TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AFRICA

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ በቀጣዮቹ 12 ወራት 190 ሺ ሰዎችን በአፍሪካ ሊገድል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ አስጠንቅቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የ47 ሃገራት ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት አስጠናሁ ባለው ጥናት ለወረርሽኙ አፋጣኝ ምላሽ እና ተገቢው ትኩረት ካልተሰጠ ስርጭቱ ሙሉ በሙሉ ሳይጠፋ ረጅም አመታትን ሊቆይ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡

ከአሁን ቀደምም እንደ መንግስታት የዝግጁነት እና የምላሽ ሁኔታ ቢለያይም እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

በያዝነው ሳምንት ይፋ የሆነው የድርጅቱ ጥናት የቁጥጥር ስራዎች በታሰበው ልክ ውጤት የማያመጡ ከሆነ ወረርሽኙ በተከሰተበት በዚህ ዓመት ብቻ ከ29 እስከ 44 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SENEGAL

ሴኔጋል በኮቪድ-19 ምክንያት በውጭ ሃገራት የሞቱ ዜጎቿን አስከሬን መቀበል ጀመረች ፤ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል የትኛውም አስከሬን ወደ ሃገሯ እንዳይገባ ከልክላ የነበረችው ሴኔጋል ክልከላዋን አንስታለች - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BorisJhonson

275 የጤና ባለሞያዎች ህይወታቸውን አጥተዋል!

በዩናይትድ ኪንግደም 275 የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ኮሮና ቫይረስ በዩናይትድ ኪንግደም 144 የጤና ባለሙያዎችንና 131 የማህበረሰብ ክብካቤ (ሶሻል ወርክ) ሰራተኞችን ህይወት እንደቀጠፈ ገልጸዋል - #AlAin

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኮሮና ክትባት በአመት ውስጥ እውን ሊሆን ይችላል!

በአውሮፓ ለሚዘጋጁ ክትባቶች ፍቃድ የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ ተስፋ የተጣለበት የኮሮና ቫይረስ #ክትባት በቀጣዩ አንድ (1) ዓመት ውስጥ እውን ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል - #AlAin

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክያት የተዘጋው የአሜሪካ እና የካናዳ ድንበር እስከ ሰኔ 14/2012 ዓ/ም ድረስ ተዘግቶ እንደሚቆይ ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ ገልፀዋል።

- ብሪታኒያ ሰዎች ራሳቸውን ችለው እንዲገለሉ ከሚያደርጉ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ማሽተት አለመቻል ወይም ጣዕም ማጣትን አካታለች - #BBC

- 2ተኛ ቀኑን በያዘው የWHO 73ኛ ዓመታዊ የቪዲዮ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ አባል ሃገራት ድርጅቱ /WHO/ እና በስሩ ያሉ ኤጀንሲዎች ለኮሮና ወረርሽኝ የሰጡት ምላሽ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተስማምተዋል - #AlAin

- የቻይና ሳንቲስቶች ኮቪድ-19ኝን የሚያቆም መድሀኒት አግኝተናል እያሉ ነው። ወረርሽኙን ክትባት ያቆመዋል ተብሎ ይገመት ነበር የሚሉት የቻይና ላብራቶሪ ተመራማሪዎች የኮሮናን ስርጭት በፍጥነት የማቆም ኃይል ያለው መድሀኒት እያዘጋጀን ነው ብለዋል - https://telegra.ph/EthioFM-05-19-2

- በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ100,000 በላይ ሆኗል። የሟቾች ቁጥር ከ3,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በብራዚል የኮሮና ቫይረስ እየበረታ ነው፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከUK፣ ከጣልያን፣ ከፈረንሳይ በልጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 261,567 ደርሷል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 162 ሰዎች ሞተዋል፤ 813 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በማዳጋስካር ሁለተኛው (2) ሞት በትላትናው ዕለት ምሽት ተመዝግቧል። በሌላ በኩል በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 326 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMikeRyan

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰባቸው ባሉ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ እገዳዎች በቶሎ የሚነሱ ከሆነ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል ሲል #አስጠንቅቋል፡፡

የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማይክ ርያን አለም በመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሞገድ ውስጥ ነች፤ ምንም እንኳን በብዙ ሀገራት በቫይረሱ የመያዝ መጠን እየቀነሰ ቢሆንም በማእከላዊና በደቡብ አሜሪካ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶክተር ማይክ ርያን ከሆነ ወረርሽኞች ሁሌም ወቅታዊ ናቸው ፤ በዚህ አመት የመጀመሪያው ሞገድ ያቆመባቸው ሀገራት እንደገና ይመለሳል ብለዋል፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ ክልከላዎች ቶሎ የሚነሱ ከሆነ ቫይረሱ በፍጥነት ሊስፋፋ የሚችልበት እድል እንዳለ ገልጸዋል - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በወላይታ ዞን በተለይም በተከሰተው ሁከት በትንሹ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን አል ዐይን ዘግቧል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የዞኑ ባለስልጣን እንዳረጋገጡት በሶዶ ከተማ ትናንት ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞ ላይ በፀጥታ ሀይሎች በተወሰደ እርምጃ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተመሳሳይ በቦዲቲ ከተማ 4 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ከሞቱት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸውንም ገልፀዋል።

በደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በተሰጠ መግለጫ በተፈጠረው ሁከት አንድ ሰው ብቻ እንደተገደለ ነው የተገለፀው #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለስልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ መስጠቱን ለአል ዐይን ገልጿል፡፡

ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ ያለባቸው የመንግስት ሹመኞች በተደጋጋሚ እንዲያስመዘግቡ ቢጠየቁም ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

ባለስልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስቀምጡ ያስቀመጠው ቀነ ገድብ ባለፈው ሀምሌ 30 ለሁለተኛ ጊዜ በማለፉ ምክንያት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድርጉን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በቀነገደቡ ማስመዝገብ ያልቻሉ አንድ መቶ ሰማንያ አራት (184) የፌደራና የአዲስ አባባ መገኘታቸውንና እነሱም በህግ ይጠየቃሉ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡ ኮሚሽኑ የባለስልጣናቱን ስም ዝርዝር ግን ይፋ አላደረገም - #AlAin

@tikvahethiopiaBOT
የአዲስ አበባ ማማ - የንግድ ባንክ ህንፃ!

- ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ እየተገነባ ይገኛል።

- 48 ወለል ያለውና 198 ሜትር ርዝመት አለው።

- ግንባታው በ2008 ዓ/ም ነበር የተጀመረው

- ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና መንግስት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።

- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተቆጣጣሪነት እየተሳተፈ ይገኛል።

- መንግስት ለግንባታው ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ መድቦለታል።

- ከፕሮጀክቱ የከፍተኛ ትምህርት መምህራርንና ተማሪዎች የዳበረ ልምድ አግኝተውበታል ተብሏል።

- ህንፃው በምስራቅ አፍሪካ በርዝመቱ ትልቅ ይሆናል።

- የህንፃው ግንባታ አሁን በመጠናቀቅ ላይ ነው።

#AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UNITED_NATION

በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች የአያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ 2 ቡድኖቹ ወደ ክልሉ መግባታቸውን የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ሃላፊ ሚሼል ባሸሌት የኢትዮጵያ መንግስት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ያልተቆራረጡ ሰብዓዊ አቅርቦቶች እንዲኖሩ መፍቀዱን መቀበላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሆኖም ሰብዓዊ አቅርቦቶቹ በጦርነቱ የተጎዱ ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች ሊያዳርሱ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡

ሚሼል ባሸሌት ከዓለም አቀፍ ህግጋት በተጣረሰ መልኩ በተሰባሰበ ህዝብ ላይ የመተኮስ፣ ሆን ብሎ ንጹሃንን ዒላማ የማድረግ፣ የግድያ እና ዝርፊያ ድርጊቶች ጭምር እንዳሉ የሚያለክቱ መረጃዎች ደርሰውናል ብለዋል፡፡

ይህም በ2ቱም ወገኖች ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ አለመቻላቸውን የሚያሳይ ነው ያሉም ሲሆን ጦርነቱ በክልሉ ሰሜናዊ ፣ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ አካባቢዎች ቀጥሏል መባሉ ይበልጥ እንዳሳሰባቸውም ነው ኮሚሽነሯ የገለጹት፡፡ #AlAin

የተመድ OHCHR ሙሉ መረጃ 👇
https://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=26623&LangID=E

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia