TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ተአማኒና ሕጋዊ የሆነ ምርጫ ማካሄድ ከቻልን ማንም አሸነፈ ማን፣ የምታሸንፈው #ኢትዮጵያ ናት፡፡"

🔹🔹ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ🔹🔹
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም በትላንትናው ዕለት ተከብሯል። ዕለቱን አስመልክቶ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ባስተላለፈው መልዕክት እያንዳንዱ ዜጋ ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ቆርጦ መነሳት እንዳለበት አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና🔝

"ሴሌሜ ሴሌሜ" በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው የሀድያን ብሔር ባህልና ወግ በአለም ደረጃ በመድረክና በሚዲያ በቀዳሚነት ያስተዋወቀ፤ በሀገራችን በሚዘጋጁ ትላልቅ ህዝባዊና ሀገራዊ ዝግጅቶች ላይ ትርኢት በማቅረብ በአዘፋፈን ስልቱ እና በጭፈራው በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው አርቲስት #አቡሎ_ጡሞሮ ትላንት ማምሻውን ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ምንጭ፦ ገረመው በቀለ

TIKVAH-ETH ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና አድናቂዎቹ በጠቅላላ መፅናናትን ይመኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ መደበኛ የሆነ የዕለት ተዕለት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ናት። በማዕበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች ነዋሪዎች ግር ልትሰኙ አይገባም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በኤርትራ ዋና ከተማ #አስመራ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ብስክሌት ዋንጫ ውድድር ትላንት ተጠናቋል። የኢትዮጵያ የብስክሌት ቡድን ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ⁉️

ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የተረዳነውና ራሳችንን ይዘን እንድንገረም ያደረገን በሜቴክ በኩል ሲዘራ የሰነበተው ገንዘብ ጉዳይ ነው፡፡ ይኸች #ድሃ ሃገር፣ ተለቅታም፣ ተበድራም፣ ሸጣም ያገኘችው የውጭ ምንዛሬ ሲመዠረጥ መክረሙ ብዙ ጥያቄዎችን የሚቀሰቅስ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡

ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደዋዛ ሲቀር ተመልካች የለም ነበር ወይ? ኧረ ለመሆኑ፣ ቢሊየኖች የገበያ ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሳይሆን እንደተፈለገ ግዥ ላይ ሲውል የፋይናንስ ሥርዓቱንስ አያወላግደውም ወይ? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡

ሸገር FM 102.1 (ንጋቱ ሙሉ) እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ይዞ ከምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።

ከላይ ያለውን ፋይል ከፍታችሁ አድምጡ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዩኒቨርሲቲ🔝

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዳ። ሰልፍ የወጡት ተማሪዎች የአማራ የኦሮሞ ልጆች የሚባል የለም ሁላችንም አንድ ነን፤ እዚህ የመጣንበት አላማ አንድ ነው እሱም ትምህርት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ሁላችንም በሰላም መመለሳችንን የምትጠብቅ #ድሀ_እናት ነው ያለችን ሙሉ ሰው ልካ እሬሳ የምትቀበልበት ጊዜ አልፏል እናም ከመቼውም ጊዜ በላይ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልንጠነቀቅ ይገባል ብለዋል። በአጠቃላይ የተሰጠንን እድል ብናውቅ እንኳን ልንጋደል ቀርቶ ልንፋቀር ጊዜ አይበቃንም ስለዚህ እኛ #ኢትዮጵያ_ነን ሲሉ ገልፀዋል። የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በቦታው ተገኝቶ ተማሪዎቹን አነጋግሯል።
.
.
ተጨማሪ

በሰልፉ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መሀከል...

🔹እኛ አንድ ኢትዮጵያ፤ አንዲት ሀገር ነን!
🔹እኛ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ አንድ ነን!
🔹ኢትዮጵያ ማደግ የምትችለው በሌብነት ሳይሆን በስራ ነው!
🔹ሌባ እምነት፤ ብሄር የለውም!!

ምንጭ፦ TIKVAH-ETH(አቢቲ)
@tsegabwolde @tikvhethiopia
"እኛ ኢትዮጵያዊያን በፍቅር የተደመርን፤ #በፍቅር ያደግን ሰዎች ነን! አማራ~ኦሮሞ ትላልቅ ብሄሮች ለኢትዮጵያ #ውበት ነን!"

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ(አዋሮ ካምፓስ) ተማሪዎች ዛሬ ባደረጉት የአንድነት ሰልፍ ካሰሙት መፈክር የተወሰደ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋሮ ካምፓስ🔝የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ተማሪዎቻቸውን #አመሰግኑ። ፕሬዘዳንቱ ተማሪዎቻቸውን ያመሰግነቱ ዛሬ ላደረጉት ከስሜታዊነት የፀዳ ፍፁም ሰላማዊ ሰልፍ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ🔝

በደብረ ማርቆስ ከተማ አንድ ግለሰብ ከዛፍ ላይ ወጥቶ #አልወርድም አለ።
በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03 ከህዳሴ ጤና ጣቢያ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ዛፍ ላይ ወጥቶ ነው ግለሰቡ ‹‹አልወርድም!››ያለው፡፡

ክስተቱ መፈጠሩን ፖሊስ የተመለከተውም ትናንት ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ነው፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት ግለሰቡ ‹‹ውረድ!›› ተብሎ ቢለመንም መልስ አልሰጠም፡፡ ፖሊስም ከዛፍ ላይ ያደረውን ግለሰብ ሲጠብቅ አድሯል፡፡ ከዛፉ ላይ ማደሩም አነጋጋሪ ሆኗል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም ግለሰቡ ከዛፉ አልወረደም። ግለሰቡን ‹‹አውቀዋለሁ›› የሚል ሰውም አልተገኘም፤ ዛፉ ረዥም መሆኑም ማንነቱን በዕይታ ለመለየት አስቸጋሪ አድርጎታል ነው ያሉት ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው፡፡

ይህ ለምን እንደሆነ ግን አልታወቀም፤ ምክንያቱንና እውነቱን የሚያውቀው ግለሰቡ ነውና፡፡ ግለሰቡ ደግሞ ይህን አልተናገረም፡፡

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia