብ ነው።

ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለሞያሌ‼️

"መንግስት ስለ ሞያሌ ሁኔታ ምንም ትኩረት እየሰጠው አይደለም። ብዙ ጊዜ ያስቆጠረ ችግር ነው። ሰው እንደ ቄጤማ እየረገፈ፤ እንዴት አንድም ቀን እንኳን ስለሞያሌ ሁኔታ ደፍሮ #መግለጫ የሚሰጥ ጠፋ? ሞያሌ ውስጥ ያለ ሰው ኢትዮጵያዊ አይደለም እንዴ? ከሞያሌ የመጡ ጓደኞቻችን እያለቀሱ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ 13 ሰዎች ሞቱ‼️

በቦረና ዞን ሞያሌ #በደረሰው_የጸጥታ_ችግር በሰዎችና በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃ 13 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል፤ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በህብረተሰቡ ላይ ጉዳይ የሚያደርሱ አካላት ላይ መንግስት #እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በቦረና ዞን በተለያዩ ቦታዎች
ተደርጓል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ጠ/ሚር #ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ታሕሳስ 4, 2011 ተወያዩ። ውይይቱም በዋናነት የኮሚቴውን የ5 ወራት የግጭት አፈታት እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን የተመዘገበውን ለውጥ በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጋራ የሆነ አንድነትን የሚያጠናክር ተቋም መመስረቱን መንግስታቸው እንደሚያደንቅ ገልፀዋል። በተጨማሪም ጠ/ሚሩ የታዩትን መግባባቶችን ለማጠናከርና እነሱንም ለማደናቀፍ የሚሰሩ ማናቸውንም እንቅፋቶች ለመከላከል የመንግስታቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የወልቃይት እና ቀሪ ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ስኳር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኦሮሚያ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ በቡርጂና በጉጂ ማህበረሰብ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ አራት ሰዎች #መገደላቸውን ንብረት መውደሙንና የተፈናቀሉ መኖራቸውን ነዋሪዎች ለ DW ተናግረዋል። የከተማው ምክትል ከንቲባ ግን ግጭቱ መከሰቱን አምነው ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና የተፈናቀለ ግን አለመኖሩን ገልፀዋል።

©DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የአማራና የትግራይ ክልል ክለቦች በሜዳቸው የሚጫወቱበትን አግባብ በተመለከተ ዛሬ ከክለቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ተወያየ። በውይይቱ የሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ክለቦቹ #ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስምምነቱ በመሰረት ከሁለት አመት በኅላ ስሁል ሽሬ ወደ ባህርዳር በማቅና ከባህርዳር ከነማ ጋር ይጫወታል።

ምንጭ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia