TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አምቦ🔝በአምቦ ዩኒቨርሲቲ እየተደረገ በሚገኘው ሰልፍ ተማሪዎች፦ከሰሞኑን በቤንሻንጉል እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ የተፈፀመውን ግድያ እንቃወማለን፤ ለአካባቢው ችግር የበላይ አካላት መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል ብለዋል። በተጨማሪ አምቦ እና አካባቢው ነዋሪ ለኢትዮጵያ ጉለበት ነው መንግስት ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ይስጥ፤ የአምቦ ማህበረሰብ ፍቅርም ያውቃል ለሰላም ያለውም ፍላጎት እስከጥግ ነው ካልሆነ ግን ሙሉ እድሜያችንን በትግል እንደማሳለፋችን አሁንም መጥተን መታገል አያቅተንም ብለዋል። ተማሪዎቹ በሠልፉ ላይ የማንም ሰው ህይወት ሊጠፋ አይገባም፤ እየደረሰ ያለው መፈናቀልም በአስቸኳይ ይቁም ሲሉ ተደምጠዋል።

🔹ተማሪዎቹ ሰልፉን ከግቢ ውጭም እያደረጉ ናቸው። ነዋሪውም አጋርነቱን አሳይቷል።
©አቢቲ(ከአምቦ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ🔝የJiT ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የጅማ ከተማ ነዋሪዎች የተካፈሉበት ሰልፍ በአሁን ሰዓት እየተደረገ ይገኛል። ሰልፉ ላይ "የወገኖቻችን ግድያ ይቁም!" የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እየተሰሙ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ🔝የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም ሰልፍ እንደ አምቦ እና ጅማው ሰልፍ ሀሳቡ አንድ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት‼️

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህዳር 22 ቀን ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በቀረበው የከተማ ግብርና ልማት ረቂቅ ስትራቴጅ ላይ በመወያየት ረቂቅ ስትራቴጅው ተጨማሪ ውይይት ተደርጎበትና ዳብሮ እንዲመጣ ወስኗል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የጉምሩክ ኮሚሽንን ተግባር፣ ሃላፊነትና አደረጃጀት ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል።

ምክር ቤቱ ደንቡ ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች ተደርገው በስራ ለይ እንዲውልም ውሳኔ አሳልፏል።

በኢትዮጵያና በሩዋንዳ መካከል በተደረገው የመረጃና የመገናኛ ብዙሃን ስምምነት እና የግብርና ዘርፍ የትብብር ስምምነት ላይም ውይይት አድርጓል።

በተጨማሪም በመንግስትና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በተደረሰውና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ኦፖርቹኒቲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ በሚውለው ስምምነት ላይ የተወያየ ሲሆን፥ ስምምነቶቹ እንዲጸድቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷቸዋል።

ምንጭ፦ ጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር በ2.4 ቢሊዮን ዶላር ለ7,000 የሕክምና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ቤት፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ ሪዞርትና መናፈሻ ያካተተ መንደር እንደሚያሠራ አስታወቀ፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ገሚቺስ_ማሞ እንደገለጹት፣ የግንባታው ሥራ የሚከናወነው በሁለት ዕርከን ሲሆን፣ በመጀመርያው ዕርከን የሚከናወነው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ነው፡፡ የቤቶቹ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኃላ በሁለተኛ ዕርከን የሆቴል፣ የሪዞርትና የመናፈሻ ግንባታ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡ የመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ለ30,000 ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ግንባታውም በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ዳሰሳ‼️

ዛሬ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ(አዋሮ እና ወሊሶ ካምፓስ)፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ(JiT)፣ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ አዋሰኝ አካባቢዎች የተፈፀመውን ግድያ #ተቃውመው ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

በአምቦ እና በጅማ ሰልፉ በተማሪዎች ብቻ ሳያበቃ ውጪ ያለው ማህበረሰብም ተማሪዎችን ተቀላቅሏል። (ከግቢ ውጭ)

በሌላ በኩል...

በASTU እና AASTU የዛሬው የትምህርት መርሀ ግብር ተቋርጧል። ዛሬ በAASTU ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። ምክንያቱ ደግሞ ተማሪዎች ያነሷቸው የአካዳሚክ ጥያቄዎች ናቸው። የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርታቸውን ወደክፍል ገብተው እንዲቀጥሉ ጠንከር ያለ ማስታወቂያ ቢያወጣም ተማሪዎች ክፍል አልገቡም።

🔹በASTU ልጆቻቸው የሚማሩ ቤተሰቦችን በስልክ እንዳነጋገርኩት ጉዳይ ቶሎ መፍትሄ እንዲበጅለት ጠይቀዋል። የልጆቻቸው ትምህርት መቋረጥም እንዳሳሰባቸው ነግረውኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UPDATE የቴፒ ከተማ የንግድ እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እየተመለሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ህዝብ!!

ዶ/ር ደብረፅዮን "ከአማራ ህዝብ የሱዳን ህዝብ ይሻለናል!" ሲል እኔ #አልሰማሁም። አለ ሲባል ግን ሰምቻለሁ። እኔን ብትጠይቁኝ ግን ..."በብዙ እጥፍ የትግራይ ህዝብ ይበልጥብኛል!"

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው (ዋሽንግተን ዲሲ)

©ጋዜጠኛ ጌጡ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‹‹ዶር. ደብረፂዮን ሲል አልሰማሁም ነገር ግን ሰዎች ሲያዎሩ ሰምቻለሁ፡፡ ከአማራ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይሻለኛል ብሎ ከሆነ አንድ ነገር ነው ማለት የምፈልገው እኔ ብጠየቅ ከሱዳን ህዝብ ይልቅ የትግራይ ህዝብ በብዙ እጥፍ ይበልጥብኛል፡፡›› አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዳሰሳ 2‼️

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሃገሪቱ እየታየ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል እና #ሁከትን ለመቀነስ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

🔹ደብረ ማርቆስ ዩኒቭርስቲ

የመከላካያ ሚንሰትር ዴኤታ አምባሰደር ዘላለም ገብረ ዮሃንሰን ጨምሮ ከፌዴረል እና ከክልል የተወከሉ የመንግስት አካላት የምስራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር፣ የሃገረ ሽማግሌዎች ፣የሃማኖት አባቶች እና የጸጥታ አካላት በተገኙበት ምክክር አካሂዷል፡፡

🔹ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የሚነሱ የግጭት መንስኤዎችን ለይቶ ቅድመ መከላከል ለመስራት እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

🔹ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

ከሕዳር 19 ጀምሮ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች #በሰላማዊ የመማር ማስተማር ዙሪያ ከፌዴራል በተገኙ አወያዮች ምክክር አድርገዋል፡፡

‹‹የምንማረው ድህነትን በአንድነት ለማሸነፍ እንጂ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን የልዩነት ምንጭ አድርጎ ለመራረቅ አይደለም፡፡›› የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተናገሩት...

‹‹በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ኢትዮጵያዊነት ለአንድነታችን ማጠናከሪያ፤ ለቁርሾዎቻችን መታረቂያ ምክንያት እንዲሆኑ ጥያቄዎችን የመፍታት ባሕል ማድረግ አለብን፡፡›› አወያዮች ከተናገሩት የተወሰደ...

🔹ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከአማራ ክልል መንግስት እና ከሌሎች አካላት የተወጣጣው የሰላም ኮሚቴ በባሕር ዳር ለ14 ቀናት የሚቆይ ከሰላም መስፈን ጋር የተያያዙ ተግባራትን እየተከታተለ እና እያገዘ መሆኑን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን እና ስታራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶር. #ዘውዱ_እምሩ ገልጸዋል፡፡

የሰላም ኮሚቴው በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት እና አጠቃላይ በከተማው ያለውን የሰላም ሁኔታ ገምግሟል፡፡ በዚህም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን በአግባቡ በመቀበል፣ መረጃ በመስጠት እና #የግጭት_ስጋቶችን በማስወገድ በጎ ስራ መስራቱን ተመላክቷል ነው ያሉት ዶር. ዘውዱ፡፡

‹‹ሰላም ቀላል የሚመስል ነገር ግን የሁላችንም እስትንፋስ ነው፡፡ ለሰላም የበኩላችንን እንወጣ››

‹‹ራሳቸውን አደራጅተው የአካባቢውን ጸጥታ የሚጠብቁ ወጣቶች የተማሪዎች ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን በጎ ስራ ሰርተዋል፡፡›› ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

.
.
©አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia