TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ...

ፈጣሪ ምን ያህል #እንደሚወደን እዩ፦
አውሎ ንፋስ አይመታን፣ ሰደድ እሳት አይበላን፣ ሱናሚ አይወስደን፣ መሬት ተንቀጥቅጦ አይውጠን፣ ኢቦላ ገብቶ አልፈጀን... ስለምን በዚህች በፈጣሪ #በምትጠበቅ ድንቅ ሀገር ውስጥ ሆነን እርስ በእርስ #እንበላላለን?? ስለምን እርስ በእርስ እንጠላላለን?? ስለምን ይህቺን ሀገር አልምተን ከአለም ቀዳሚ አንሆንም?? #የኃልዮሽ ጉዞ አይሰለችም?? ዛሬም ትንንሽ ጉዳዮች የኛ መገለጫ መሆናቸው የሚያሳዝን ነው። እስኪ እንቅና ሌላው የደረሰበት #የእድገት ደረጃ ለመድረስ እንቅና!!

መልካም ቀን!!
ከፈጣሪ ተሰጠንን ፀጋ እንጠቀምበት ኃላ እንዳይቆጨን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ዣማል ካሾግዢ‼️

በሳዑዲ አረቢያዊው ጋዜጠኛ ዣማል ካሾግዢ ግድያ ውስጥ “እጃቸው አለ” ያለቻቸው አሥራ ስምንት ሰዎች ወደ ድንበር ወደማይገድበው የአውሮፓ ሃገሮች የዝውውር ክልል ወደሆነው ሸንገን ቀጣና እንዳይገቡ ጀርመን #እገዳ መጣሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሃይኮ ማስ አስታወቁ።

በርሊን በግለሰቦቹ ላይ እገዳውን ከመጣሏ በፊት ከፈረንሣይ እና ከእንግሊዝ ጋር መመካከሯንም ጀርመናዊው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ገልፀዋል።

ብራስልስ ላይ ከተሰበሰሰው የአውሮፓ ኅብረት ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደ መግለጫ ላይ የተናገሩት ማስ “አሁን በራሱ በወንጀሉ ላይና አድራጎቱ እንዲፈፀም ማን እንዳዘዘ መለየትን ጨምሮ ከመልሶቹ ጥያቄዎቹ ይበዛሉ” ብለዋል።

የዣማል ኻሾግዢ ግድያ እንዴት እንደተፈፀመ የሚጠቁመው የተቀረፀ ድምፅ ምን እንደሆነ ሙሉ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ትናንት የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በአድራጎቱ የአመፃና የክፋት መጠን መብዛት ምክንያት ድምፁን እራሱን ማዳመጥ እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

“የሥቃይ ድምፅ ነው፤ አስቀያሚ ድምፅ ነው፤ ሁከትና አመፃ የበዛበት፣ #የጭካሄና የክፋት አድራጎት ነው” ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA የአማርኛው አግልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የቀድሞ ዋና ፅህፈት ቤቱን ዳግም በዛሬው ዕለት ተረከበ።

የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ኦነግ ዛሬ የተረከበው ፅህፈት ቤት እሰከ 1985 ዓ.ም ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑን ተናግረዋል።

ግንባሩ በተለያዩ ምክንያቶች ከሽግግር መንግስቱ ራሱን ካገለለበት ጊዜ ጀምሮ ፅህፈት ቤቱ፥ ከኦነግ ተቀምቶ ለተለያዩ የመንግስት ግልጋሎቶች ሲውል እንደነበር ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

ግንባሩ ዛሬ የፅህፈት ቤቱን ህንፃ የተረከበው ከወራት በፊት በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገረሳ የተመራ ልኡክ በአሰመራ ከኦነግ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት፥ ለግንባሩ እንዲመለስ በተስማሙት መሰረት መሆኑን አቶ ቶሌራ አስታውቀዋል።

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮምያ ክልል መንግስት ቃላቸውን ጠብቀው ፅህፈት ቤቱ ለግንባሩ እንዲረከብ ላደረጉት አስተዋፅኦም ኦነግ ምስጋና አቀርቧል።

የኦነግ ፅህፈት ቤት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በተልመዶ ጉለሌ ተብሎ በሚጠራው ስፊ ግቢ ወስጥ የሚገኝ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ‼️

በጋምቤላ በኩል የገባ 50 ክላሽንኮቭ፣ አንድ ላውንቸር እና 40 ካርታ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ።

የጦር መሳሪያው በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከጋምቤላ ጀምሮ #ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ አዲስ አበባን አልፎ ደብረ ብርሃን ላይ ነው የተያዘው።

የጦር መሳሪያው በገልባጭ መኪና የብረት ረብራብ ተሰርቶለት በመጓጓዝ ላይ እንዳለ የተያዘ ሲሆን በቁጥጥር ስር ከዋሉት 50 ክላሽንኮቭ ውስጥ 37ቱ ባለሰደፍ ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ታጣፊ መሳሪያዎች መሆናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን🔝

በኢትዮጵያ የሕግ ልዕልና ለማክበር የተጀመረው ሂደት ፖለቲካዊ መልክ ይዟል አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።

ሂደቱን ትግራይን #ለማንበርከክ የሚደረግ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም የውጭ እጅ አለበት በማለት በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀረር የውሃ ችግር አልተቀረፈም‼️

ጥንታዊቷ የሐረሪ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ምንጯ የሆነው ሐረማያ ሐይቅ ከነጠፈ በኋላ ከውሃ አቅርቦት ችግር ልትላቀቅ #አለመቻሏን ነዋሪዎቿ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ከሳምንታት በፊትም ሐረር የከፋ የውሃ ጥም አጋጥሟት ‘ድረሱልኝ’ ማለቷ አይዘነጋም።

ኢዜአ ከሰሞኑ በከተማዋ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ከሰሞኑ #ቢሻሻልም ችግሩ በዘላቂነት እንዳልተቀረፈላቸው ይናገራሉ።

የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት እየጣረ እንደሆነ ገልጿል።

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ፤ ውሃ የሚያገኙት ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር እየቆዩ በመሆኑ ለከፍተኛ የኑሮ ጫና እየተጋለጡ ነው።

ከአስተያየት ሰጭወቹ መካከል  ወይዘሮ እታለማው ተሾመ  ውሃ ተቋርጦ እስከ  ወር ፣ በሁለት ወር፣  አንዳንዱም ቦታ ደግሞ   እስከ ስደስት ወር  እንደሚቆይ አመላክተው  ችግሩ  አሳሳቢ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ የታየው “አልጋ ሁሉ አንሶላ ለማጽዳት ውሃ የለም። በየመንደሩ አንድ ጣሳ ውሃ ለማግኘት ህዝቡ እንደ እግዚአብሔር ውሃ እየለመነ ያለው።”

የውሃ አቅርቦቱ  ለሁለት ወር ያህል ተቋርጦ  እንደነበር  አስታውሰው  አንድ ጄሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ድረስ  መግዛታቸውን ያመላከቱት ደግሞ  አቶ ኢበሳ ሲራጅ  ናቸው፡

 አሁን በአንጻንራዊ  መሻሻሉን  አመላክተው  በሳምንትና  በሁለት  ሳምንት  እንደሚመጣ ጠቁመዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የቴክኒክና ኦፕሬሽን የስራ ሂደት ኃላፊ አዲል በከሪ መሃመድ ሐረር ከድሬዳዋ፣ ኤረርና ሐረማያ አፋባቴ ከተሰኙ ስፍራዎች የከርሰ ምድር ውሃ እንደምታገኝ ጠቁመው ከድሬዳዋ አካባቢ ከሚመጣው በስተቀር የኤረርና ሐረማያ አፋባቴ የከርምደር ውሃ ምንጮች ለማሟያነት እንጂ የከተማዋን ህዝብ ውሃ ፍላጎት የሚያሟሉ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት የሚያጋጥመው የውሃ እጥረት ድሬዳዋ አካባቢ የሚገኘው የውሃ ጉደጓድ መጠን የመቀነስና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንደነበር ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንደ አማራጭ የሚያገለግሉት በኤረርና ሐረማያ አፋባቴ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የካሳ ጥያቄዎች በማንሳት የውሃ መስመሩን አቋርጠውት እንደነበር አስታውሰዋል።

ባለስልጣኑ ለአካበባው ማህበረሰብ የቦኖ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ ስራዎች ቢሰሩም ከዋናው መስመር የመጠቀም አዝማሚያዎች ስላሉ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በሌ በኩል በድሬዳዋ ያሉ የውሃ ጉድጓዶችን ጥልቀት ከ150 ሜትር ወደ 500 ሜትር በማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ ፖል የሌላቸውን በመትከል የውሃ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መውልዲ!!

1 ሺህ 493ኛው የነብዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል በእምነቱ ተከታዮች በታላቁ #አንዋር መስጅድ ተከብሯል። በበዓሉ መክፈቻ ላይ ቁርአን የተቀራ ሲሆን በታዳጊ ተማሪዎች ነሺዳ ቀርቧል። የነብዩ መሐመድ የህይወት ታሪክና ያከናወኗቸውን ተግባራት የተመለከተ ትምህርት በሃይማኖት አባቶች የተሠጠ ሲሆን መንዙማና ዱአ /ፀሎት/ በበዓሉ አከባበር የተከናወኑ ተግባራት ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሜቴክ ሰራተኛ‼️

"ሰላም ፀግሺ ስሜ E ይባላለሁ። የምፅፍልህ ከደ/ዘይት ነው፡፡ የሜቴክ ሰራተኛ ነኝ ከደጀን አቭዬሺን ኢንዱስትሪ ነገር ግን ሰሞኑን ከተያዙት የሜቴክ ሃላፊዎች ጋር ሰራተኞችን እንደ #ሌባ ማየት ጥሩ አይደለም። በወረደ ደሞዝ ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን ሌላ መ/ቤት እንኳን እንዳንወዳደር የስራ ልምዳችንን እያዩ የሜቴክ ስለሆነ አይጠሩንም፡፡ እዚጋ መታወቅ ያለበት በጣም ትልቅ አቅምና የስራ ዲሲፒሊን እንዲሁም የፈጠራ አቅምና የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸው ምርጥ ሰራተኞች ነው ያሉት ስለዚህ አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ የሚለው አባባል እየደረሰብን ስለሆነ ማንም የበላይ አመራርና ሃላፊ በፈፀመው ሌብነት ታቺ ያለው የኔ ቢጤ ሰራተኛ 15 ቀን የማያቆይ ደሞዝ እየተከፈለው ስማችን አይጥፋ ወንጀለኛን ወንጀለኛ ስንል እየለየን ይሁን እባክህ ለሁሉም አድርስልኝ፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶ/ር ደብረፅዮን መግለጫ‼️

"አንዳንድ ሚድያዎች በተለይም ደግሞ ኢዜአ እና FBC መግለጫዎችና መረጃዎች በማዛባት የትግራይ ህዝብና መንግስት ገፅታ የማበላሸት ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡

ይህ የሚድያ ብሮድካስቱ ህገ-ደምብ የጣሰና ፈር የለቀቀ አካሄድ መለዉ የአገሪቱ ህዝብ እዉነተኛ መረጃ የማግኘት ህግ-መንግሰታዊ መብቱ የነፈገ ተግባር በትናንትናው ዕለት በወቅታዊ ጉዳይ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ር/ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ደብረፅየን ገ/ሚካኤል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በማዛባት አሁንም ቀጥለውበታል፡፡

በዚህ የተንሸዋረረ #የእብደት አካሄድ የሚደናበር የኢትዮጵያ ህዝብ አለ ብሎ ማሰብ በራሱ ሞኝነት ነው፡፡ ሰለሆነም ለህገ-መንግስቱና ለብሮድካስቱ ስርአት መጠበቅ በመታገል ህዝባዊ ሃላፈነታቹ ለመወጣትና በእኩልነት የብዙሃን ድምፅ ለማስተናገድ የተዛባዉ መረጃ በአስቸካይ ሊታረም ይገባል፡፡"

የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ቃል አቀባይ #ሊያ_ካሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ🔝በአማራ ክልል #ደብረብርሃን ከተማ የተዘያዙት 52 ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኢትዮጵያውያን የጠበበን ቦታ ሳይሆን #ፍቅር ነው፡፡›› በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የሀይማኖት መሪ የሆኑት ሃጂ #ሙስባ_ሙሃመድ_አሚን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ🔝

"ሀዋሳ ዛሬ 12:00 ገደማ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ የትራፊክ አደጋ ተከስቷል። አደጋው የተከሰተው ሞተር እና መኪና ተጋጭተው ሲሆን ሞተር ላይ አንድ ቤተሰብ ናቸው ያሉት አባት፣ እናት እና ልጅ ናቸው። ህፃኑ ልጅ ላይ ከባድ ጉዳት ነው የደረሰው። የአደጋውን ምክንያት ፖሊስ እያጣራው ነው። የመኪና አደጋ አስከፊነት ጨምሯል። ቤቢ ከሀዋሳ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ‼️

በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በምትገኘው ሸካ ዞን የተለያዩ ግጭቶች መሰማት ከጀመሩ ጥቂት ወራቶችን አስቆጠሩ።

ይህም አለመረጋጋት #በሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን የትምህርት ጉዳይ አስተጓጉሏል።

የዚህ ችግር መንስኤ በነዚህ ጥቂት ወራት የተከሰተ ሳይሆን ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የሸኮ ሕዝብ ራሳችን በራሳችን እናስተዳድር የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ እንደሆነ በሥራ ምክንያት ነዋሪነቱን አዲስ አበባ ያደረገውና የአካባዊው ተወላጅ #ኮስትር_ሙልዬ ይናገራል።

የያደገበትን አካባቢ 'ትንሿ ኢትዮጵያ' ሲል የሚጠራው ኮስትር የሸካ ዞን የብዙ ህዘቦች መናኸሪያም እንደሆነች ይናገራል።

በተለይም ከጥቂት ጊዜ ወራት በፊት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል የአካባቢውን ሕዝብ ሊያናግሩ ከመጡ ወዲህ ደግሞ ነገሮች መባባሳቸውን የከተማዋ ሰላም ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንገሻ አዲስ ይናገራሉ።

የሸካ ዞን የመዠንገር፣ ሸካ እና ሸኮ ብሔሮች የሚኖሩበት ሲሆን፤ ከአፈ ጉባዔዋ ጋር በነበረው ውይይት ላይ የተሳተፉት ሰዎች እኛን የማይወክሉ ናቸው በሚል መንስዔ ችግሩ እንደተባባሰ ኮስትር ለቢቢሲ ገልጿል።

«አፈ ጉባዔዋ ውይይት ላይ ሳሉ፤ ከአዳራሹ ውጭ ያሉ ወጣቶች ተቃውሞ በማሰማታቸው ወጥተው አነጋግረዋቸዋል። ቢሆንም ጉዳዩ
ሊፈታ ስላልቻለ የአካባቢው ሕዝብ ተቃውሞውን በሥራ ማቆም አድማ እየገለፀ ነው፤ ትምህርት ቤቶችም ዝግ ናቸው» ብሏል ኮስትር።

በቴፒ ከተማ እና የኪ በተሰኘችው ወረዳ ከሆስፒታል በቀር ሌሎች የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሥራ ላይ እንዳልሆኑ ከነዋሪዎችና ከቴፒ ከተማ ፀጥታና ፍትህ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ተሥፋዬ አለም ሰምተናል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ጉዳዩን ለክልልም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት እንዳቀረቡና ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸውም ምሬታቸውን አሰምተዋል።

ከተማዋ ባለመረጋጋቷና የንግድም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ድረስ ልከው እያስተማሩ ያሉ ነዋሪዎች እንዳሉ ኮስትር ያስረዳል።

«እንግዲህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አሁንም ተቸግሮ ነው ያለው፤ የቴፒ ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎችን ያልጠራበት ምክንያት ይህ ነው።» ይላል

የአካባቢው ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጠው ነው እንቅስቃሴዎችን ወደማቆም የተገባው ሲል ኮስትር ሁኔታውን ያስረዳል፤ «ቢያንስ የፌዴራል ቢሮ ዝግ ሲሆን ለምን ሆነ ብሎ የሚመጣ አካል ይኖራል በሚል" እንደሆነ የሚናገረው ኮስትር «አዲሱ የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስም ጉዳዩን ያውቁታል፤ ሶስት ወር ገደማ ሆነው። ነገር ግን ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም።» ብሏል።

ጥያቄው ምንድነው?

የደቡብ ክልል መንግሥት የዞን እና ክልል እንሁን ጥያቄዎችን በመመለስ እና በመመርመር የተጠመደ ይመስላል።

«የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን በደንብ ያውቀዋል፤ በቅርቡ ዞኖችን እንደ አዲስ ሲያዋቅር እንኳ የእኛን አካባቢ ጥያቄ ችላ ብሎታል» በማለት ኮስትር ቅሬታውን ያሰማል።

የሸካ ዞን በዋናነት የሶስት ብሔር ተወላጆች ይኖሩበታል፤ ሸካ፣ ሸኮ እና መዠንገር።

ከእነዚህ ብሔሮች መሃል የሸካ የበላይነት ስላለ እኛ ራሳችን በራሳችን እንደ ዞን ማስተዳደር እንድንችል ይሁን ዋነኛው ጥያቄ እንደሆነ ኮስትር እና አቶ መንገሻ ያስረዳሉ።

ትላንት ረፋዱ ላይ በቴፒ ከተማ አለመረጋጋት ነበር የሚሉት አቶ መንገሻ፤ ጥያቄያቸው ከራስን ማስተዳደር ወደ መሠረተ ልማት ጥያቄ ወርዷል።

ጥያቄያቸውንም ለክልል ምክር ቤት እንዲሁም ለፌዴሬሽን እንዳቀረቡ ገልፀዋል።

"በጣም በርካታ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ጩኸቱን አሰምቷል። አሁንም ቢሮዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም። በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኮ እና የመዠንገር ተወላጆች ዛሬ ወደ ከተማ ወጥተው አወያዩን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥያቄያችንን የመሠረተ ልማት ነው ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለው ወጥተዋል።» ብለዋል፥

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ዋና አማካሪ የሆኑት #አኔሳ_መልኮ ሁኔታውን አጥንተን ምላሽ እንሰጣለን ብንልም የሚሰማን ማግኘት አልቻልንም ይላሉ።

«ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድር የሚሉ አሉ። እኛ ይህ ትክክል ነው ብለን ዛሬውን ምላሽ መስጠት አንችልም። በጥናት ወደፊት ይታያል ተብሎ ተነግሯቸዋል። ዛሬውኑ ይደረገልን፤ ዛሬውኑ ይጠና የሚሉ አሉ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል
አቶ አኔሳ የአቶ ሚሊዮን አስተዳደር ሁኔታውን በማረጋጋት ሥራ ላይ መጠመዱን ይናገራሉ።

«አመራሩ የማረጋጋት ሥራ ላይ ነው፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ነገር እንዳይኖር ነው የምንሰጋው። ዋናው ሰላምና መረጋጋት ነው።»

ለአለመረጋጋቱ ዋናው መንስዔ የሕዝቡ ጥያቄ አለመመለስ ሆኖ ሳለ ጥያቄው መፍትሄ ሳይበጅለት ሰላም ማምጣት አይከብድም ወይ የሚል ጥያቄ ለአማካሪው ሰንዝረንላቸው ነበር።

«ጥናት ይካሄዳል ብያለሁ እኮ፤ አጥኚ ቡድኑም በሰላም መንቀሳቀስ መቻል አለበት። መደማመጥ ከሌለ፤ እኔ ያልኩት ብቻ ይሰማ የሚል ባለበት እንዴት መሥራት ይቻላል?» በማለት ጥያቄ ያነሳሉ የደቡብ ክልል የገጠር ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሊሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማነጋገር ትላንት በሥፍራው ቢገኙም ሰዎች እየመረጡ እንጂ ሁላችንንም አላነገሩንም ሲሉ ነዋሪዎቹ ይወቅሳሉ።

ኃላፊውን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም።

በአካባቢው የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ፀጥታ ለማስከበር እየጣሩ እንደሆነና፤ አከባቢው አሁንም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደማይስተዋልበት ኮስትር ይናገራል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

ሜድሮክ ፒያሳ አካባቢ ያጠረውን ጨምሮ በመዲናዋ ለዓመታት ያለስራ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን አጥር #የማፍረስ ስራ ነገ በይፋ ይጀመራል።

በነገው እለት አጥር የማፍረስ ስራ ከሚጀመርባቸው ውስጥ ሜድሮክ ኢትዮጵያ ፒያሳ አካባቢ ለግዙፍ የገበያ ማእከል ግንባታ ከተረከበው በኋላ ለዓመታት አጥሮ ያቅመጠው ቦታ አንዱ ነው።

ሜድሮክ ፒያሳ አካባቢ ያለውን ስፍራ ለልማት ከተረከበ በኋላ ያለምንም ስራ ከ20 ዓመት በላይ አጥሮ ማስቀመጡም አይዘነጋም።

በተጨማሪም በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች በልማት ስም መሬት ከወሰዱ በኋላ ሳያለሙ ለበርካታ ዓመታት ታጥረው የተቀጡ መሬቶች ላይ ያሉ አጥሮችም ከነገ ጀምሮ መፍረስ ይጀምራሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ጊዜ ታጥረው በቆዩ ቦታዎች ንብረታቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባላነሱት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተከትሎ ነው አጥሮቹ የሚፈርሱት።

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት የደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን እርምጃ መውሰድ የጀመሩት።

አስተዳደሩ ባልለሙ ቦታዎች ላይ ንብረቶቻቸውን ያስቀመጡ አካላት ንብረታቸውን እንዲያነሱ ከሳምንት በፊት መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጅ እነዚህ አካላት ንብረቶቻቸውን ማንሳት ባለመጀመራቸው ምክንያት አስተዳደሩ ወደ እርምጃ የገባው።

አስተዳደሩ የህዝብን ሃብት ለተገቢው ልማትና ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት እንዲውል በጀመረው ተግባር ህገ ወጥነትን እንደማይታገስና፥ ህግ የማስከበር ሃላፊነቱን እንደሚወጣ መግለጹም ይታወሳል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተከሰተ #ግጭት ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው ዕለት በሁለት ተማሪዎች መካከል የተከሰተ ግጭት ሰፍቶ ለተማሪዎች #መጎዳትና ለትምህርት መስተጓጎል ምክንያት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሐይማኖት_ዲሳሳ ለኢቢሲ እንደገለፁት ግጭቱ መጀመሪያ ላይ የግል ቢሆንም ወደ ኃላ ላይ ሰፍቶ ወደ ሁከት ተሸጋግሮ ትናንትና ዛሬ 34 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከተጎችዎቹ ውስጥ 29ቱ ቀላል ጉዳት በመሆኑ ወዲያው ህክምና ተደርጎላቸው ተመልሰዋል፡፡5 ያህሉ ደግሞ በአሶሳ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

አሁን ላይ ተፈጥሮ የነበረው ሁከት #በመብረዱ ተማሪዎችን ጭምር በማወያየት ችግር ፈጣሪዎቹን ለመለየት እየተሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐይማኖት ተናግረዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስም በስፍራው ተገኝተው የማረጋጋቱን ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ተዉቋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በርበራ‼️

የኢትዮጵያ መንግሥት በራስ ገዟ ሱማሌላንድ የሚገኙትን ዲፕሎማቲክ ልዑኩን #ጠርቷል፡፡

በበርበራ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሃላፊው በርሄ ተስፋይ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱም All East Africa የተሰኘው ዜና ወኪል ዛሬ በድረገጽ አስነብቧል፡፡

የቆንስሉ መጠራት በቀጠናው የአሰላለፍ ለውጥ በመምጣቱ እና ኢትዮጵያ ከሱማሊያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት በመጥበቋ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

“ምናልባት ጠቅላይ ሚንስትር #ዐቢይ_አሕመድ ከሱማሌላንድ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቀዝቀዝ እንደሚፈልጉ አንድ ምልክት ሊሆን ይችላል” ሲሉ የሱማሌላንድ ፓርላማ አባል ኢስማኤል አብዲራህማን ለዜና አገልግሎቱ ተናግረዋል፡፡

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት #ሞሃመድ_ፎርማጆ በቅርቡ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳያችን ከመግባት ትቆጠብ ሲሉ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በትግራይ ክልል የሚነገሩ ቋንቋዎችን መሰረት ያደረገ አገር አቀፍ ሲምፖዝየም በመቀሌ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ የትግራይ ቋንቋዎች አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር #ዳንኤል_ተክሉ ዛሬ እንደገለፁት ከህዳር 14 ቀን 2011 ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ሲምፖዝየም ዋና አላማው በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎች ስነ ልሳን፣ ስነ ቃልና ስነ ጽሁፍ እድገት ዙሪያ ለመወያየት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ  አቶ #ገዙ_አሰፋ ዞኑን በምክትል ዋና አስተዳዳሪነት እንደመሩ ሾሟል፡፡

©ena(ዲላ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia