ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ🔝
በኢትዮጵያ በአለፉት ስምንት ወራት ሁለት #ተቃራኒ የሚመስሉ ሁነቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት፣ የኢኮኖሚ ግንባታ ይታያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አለመረጋጋት፣ የሰላም መናጋት፣ ሕገወጥነት፣ በግልም ሆነ በቡድን መፃዒ #እድሎች እርግጠኛ አለመሆን ይስተዋላል፡፡
🔹VOA ከፕሮፌሰር ፕርሀኑ ነጋ ጋር ያደረገውን ቆይታ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል አዳምጡ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አሶሳ ዩንቨርስቲ‼️
በአሶሳ ተከስቶ በነበረው #ግጭት የሦስት ተማሪዎች #ህይወት ማለፉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ሚኒስቴር የሆኑት ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ምን ይመስላል በሚለው ጉዳይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህ የተሰማው፡፡
ዶክትር ሂሩት ባለፉት ቀናት በውስን ዩኒቨርስቲዎች ተፈጥሮ የነበሩ ግጭቶችን አስመልክቶ ስለምክንያታቸም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም አሁን ያለው ሀገራዊ ለውጥ እና ለውጡን ለማደናቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ኢላማ መሆን፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚነሱ ሁከቶች ምክንያት ወይም ከግጭቶቹ በስተጀርባ ያለ ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዎች ምንነትና፣ መንግስት ለእነዚሁ ጉዳዮዮች እየሰጠ ያለው ምላሽ በተመለከተ አንስተዋል፡፡
ዶክተር ሂሩት ሀገሪቱ በለውጥ ሂደት ላይ ያለች፣ ባለፉት ሰባት ወራትም የተወሰዱ በርካታ እርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ያተረፉ ቢሆንም፤ አሁንም ግን ከቀድሞ በተለየ መልኩ በተለይ ዩኒቨርስቲዎችን ኢላማቸው አድርገው ለውጡን ለማደናቀፍ እንቅስቃሴዎች እያየን ነው ብለዋል።
ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ

#Update የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ ሰብሳቢን #ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።
Via-ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via-ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሰራዊት ትጥቅ በመፍታት ወደ ሃገር ውስጥ ገብቷል።
ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️
አሶሳ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ሰላሙ #ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ካለፈው እሑድ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩ ተስተጓጉሏል፡፡ ተማሪዎች እና ተወካይ ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የግጭቱ መነሻ የሁለት ተማሪዎች አለመግባባት ነው፡፡ ይህም እየተስፋፋ ሄዶ ወደ ቡድን ፀብ ተቀይሮ ነበር፡፡
ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር #ሃይማኖት_ዲሳሳ ችግሩን ለመፍታት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ምክክር ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም መግባባት ላይ መደረሱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡
ይሁን እንጂ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት ላይ ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲገቡ እንደገና #ረብሻ ተጀምሮ ነበር፡፡
እንደ ተማሪዎቹ መረጃ የግጭቱ ዋነኛ ምክንያት የተማሪዎች መማክርት በወቅቱ አለመመረጥ ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ፈጥሯል የሚል ነው፡፡
ተማሪዎቹ ምርጫው ‹‹ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ መካሄድ ነበረበት፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት አልተካሄደም፤ እስካሁን ግን መቆየት አልነበረበትም›› የሚል አቋም አላቸው፡፡
አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችን ተወካዮቻቸው በወቅቱ አለመፍታታቸውም ለችግሩ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ተማሪዎቹ የተናገሩት፡፡
ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹በውይይቱ ለከፋ ግጭት የሚዳርግ ችግር አላገኘንም›› ነው ያሉት፡፡
በረብሻው ምክንያት ‹‹34 ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል ብለዋል
ዶክተር ሃይማኖት፡፡
በተከሰተው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች ግቢውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም ይህን መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተረጋግተው ለመኖር እና ለመንቀሳቀስም ስጋት ውስጥ መሆናቸውንና ለሰላማቸው #ዋስትና እንደሚፈልጉ ነው የተናገሩት፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

ሰበር ዜና‼️
ወይዘሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳ በነገው ዕለት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሀላፊ ሆነው ሊሾሙ መሆኑ ተሰምቷል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ወሪት ብርቱካንን የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ መንግስት የሚቀርብለትን ሹመት ድምፅ ይሰጥበታል።
ወይዘሪት ብርቱካን ከሰባት አመታት ስደት በኋላ መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ wazemaradio

"በኢትዮጵያ 27 በመቶ ያህል ሰዎች #የአዕምሮ ጤና ችግር አለባቸው።" ዶክተር #ዳዊት_አሰፋ (የኢትዮጵያ አዕምሮ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ዓለም ፍፁም‼️
ፖሊስ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙት ባለሀብቱ አቶ #ዓለም_ፍጹምን የፕላስቲክ ፋብሪካቸውን እና ሆቴላቸውን በሕገ ወጥ መንገድ #ያለጨረታ ለብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በእንግሊዝኛ ምኅጻሩ ሜቴክ #በመሸጥ እንደጠረጠራቸው ዛሬ ለፍርድ ቤት አስታወቀ።
አቶ ዓለም ፋብሪካቸውን ለመሸጥ የሰጡት ዋጋ 128 ሚሊዮን ብር ሲሆን፤ ለሜቴክ የሸጡት ግን ከፍ ባለ ዋጋ በ195 ሚሊዮን ብር መኾኑን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ይህን ያደረጉትም ጓደኛቸው ከሆኑት ከሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጋር ተመሳጥረው ነው ሲል ገልጿል።
የአቶ ዓለም ጠበቆች የፖሊስን ክስ ተቃውመዋል። ፍርድ ቤቱ አቶ ዓለም የዋስትና መብት እንዲሰጣቸው የቀረበለትን ጥያቄም ውድቅ ማድረጉን፤ ለምርመራ የተያዘላቸውን ጊዜም ከ14 ቀን ወደ 10 ቀናት ዝቅ ማለቱንም ታውቋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

ኮሎኔል አሰፋ ዮሐንስ‼️
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በተያዙት በቀድሞው የፓወር ፕላንት ኢንጂነሪንግ ስራ አስኪያጅ ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት ፈቀደ።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ኮሎኔል አሰፋ ጠበቆች የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለህዳር 24 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ኮሎኔል አሰፋ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ድርጊት ከበለስ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ምንጭ፦ ena

የአዲስ አበባ ወጣቶች🛫ባህር ዳር
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ እና 300 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የፊታችን አርብ (ህዳር 14/2011ዓ.ም) የአማራ ክልል ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ ያመራሉ፡፡
በከንቲባው የሚመራው የልዑካን ቡድን በሶስት ቀን የባሕርዳር ቆይታው ብሄራዊ ሃብታችን የሆነውን ጣናን እየተፈታተነ ያለውን #የእንቦጭ_አረምን ያርማል፥ የህዝብ ለህዝብ ውይይት ከከተማዋ ወጣቶች እና ከከተማዋ ኃላፊዎች ጋር ያደርጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሰል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች በቀጣይነትም ከኦሮሚያ ፥ ከትግራይ እና ሌሎችም የሃገሪቱ ክፍሎች ጋር ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ቢሮን ዋቢ አድርጎ ዋልታ ዘግቧል፡፡
ምንጭ፦ ዋልታ

#update በሱማሌ ክልል “ሔጎ” በሚል ስያሜ ይንቀሳቀስ የነበረው የወጣቶች ሕገ ወጥ ቡድን ከሞላ ጎደል #እንዲበተን ተደርጓል፡፡ ብዙዎቹ ሕገ ወጥ ሥራ ሲሰሩ የነበሩ የቡድኑ አባላት በቁጥር ሥር ውለዋል፤ ሰው #ሲገድሉ የነበሩ ጥቂት ቁልፍ አመራሮቹ ግን ተሰውረዋል ብለዋል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር #ሙስጠፋ_ዑመር ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን በሰጡት መግለጫ፡፡
via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትውልድ አድን‼️
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሠላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት “ትውልድ አድን” የተሰኘ የህይወት ክህሎት ሥልጠና መርሃ-ግብር ሊጀመር ነው።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም ሠላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።
የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ በዩኒቨርስቲዎች ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸውም ሠላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችል “ትውልድ አድን” የተሰኘ የህይወት ክህሎት ሥልጠና መርሃ-ግብር ሊጀመር መሆኑን በዚህ ወቅት ጠቁመዋል።
በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎችም መርሃ-ግብሩ በጅምር ላይ መሆኑን ጠቁመው በታዋቂ ግለሰቦች፣ በአርቲስቶችና በሥነ-ልቦና ባለሙያዎች የሚካሄድ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሯ እንዳሉት አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ሥር-ነቀል የለውጥ ሂደት ላይ በመሆኗ የተለያዩ ችግሮችን እያስተናገደች ነው።
በተለይም ሂደቱን #ለማደናቀፍ የሚሠሩ ኃይሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት ማድረጋቸውን ጠቁመው ይህ እንዲሆን የተፈለገው ተቋማቱ “ትንሿን ኢትዮጵያ” የመወከል አቅም ስላላቸው ነው ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን በመገንዘብ ችግሮችን ከወዲሁ መከላከል እንደሚገባ ገልጸው በዩኒቨርስቲዎች ሠላማዊ የመማር ማስተማር እንዲጠናከር መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️
ፓርላማው ነገ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
• የቀድሞ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወ/ት #ብርቱካን_ሚደቅሳ ሰብሳቢ ይሆናሉ ተብሏል
• የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጉዳይ #ውሳኔ ላይ #አልተደረሰም
በነገው ዕለት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል ተብሎ የሚጠበቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት በጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አሕመድ ዕጩ ሆነው የሚቀርቡትን የቀድሞዋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና የሕግ ባለሞያ ወ/ት ብርቱካን ሚደቀሳ ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ በኩል የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያው አቶ ዳንኤል በቀለ (እጩ ዶክተር) ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነርነት በዕጩነት ቀርበው በመንግሥትና በእርሳቸው በኩል የተጀመረ ንግግር ቢኖርም እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አለመደረሱን ምንጮች ጠቁመዋል።
በመንግሥትና በአቶ #ዳንኤል_በቀለ መካከል ንግግር መጀመሩንና ነገር ግን ውሳኔው አለመጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።
🔹አቶ ዳንኤል በቀለ (እጩ ዶክተር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪና በዲቨሎፕመንት ስተዲስ በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል። እንግሊዝ ከሚገኘው ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለም አቀፍና የሰብዓዊ መብቶች ሕግ በማስተርስ ተመርቀዋል። በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ሕግ ከዚያው ከኦክስፎርድ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለመጨረስ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ይቀራቸዋል።
አቶ ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆነው ሠርተዋል፣ በሕብረት ኢንሹራንስ የሕግ ዳይሬክተረ ነበሩ። መንግሥታዊ ባልሆነው ግብረ ሰናይ ድርጅት (Actionaid- Ethiopia ) አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። በምርጫ 97 ከቅንጅት አመራሮች ጋር ታስረው ነበር። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዲቪዥን ዳይሬክተር ነበሩ።
ምንጮች እንደገለፁት አቶ ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እዲመሩት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለና በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደሚደረስ ነው። በዚህ መሰረት በነገው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርበው ሹመት የብሔራዊ ምራጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ብቻ ነው።
🔹ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል። ከረዳት ዳኛነት እስከ ፌደራል ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል። በጥብቅና ሞያና በሕግ አማካሪነት ሠርተዋል። በ1992 ዓ.ም ተወልደው ያደጉበትን (ፈረንሳይ ለጋሲዮን) አካባቢ በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል ተወዳዳሪ ነበሩ። የቅንጅት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ሆነው ሠርተዋል። በእዚህ ወቅትም ለእስር ተዳርገዋል። ከእስር ከተፈቱ በኋላ አንድነት ፓርቲን በሊቀመንበርነት መርተዋል። በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ ታስረዋል። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዛ National Endowment for Democracy (NED) ኔድ በተሰኘ የታወቀ የዴሞክራሲ የምርምር ተቋም ውስጥ ተመራማሪ ፌሎ በመሆን ለአንድ ዓመት በዴሞክራሲ ላይ ምርምር አድርገዋል። በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ውስጥም (Scholars at Risk) በተሰኘ ፕሮግራም ለአንድ ዓመት ሰልጥነዋል።
በዚሁ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ አስደዳደር (Public Administration) በሁለተኛ ዲግሪ ተመረቀዋል። ምክር ቤቱ ነገ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያን በወ/ት ብርቱካን ተክቶ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ያልተሟሉ የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መናብርት ሹመትን ለማፅደቅ የውሳኔ ሐሳብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ፦ ፂዮን ግርማ(ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት)

#Update የኮንጎ የጤና ባለሙያዎች የኢቦላ ቫይረስን ከሀገሪቱ ለማጥፋት #አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ተናገሩ፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ #ወረረሽኙ በተስፋፋበት ጊዜ ቶሎ መቆጣጠር ባለመቻሉ ነው ብለዋል፡፡
©አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️
በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ሁኔታ መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው እና ችግሩን እንዲፈታ ተማሪዎች ደግመው ደጋግመው በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን!
“ጤናማ የአኗኗር ዜይቤ ለጤናማ ሕይወት” በሚል መሪ ቃል መንገዶችን ከተሽከርካሪ ፍሰት #ነፃ በማድረግ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማክበር ማቀዱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችንና አጋላጭ መንስኤዎቻቸውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በማሰብ መርሃ ግብሩ እንዳዘጋጀ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ ለጊዜው #በአዲስ_አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በሂደት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ከተሽከርካሪ ነፃ በሚሆኑ የተመረጡ መንገዶች ላይ የአካል እንቅስቃሴዎች፣ ተላለፊ ላልሆኑ በሽታዎች ነፃ ምርመራዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በሚል ይከናወናሉ፡፡
ምንጭ፦ etv

የዛሬ ውይይት‼️
በየቤታችሁ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ተወያዩ!!
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍፁም ባልተለመደ መልኩ በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች ግጭቶችን እያስተዋልን ነው። አንዳንዶቹ ከተማዎችማ ጭራሽ በግጭት ስማቸው ተነስቶ የማያውቅ እና በአስተማማኝ ሰላማቸው የተመሰከረላቸው ናቸው። ግጭቶቹን ከጀርባ ሆኖ የሚመራ አካል እንዳለም መንግስት በተደጋጋሚ ገልጿል። ግጭቶቹ ካለፉ በኃላም ዜጎች ድጋሚ ተመሳሳይ ነገር እንዳይከሰት ዘውትር እንደሰጉ ነው።
.
.
ዛሬ የምንወያየው ግን አሁን አሁን እየተስተዋለ ያለውን የሞራል ዝቅጠት ነው። ግለሰቦች በተጣሉ ቁጥር #ብሄራቸው ምንድነው?? ምን እና ምን #ብሄር ነው የተጣሉት? ተብሎ መጠየቅ ተጀምሯል። ይህ በእንዲህ ከቀጠለ ሀገሪቷን የማትወጣው ችግር ውስጥ እንከታታለን። ግለሰቦች እንደግለሰብ መፈረጅ እና መዳኘት ሲገባቸው የብሄር ተወካይ አድርጎ እርስ በእርስ ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም።
እናተስ በዚህ ጉዳይ ምን ትላላችሁ??