TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ለመቄዶንያ የአረጋዊያንና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የ10 ሚሊዮን ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ድጋፉን የባንኩ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ዛሬ ለማዕከሉ አስረክበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን🔝

ኢትዮጵያዊቷ ድምጻዊት #ብሩክዊት_ጌታሁን (ቤቲ ጂ) ለአምስተኛ ጊዜ በተካሄደው በመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ላይ #በሦስት_ዘርፍ አሸናፊ ሆነች።

ድምጻዊት ቤቲ ጂ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የምስራቅ አፍሪካ በምርጥ ሴት አርቲስት እና የአፍሪካ ተስፋ የተጣለበት ዘርፍ ነው ሽልማትዋን የተቀበለችው።

ድምጻዊት ቤቲ የዓመቱን ምርጥ አልበም ሽልማትዋን ያሸነፈችው #ወገግታ በሚለው አልበሟ ነው።

እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት አርቲስት ሽልማትን መንገደኛ በሚለው የሙዚቃ ስራዋ ስታሸንፍ፤ ተስፋ የተጣለባቸው በሚለው ዘርፍ ደግሞ ኧረ ማነው በሚለው የሙዚቃ ስራዋ ነው ያሸነፈችው።

ቤቲ ጂ ሽልማቶቹን ከተቀበለች በኋላ በፌስቡክ ገጿ ላይ "ድምፅ በመስጠት ላገዛችሁኝ አድናቂዎቼ በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው" ብላለች፡፡

"ኢትዮጵያን ወክዬ ስቆም አኮራችሁኝ፤ እናንተ ከጐኔ ነበራችሁ፤ አንድ ላይ ሆነን የአገራችንን ስም እናስጠራለን" በማለት ከጎኗ ለነበሩ ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡ እንዲሁም "ይህ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም" በማለት መልዕክቷን አስተላልፋለች።

አፍሪማ በአውሮፓውያኑ 2014 የተጀመረ የሙዚቃ ውድድር ሲሆን፥ የዘንድሮው ዝግጅት በጋናዋ መዲና አክራ ነው የተካሄደው፡፡

ምንጭ፦ ghanaweb.com,fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ🔝

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት የተጠረጠረን  አንድ ግለሰብ #በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ሰይፈዲን_ሃሩን ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ፖሊስ ሰሞኑን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት ለሶስት ተማሪዎች ሞትና በሌሎችም ለደረሰው ጉዳት የጠረጠረውን አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ “ታምሚያለሁ “ በሚል መድኃኒት ለመውሰድ በጸጥታ ሃይሎች ታጅቦ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከሄደ በኋላ በመኖሪያ ቤቱ ያስቀመጠውን መሣሪያ በማቀባበል በጸጥታ ኃይሎች ላይ #ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ሲፈተሽ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነር ሰይፈዲን የሚጠቀምበትን ኮምፒዩተር ጨምሮ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረበት ክለሽንኮብ መሣሪያም በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስረድተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ግጭት በተጠረጠሩ ሌሎች ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል፡፡

በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ማክሰኞ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት ማለፉና በሌሎች ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH(AB)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል‼️

#በአሶሳ_ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ “ታምሚያለሁ” በሚል ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዲሄድ በመፍቀድ በግለሰቡና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል የተጠረጠሩ ሶስት #የፖሊስ_አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማደር አኑር ሙስጣፋ ለኢዜአ እንዳስታወቁት በከተማው የወረዳ ሁለት መደበኛ ፖሊስ አባላት የሆኑ ሶስት ግለሰቦች ማምሻውን #ትጥቃቸውን ፈትተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የፖሊስ አባላቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ላቀረበው የ”ታምሚያለሁ” ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከተው የወረዳው አካል ትዕዛዝ ሳያገኙ በራሳቸው ፈቃድ ግለሰቡን ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰዳቸው ነው፡፡

የጸጥታ ሃይሎቹ ተጠርጣሪውን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ሲገባቸው ወደ መኖሪያ ቤቱ መውሰድ እንዳልነበረባቸው ኮማንደር አኑር አስረድተዋል፡፡

ግለሰቡም ወደ መኖሪያ ቤቱ በተወሰደበት ወቅት ክላሽንኮብ በማውጣት በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በከተማው በተወሰኑ ቦታዎች አለመረጋጋት ታይቶ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ግን የከተማው ሁኔታ በጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ነበረበት እንደተመለሰ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወደ ባህር ዳር የመጣነው በብሄሮች መካከል የሚረጨውን የጥላቻ እንቦጭ ነቅሎ ለመጣል" ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በሶርያ መንግስት ቁጥጥር ስር ባለችው አሌፖ ከተማ ውስጥ 107 ሰዎች #የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቃት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ።

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በቱርክ የሚደገፈው የብሄራዊ ነጻነት ግንባር በመባል የሚታወቀው ተፋላሚ ኋይል ጥቃቱን ሳይፈጽመው አልቀረም ተብሏል።

ሆኖም ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ አልጀዚራ የግንባሩን ኃላፊዎች የጠየቀ ሲሆን፥ መሳሪያው ጭራሽ በእጃቸው እንደሌለ ተናግረዋል።

እንዲሁም ድርጊቱን እንደከዚህ ቀደሙ #የበሽር_አላሳድ መንግስት ያቀነባበረው ነው ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

የበሽር አላሳድ መንግስት በበኩሉ ጥቃቱን የሰነዘሩት ተፋላሚ ኃይሎቹ ናቸው በማለት ወቀሳውን ሰንዝሯል።

ጥቃቱን ተከትሎም የሩሲያ የመከላከያ ኃይል በአካባቢው አሸባሪ ናቸው ብሎ በሚያምንባቸውንና ጥቃቱን አቀነባብረዋል ባላቸው ላይ የአየር ጥቃት ማከሄዱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወቅቶች በሶርያ ህዝብ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች መድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን፥ በዚህም የተባበሩት መንግስታትና ዓለምአቀፉ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተቋም በጋራ ባጠኑት ጥናት የበሻር አላሳድ መንግስትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ ሲኤንኤንና አልጀዚራ(በfbc)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና🔝

ሶሪያ መንግስት ስር በምትደዳደረው #አሌፖ ከተማ ውስጥ 107 ሰዎች #የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቃት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሞት የተነሳው ኢትዮጵያዊ ከBBC ጋር፦

ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች የሚባለው መቼ ነው? ምን ሲሆን?

አቶ ሂርጳ ነገሮ ለዚህ ፍንጭ ሊሰጡን የሚችሉ ሁነኛ ሰው ናቸው፤ የቅርብ ጊዜ ምሥክር። ትውልዳቸው ከወደ ምሥራቅ ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ ነው።

ዘለግ ላለ ጊዜ በጽኑ ታመው ቆይተዋል። ከ2 ዓመት በፊት ሆድ ዕቃቸው ተከፍቶ በቀዶ ጥገና ታክመዋል። የጤና ታሪካቸው በአጭሩ ይኸው ነው።

ማክሰኞ ረፋድ ላይ ግን ድንገት ደካከሙ። በዚያው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ሞቱ [ተባለ]። ጥሩምባ ተነፋ፣ ጥይት ተተኮሰ፣ ድንኳን ተጣለ፤ ለቀስተኛ ተሰበሰበ፤ ሬሳ ተገነዘ።

ከአራት ተኩል ሰዓታት በኋላ ግን አቶ ሄርጳ[ሳጥን ፈንቅለው ወጡ]፤ 'ኢጆሌ ኢጆሌ እያሉ....'። ይህ የኾነው ማክሰኞ 'ለታ ተሲያት ላይ ነው።

ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከእርሳቸው ጋር የስልክ ቆይታ አድርጓል። በ'ሞቱበት' ሰዓት ያለ ቀጠሮ ያገኙት 'መልአክ' ምን ሹክ እንዳላቸው ጭምር አብራርተዋል። ኾኖም መቅደም ያለበትን እናስቀድም። አቶ ኢታናን፤ ገናዣቸውን።

ቢቢሲ፦ ሳይሞቱ እንዳይሆን አጣድፋችሁ ሳጥን ውስጥ የከተታችኋቸው።

አቶ ኢተና፦ "ዛሬ አይደለም እኮ ሰው የገነዝኩት [ቆጣ አሉ]። ስንትና ስንት ሰው ገንዣለሁ። ስንትና ስንት..."

ቢቢሲ፦ እና ሳጥን ውስጥ ሲከቷቸው ትንፋሽ አልነበራቸውም? እርግጠኛ ኖት?

አቶ ኢታና፦ "[ምን ነካህ!] ስንትና ስንት ሰው ሲሞት ዐይቻለሁ። ስንትና ስንት አው ገንዣለሁ። መሞቱን አረጋግጬ ነው ሳጥኑ ውስጥ ያስገባሁት። ዝም ብዬ እከታለሁ እንዴ። [የምር እየተቆጡ መጡ]

ቢቢሲ፦ ታዲያ እንዴት የሞቱ ሰውዬ ሊነሱ ቻሉ?

አቶ ኢተና፦ እንጃ! እንዲህ ዓይነት ነገር ሆኖ አያውቅም። ይሄ ከእግዛቤር የሆነ ነው እንጂ...።

እሑድ ሊናዘዙ ቀጠሮ ነበራቸው
"ሞቼ ተነሳሁ" የሚሉት አቶ ሂርጳ በሽታቸውን በውል አያውቁትም። ኾኖም እምብርታቸው አካባቢ ለረዥም ጊዜ ይቆርጣቸው ነበር።

ነገርየው የጉበት ሕመም ሳይሆን እንዳልቀረ ይጠረጥራሉ። ሐኪምም ዐይቷቸዋል። የፈየደላቸው ነገር ባይኖርም።

መጀመርያ ነቀምት ሆስፒታል፣ ከዚያ ደግሞ ጥቁር አንበሳ 'ሪፈር' ተብለው ሄደዋል። ደንበኛ ምርመራ አድርጊያለሁ ነው የሚሉት። ኾኖም የምርመራ ውጤቱ አልተነገራቸውም። በታኀሣስ 1፣ ሊነገራቸው ቀጠሮ ተይዞ ነው በዚያው 'ያሸለቡት'። በዚያ ላይ ለመዳን ከነበረ ጽኑ ፍላጎት የተነሳ በሬ ሽጠዋል። ዘመድ አዝማድ ተቸጋግሯል። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዶ ለመታከም።

ከሰሞኑ ጉልበት ሲከዳቸው ታዲያ እንደማይተርፉ ጠረጠሩ። ያለቻቸውን ጥሪት ለአምስት ልጆቻቸው ሊናዘዙ ፈለጉ። ሰኞ ሊሞቱ እሑድ ዕለት ለመናዘዝ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ያጋጣሚ ነገር ኾኖ በዕለቱ የበኩር ልጃቸው ስላልነበረ ኑዛዜው ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ። ማክሰኞ 'ለት 'ሞቱ'።

"ሬሳ ሳጥን የሰጠሁት እኔ ነኝ"

ገናዥ አቶ ኢታና ቤተሰብም ናቸው፤ ጎረቤትም ናቸው። 'ሟች' የወንድማቸው ልጅ ናቸው። 3ሺህ የሚያወጣ ሬሳ ሳጥን በታላቅ ቸርነት ያበረከቱትም የገነዙትም እርሳቸው ናቸው።

"ጋዜጠኞች ትናንት መጥተው ዐይተዋል። የወንድሜ ልጅ ስለሆነ የራሴን ሳጥን ሰጠሁት" ይላሉ። ቤተሰቡን ከወጪ ለመታደግ ነው ታዲያ ይህን ያደረጉት። ሳጥኑ ውስጥ ልብስ ምናምን ነበር የሚቀመጥበት። ምናምኑን ሁሉ ወለል ላይ ጣጥለው፣ አራግፈው፣ የወንድማቸውን 'ሬሳ' በክብር አኖሩበት።

"ነጭ ልብስ የለበሰ መልአክ 'ተመለስ' አለኝ" እጅግ በተረጋጋ ሁኔታ የሚያወጉት አቶ ሄርጶ በሰማይ ቤት ቆይታቸው የተመለከቱትን ለቢቢሲ አጋርተዋል።

እርግጥ ነው አንዳንድ ነገሮች ተዘንግተዋቸዋል። አንዳንዶቹ ትውስ ይሏቸዋል፣ ኾኖም በጠራ መልኩ አይደለም። አንዳንዶቹን ነገሮች ግን አጥርተው ማስታወስ ይችላሉ። ልክ ዛሬ የኾነ ያህል።

ለምሳሌ በሰማይ ቤት በብረት ሰንሰለት የሚታጠር ግቢ ብዙ ሺ ሰዎች ተሰብስበው ተመልክተዋል። አጥሩ ከምን እንደተሠራ ግን አያስታውሱም፤ በሩ የብረት ይሁን የሳንቃ ትዝ አይላቸውም። አካባቢው ደጋና ልምላሜ የወረሰው እንደነበር ያስታውሳሉ። ኾኖም የሰማይ ቤቱ መልከዐምድር አይከሰትላቸውም።

ከሁሉ ከሁሉ ያልዘነጉት ግን ከባድ ንፋስ ይነፍስ እንደነበረ ነው። ክብደቱን ሲገልጹ ድምጻቸውን ሁሉ ይበርደዋል።

ሰዎች ተሰብስበውበታል ከሚሉት ከዚያ ግቢ ታዲያ ማንንም አያውቁም። ከሦስት ሰዎች በቀር። እነርሱም ከ2 ዓመት በፊት የሞቱትን አባታቸው፤ ከዓመታት በፊት የሞቱትን አማቻቸውን እና አንድ ሌላ አጎት ናቸው።

ከሦስቱ ጋር ምን እንዳወጉ በውል አያስታውሱም። የሚያስታውሱት "እኛን ተከተለን" ብለዋቸው ቢከተሉ፣ ቢከተሉ፣ በፍጥነት ቢራመዱ፣ ቢሮጡ ሊደርሱባቸው እንዳልቻሉ ነው። ነገሩ የሕልም ሩጫን ይመስላል። ቀዩን መልአክ ግን መቼም አይረሱትም። በሁለተኛው ምዕራፍ የሕይወት ዘመናቸውም የሚረሱት አይመስልም።

ቢቢሲ፦ መልአኩ ቀይ ነው ጥቁር?
አቶ ሂርጶ፦ ነጭ ነው፤ ቀይ ነው...ጌታን ኢየሱስንም ይመስላል።

ቢቢሲ፦የሰው መልክ ነው ያለው ወይስ የመልአክ?

አቶ ሄርጶ፦ፊቱ በደንብ አላየሁትም። ወደ አጥሩ ቆሞ እኔ ውጭ ነበርኩ። #መልኩ ቀይ ነው፣ ነጭ ልብስ ይለብሳል። ሰዎቹን ወደ ውስጥ አስገባና ይዟቸው ሄደ።

ቢቢሲ፦ሌላ መልአክ አልነበረም አጠገቡ?

አቶ ሄርጶ፦ አላስታውስም፤ እሱን ብቻ ነው ያየሁት።

ቢቢሲ፦ምን አሎት?

አቶ ሄርጶ፦ 'አንተ የት ትሄዳለህ? ተመለስ!' አለኝ።

ቢቢሲ፦በምን ቋንቋ ነው ያናገርዎት?

አቶ ሄርጶ፦ በኦሮምኛ።

ቢቢሲ፦ አልፈሩም?

አቶ ሄርጶ፦ አቅም አጣሁ እንጂ አጥሩን ኬላውን አልፌ ብገባ ደስ ባለኝ ነበር።

"ኢጆሌ ኢጆሌ..."

ማክሰኞ ተሲያት ላይ ከሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ድምጽ ሲሰማ የአጋጣሚ ነገር በቅርብ የነበሩት የ'ሟች' እናትና ባለቤቱ ነበሩ። "ኢጆሌ ኢጆሌ..." ይላል ድምጹ። ሚስትና እናት ራሳቸውን አልሳቱም፤ በርግገው ከአካባቢው ተሰወሩ እንጂ። ድምጹ አልቆመም። "ኢጆሌ ኢጆሌ ነምኒ ሂንጂሩ?..." ለቀስተኛው ግማሹ እግሬ አውጪኝ አለ። ግማሹ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የሰሙት ሬሳው እየጮኸ እንደሆነ ተናገሩ። ለመጠጋት የደፈረ አልነበረም። ከገናዣቸው በስተቀር። "ወንዶቹ ሁሉ ጥለው ጠፉ" ይላሉ አቶ ኢታና።

ቢቢሲ፦ እርስዎ ግን አልፈሩም?

አቶ ኢታና፦ ለምን እፈራለሁ፤ ሬሳውን ማስቀመጤን አውቃለዋ...

🔹"ከዚህ በኋላ የምኖረው ትርፍ ሕይወት ነው"

ያን 'ለታ ፀሐይ ስታዘቀዝቅ ሚሪንዳ ቀመሱና ነፍሳቸው መለስ አለች። ሲረጋጉ ዘመድ አዝማድ መሰብሰቡን አስተዋሉ። እልልታና ለቅሶም ሰሙ። "ምንድነው ይሄ?"። 'ሞተው ነበረኮ' ተባሉ።

"እንኳን በሰላም ገባህ፤ እንኳን በሰላም ተመለስክ ብለው ተደሰቱ" ይላሉ የወቅቱን የለቀስተኛውን መደነቅና ደስታ ለቢቢሲ ሲያስረዱ።

"ተጸጸቱ እንዴ ግን? ወደ ሕይወት በመመለስዎ?" ተብለው ነበር።

"እዛ ብሆን ጥሩ ነበር...። ግን አሁን ቅር የሚለኝ ነገር የለም። ወደ ልጆቼ፣ ወደ ቤተሰቤ በመመለሴ በጣም ደስ አለኝ።" ከዚህ በኋላ ምን ለማድረግ እንዳሰቡ ሲጠየቁ ጊዜያቸውን የሃይማኖት ትምህርት በመስጠትና የተጣሉ ሰዎችን በማስታረቅ ለማሳለፍ እንዳሰቡ ተናግረዋል።

ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ እነ አቶ ሄርጳ ቤት ዛሬም ለለቅሶው ሲባል የተተከለው ድንኳን ባለበት አለ። "ሰዎች በብዛት እየመጡ ነው። እንደለቅሶ ነው የሚመጡት" አሉ ገናዡ አቶ ኢታና።

ጥቁር አንበሳ ቀጠሮ አላቸው "ከመሞቴ በፊት ከነሐሴ ጀምሬ እንጀራ በልቼ አላውቅም" የሚሉት አቶ ሄርጳ "አፌም እንደዚህ መናገር አይችልም ነበር" ይላሉ።

ከሬሳ ሳጥን ከወጡ በኋላ ግን ሕመማቸው
ሙሉ በሙሉ ድኖ በሶም እንጀራም መቀማመስ ጀምረዋል። ድምጻቸው ደከምከም ይበል እንጂ ዘለግ ላለ ሰዓት እንደልብ ያወራሉ።

የተዘነጋው ጉዳይ! ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቀጠሮ አላቸው። ለታኅሣሥ አንድ። ለውጤት ነው የተቀጠሩት።

ከዚህ በኋላ ሐኪም ዘንድ ይሄዳሉ? ተብለው ሲጠየቁ ታዲያ መልሳቸው አጭርና ፈጣን ነው። "ለምን ብዬ!"

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia