TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ‼️

አትሌት #ሀይሌ_ገብረስላሴ ለፓራኦሎምፒክ ውድድር በ2016 ብራዚል ሄደው መንግስት ላይ ተቃውሞ አሰምተው አሁንም እዛ የሚገኙት አትሌት #ታምሩ_ከፍያለው እና አትሌት #መገርሳ_ታሲሳ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ እንደሚጥር እና የትራንስፖርት ወጪያቸውን እንደሚችል አሳውቋል።

አትሌቶቹ በአሁን ሰአት በሳኦ ፖሎ ከተማ መንገዶች እና ቤተክርስቲያኖች ተጠልለው እንደሆነ ከሁለት ሳምንት በፊት በስልክ ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነግረውት ነበር።

ምንጭ፦ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መውሊድክቡር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ለ ነቢዩ መሐመድ (ሰዓወ) የልደት በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት፦

bit.ly/2FqByFY
አውዳሚው ሰደድ እሳት‼️

የዩናይትድ ስቴትሷን ምዕራባዊ ግዛት በገጠማት እጅግ አውዳሚ ሰደድ እሣት እስከአሁን #የደረሱበት ያልታወቀ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መኖራቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ ከወደመችው ፓራዳይዝ ከተማ የተረፉ ተጨማሪ ሦስት መቶ ሰዎች በደኅና መገኘታቸውም ዛሬ ተገልጿል።

በቃጠሎው ምክንያት እስከትናንት፤ ዕሁድ የሞተው ሰው ቁጥር ሰባ ሰባት መድረሱ የተረጋገጠ ቢሆንም ማንነታቸው የታወቀው ግን የስድሣ ሰባቱ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል።

ሰደዱን ለማቆም ከአምስት ሺህ አምስት መቶ በላይ የእሣት አደጋ ተከላካዮች ተሰማርተው ቀንና ሌት እየሠሩ ሲሆን ቃጠሎው ባይቆምም ወደ ስድሣ አምስት ከመቶ የሚሆነውን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው እየተሰማ ነው።

ፕሬዚዳንት #ዶናልድ_ትረምፕ ከትናንት በስተያ ቃጠሎው ያለፈባቸውን አካባቢዎችና የፓራዳይዝ ከተማን ቅጣይ እና ፍርስራሽ ተመልክተዋ አደጋው እጅግ የከፋ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ የአስቸኳይ ድጋፍ ፌደራል የገንዘብ እርዳታ እንዲላክ የፈቀዱ ሲሆን የፕሬዚዳንቱ ድጋፍ ይቀጥላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው የካሊፎርኒያ ገዥ ጄሪ ብራውን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለ ነቢዩ መሐመድ (ሰዓወ) የልደት በዓል
ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት፦

በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ ለምትኖሩ መላው የእስልምና ተከታይ ወገኖቼ፤ እንኳን ለ1493ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዓ.ወ) የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡

በአስልምና የወራት አቆጣጠር ራቢአል
አወል በሚባለው በሦስተኛው ወር በ12ኛው ቀን በየዓመቱ የሚከበረው ይህ የልደት በዓል በተለምዶ በእኛ ሀገር መውሊድ ወይም መውሊደል ነቢ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ወጣት፣ ዐዋቂ፣ ሕጻን፣ ወንድ፣ ሴት፣ ከተሜ፣ ባላገር፣ የተማረ፣ ያልተማረ፣ ሀብታም፣ ድኻ፣ ሙስሊም፣ ክርስቲያን ወዘተ. ሳይለይ የሚያሳትፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ በመኖሪያ ቤት፣ በመስጊድ እንዲሁም
በእስልምና የመድረሳ ት/ቤቶች በተለያዩ የእምነቱ ሥርዓት የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በድምቀት የሚያከብሩት ይህ የመውሊደል ነቢ በዓል በሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚከበር ወደ መደመር የፍቅር ሰገነት ከፍ ያለ ልዩ በዓል ነው፡፡ በኢትዮጵያችን በሙስሊሙ በዓል ክርስቲያኑ፤ በክርስቲያኑ በዓል ዋቄፈታው፤ በኢድ-
በፋሲካው -በመውሊድ በገናው እና በእሬቻው የእንኳን አደረሰህ፣ እንኳን አደረሰሽ ቅብብሉ የማንለያይና የተዛመድን መሆናችንን አጉልቶ የሚያሳይ ነው። መስተጋብራችንም መልካም ምኞት እስከታከለበት ዝይይር በሚዘልቅ የፍቅር ሸማ ተከብክቦ ወደፊትም ደምቆ ይቀጥላል፡፡

መውሊደል ነቢ በመሠረታዊነት ነቢዩን እና በነቢዩ አማካኝነት ለዓለም የወረደውን የእስልምና አስተምህሮቶች በመዘከር ለሕፃናት በትረካ የሚተላለፍበት በዓል ሲሆን የዲኑ ኡለማዎችም በግጥምና በመንዙማ ለፈጣሪያቸው ምስጋና በማቅረብ ያሳልፉታል፡፡ ዕለቱን በበጎ ሥራ፤ በምጽዋት፣ የተመረጡ የቁርአን ክፍሎችና የመውሊድ ምንባብ በመስማት፣ የመንዙማ ፕሮግራሞች በማካሄድ ከዚያም አልፎ የተቸገሩን በመርዳትና የታመሙትን በመጠየቅ፣
ብሎም ራሳችንን ከክፉ ተግባራት በማራቅ እምነታችንን የምናጠናክርበትም ዕለት ነው፡፡

በመሆኑም መላ የሀገራችን ሙስሊሞች እና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንደ ሁል ጊዜው በመውሊደል ነቢ በዓልም የነበሩንን የሰላም፣ የመረዳዳት፣ የመከባበር እና የመጠያየቅ ባሕል በማስቀጠል የሀገራችንን ሁለንተናዊ ለውጥ እና ሕዳሴ ለማረጋገጥ የበኩላችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

በመጨረሻም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ እና የመደመር በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ፡፡ መልካም የልደት በዓል!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴፒ⁉️

"ዛሬ የምፅፍልህ በጣም ስሜታዊ ሆኜ አዝኜም ነው። ዛሬ ቴፒ ከተማ ላይ የመንግስት መስሪያ ቤት,ትምህርት ቤቶች,የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተዘጉ 107 ተኛ ቀኑ ነው። ይህንን ጉዳይ ምንም አይነት የፖለቲካ ጥግ ሳንይዝ እንደተማረ ምክንያታዊ ሰው እናስበው።

በመጀመሪያ ደረጃ በዘንድሮው አመት የብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች አሉ ለነሱ ብሎ የፈተና ግዜ የሚያራዝም የለም። ስለዚህ ሳይማሩ የመፈተን ችግር ተጋርጦባቸዋል። ይህ ብቻ አይደለም ለትምህርት ፍላጎት ከ50 ኪ.ሜ በላይ በመጓዝ ወደ ሚዛን ሄደው ቤት ተከራይተው ለከፍተኛ ወጪ ተዳርገው እንዲማሩ ሆነዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ተመራቂ ተማሪዎች አሉ። የክረምት የስራ መወዳደሪያ ግዜ ከአሁኑ እያለፋቸው ነው። ይህ ብቻ አይደለም የመንግስት ሰራተኞች ስራ እየሰራችሁ አይደለም በሚል ምንም ደመወዝ አልተከፈላቸውም። ይህም ግማሹን ስራውን ትቶ በየሀገሩ እየዞረ ስራ እንዲፈልግ ግማሹን ደግሞ የሚበላ ለኪራይ የሚከፈል አሳጥቶ መከራ እያሳየ ነው። ወደ አራት ወራት ደግሞ ኢኮኖሚው መቃወሱ የከተማዋን እድገት ለቀጣይ ብዙ አመታት እንዳያንሰራራ ያደርገዋል። ሌላው እንዳያንሰራራ የሚያደርገው ክረምት ይሰበሰብ የነበረው ግብር አለመሰብሰቡ ነው። ይህ ደግሞ ሃገርንም መንግስትንም ይጎዳል። ከዚህ ሁሉ ጋር በየጊዜው የሚሰማው ድብደባና እስር, የየትኛውም ሚዲያ (ከLTV በቀር) ሽፍን ያለመስጠታቸው አሁንም እርግጥ በዶ/ር አብይ ዘመን እየኖርን ነው? ያስብላል።

ይህንን የምልህ በትምህርት አለመኖርና በኢኮኖሚ እጥረት ምክንያት ያለትምህርት ቤት ውስጥ የተቀመጡ ሁለት #እህቶች ስላሉኝ ነው። አዕምሮ ያለው ሰው ግን ይህ በዚህ ዘመን መደረጉ በጣም ያሳዝነዋል። የቴፒ ልጅ ነኝ!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሜቴክ ሰራተኛ‼️

"ሰላም ነው ፀግሽ D እባላለው ያንተው መረጃ ተካፋይ ነኝ! ስለ METEC ሰራተኛ ኣንብቤ ነበር እኔም ኣንዱ የሚቴክ ሰራተኛ ነኝ። ከ16ቱ ኣንዱ ኢንዱስትሪ ውስጥ ነው የምሰራው በጣም ተጨንቀናል ስራ የለም በፋብሪካ ውስጥ ስራ ለማፈላለግ ስራ ልምዳችን ተቀባይ እያገኘ #ኣይደለም ደሞዛችን ከኢትዮጲያ መስራቤት የመጨረሽ ዝቅተኛ የሚከፈለን እኛ ነን ከፍተኛው ለእንጅነር 3500 ነው በምንም ታምር ኑሮውን #መቋቋም ኣልቻልንም ሰራተኛው በብዛት የክፍላገር ልጅ ነው ለ3ት ተከራይቶ ነው የሚኖረው በጣም #ይከብዳል። የሌባ ድርጅት ሰራተኛ እየተባልን ነው!! የሰረቁት የበላይ ሓላፊዎች ናቸው በመታሰራቸው ሰራተኛው በጣም ደስተኛ ነው የቀሩትንም መንግስት ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርባቸው እንጠይቃለን። ሰራተኛው ለስም የመንግስት ሰራተኛ ደሞዝ ይከፈለዋል የመጨርሻ ዝቅተኛ ነው ለሚመለከተው ኣካል ኣድርስልን
ሚድያዎችም የሰራተኛውንም ችግር ተረድተው ኣንጋግረው ኣይርላይ ቢያውሉልን ሕብረተሰቡ የሰራተኛውን ችግር ይረዳሉ ብዬ እገምታለው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጃፓኑ መኪና አምራች ኩባንያ የኒሳን ሊቀመንበር ካርሎስ ጆሰን #በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #ታሰሩ፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቄዶንያ የረሱላችንን (ሰ · ዐ · ወ) ውዴታ የምናሳይበት ትልቁ መንገዳች ሰደቃችን ነው። ኑ! እነኚህን የስው ፍቅር የተጠሙ አረጋዊያንን በዚህ ቀን አብረናቸው። በመሆን አለንላቹ እንበላቸው።

ማክሰኞ ከ 9 ሰአት ጀምሮ
#በመቄዶንያ_የአረጋዊያን_
እንኳን አደረሳችሁ!! 1493ኛው የነብዩ ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል መውሊድ #ማክሰኞ ሕዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ...

ፈጣሪ ምን ያህል #እንደሚወደን እዩ፦
አውሎ ንፋስ አይመታን፣ ሰደድ እሳት አይበላን፣ ሱናሚ አይወስደን፣ መሬት ተንቀጥቅጦ አይውጠን፣ ኢቦላ ገብቶ አልፈጀን... ስለምን በዚህች በፈጣሪ #በምትጠበቅ ድንቅ ሀገር ውስጥ ሆነን እርስ በእርስ #እንበላላለን?? ስለምን እርስ በእርስ እንጠላላለን?? ስለምን ይህቺን ሀገር አልምተን ከአለም ቀዳሚ አንሆንም?? #የኃልዮሽ ጉዞ አይሰለችም?? ዛሬም ትንንሽ ጉዳዮች የኛ መገለጫ መሆናቸው የሚያሳዝን ነው። እስኪ እንቅና ሌላው የደረሰበት #የእድገት ደረጃ ለመድረስ እንቅና!!

መልካም ቀን!!
ከፈጣሪ ተሰጠንን ፀጋ እንጠቀምበት ኃላ እንዳይቆጨን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ዣማል ካሾግዢ‼️

በሳዑዲ አረቢያዊው ጋዜጠኛ ዣማል ካሾግዢ ግድያ ውስጥ “እጃቸው አለ” ያለቻቸው አሥራ ስምንት ሰዎች ወደ ድንበር ወደማይገድበው የአውሮፓ ሃገሮች የዝውውር ክልል ወደሆነው ሸንገን ቀጣና እንዳይገቡ ጀርመን #እገዳ መጣሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሃይኮ ማስ አስታወቁ።

በርሊን በግለሰቦቹ ላይ እገዳውን ከመጣሏ በፊት ከፈረንሣይ እና ከእንግሊዝ ጋር መመካከሯንም ጀርመናዊው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ገልፀዋል።

ብራስልስ ላይ ከተሰበሰሰው የአውሮፓ ኅብረት ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደ መግለጫ ላይ የተናገሩት ማስ “አሁን በራሱ በወንጀሉ ላይና አድራጎቱ እንዲፈፀም ማን እንዳዘዘ መለየትን ጨምሮ ከመልሶቹ ጥያቄዎቹ ይበዛሉ” ብለዋል።

የዣማል ኻሾግዢ ግድያ እንዴት እንደተፈፀመ የሚጠቁመው የተቀረፀ ድምፅ ምን እንደሆነ ሙሉ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ትናንት የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በአድራጎቱ የአመፃና የክፋት መጠን መብዛት ምክንያት ድምፁን እራሱን ማዳመጥ እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

“የሥቃይ ድምፅ ነው፤ አስቀያሚ ድምፅ ነው፤ ሁከትና አመፃ የበዛበት፣ #የጭካሄና የክፋት አድራጎት ነው” ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA የአማርኛው አግልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የቀድሞ ዋና ፅህፈት ቤቱን ዳግም በዛሬው ዕለት ተረከበ።

የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ኦነግ ዛሬ የተረከበው ፅህፈት ቤት እሰከ 1985 ዓ.ም ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑን ተናግረዋል።

ግንባሩ በተለያዩ ምክንያቶች ከሽግግር መንግስቱ ራሱን ካገለለበት ጊዜ ጀምሮ ፅህፈት ቤቱ፥ ከኦነግ ተቀምቶ ለተለያዩ የመንግስት ግልጋሎቶች ሲውል እንደነበር ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

ግንባሩ ዛሬ የፅህፈት ቤቱን ህንፃ የተረከበው ከወራት በፊት በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገረሳ የተመራ ልኡክ በአሰመራ ከኦነግ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት፥ ለግንባሩ እንዲመለስ በተስማሙት መሰረት መሆኑን አቶ ቶሌራ አስታውቀዋል።

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮምያ ክልል መንግስት ቃላቸውን ጠብቀው ፅህፈት ቤቱ ለግንባሩ እንዲረከብ ላደረጉት አስተዋፅኦም ኦነግ ምስጋና አቀርቧል።

የኦነግ ፅህፈት ቤት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በተልመዶ ጉለሌ ተብሎ በሚጠራው ስፊ ግቢ ወስጥ የሚገኝ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ‼️

በጋምቤላ በኩል የገባ 50 ክላሽንኮቭ፣ አንድ ላውንቸር እና 40 ካርታ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ።

የጦር መሳሪያው በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከጋምቤላ ጀምሮ #ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ አዲስ አበባን አልፎ ደብረ ብርሃን ላይ ነው የተያዘው።

የጦር መሳሪያው በገልባጭ መኪና የብረት ረብራብ ተሰርቶለት በመጓጓዝ ላይ እንዳለ የተያዘ ሲሆን በቁጥጥር ስር ከዋሉት 50 ክላሽንኮቭ ውስጥ 37ቱ ባለሰደፍ ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ታጣፊ መሳሪያዎች መሆናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን🔝

በኢትዮጵያ የሕግ ልዕልና ለማክበር የተጀመረው ሂደት ፖለቲካዊ መልክ ይዟል አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።

ሂደቱን ትግራይን #ለማንበርከክ የሚደረግ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም የውጭ እጅ አለበት በማለት በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀረር የውሃ ችግር አልተቀረፈም‼️

ጥንታዊቷ የሐረሪ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ምንጯ የሆነው ሐረማያ ሐይቅ ከነጠፈ በኋላ ከውሃ አቅርቦት ችግር ልትላቀቅ #አለመቻሏን ነዋሪዎቿ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ከሳምንታት በፊትም ሐረር የከፋ የውሃ ጥም አጋጥሟት ‘ድረሱልኝ’ ማለቷ አይዘነጋም።

ኢዜአ ከሰሞኑ በከተማዋ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ከሰሞኑ #ቢሻሻልም ችግሩ በዘላቂነት እንዳልተቀረፈላቸው ይናገራሉ።

የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት እየጣረ እንደሆነ ገልጿል።

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ፤ ውሃ የሚያገኙት ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር እየቆዩ በመሆኑ ለከፍተኛ የኑሮ ጫና እየተጋለጡ ነው።

ከአስተያየት ሰጭወቹ መካከል  ወይዘሮ እታለማው ተሾመ  ውሃ ተቋርጦ እስከ  ወር ፣ በሁለት ወር፣  አንዳንዱም ቦታ ደግሞ   እስከ ስደስት ወር  እንደሚቆይ አመላክተው  ችግሩ  አሳሳቢ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ የታየው “አልጋ ሁሉ አንሶላ ለማጽዳት ውሃ የለም። በየመንደሩ አንድ ጣሳ ውሃ ለማግኘት ህዝቡ እንደ እግዚአብሔር ውሃ እየለመነ ያለው።”

የውሃ አቅርቦቱ  ለሁለት ወር ያህል ተቋርጦ  እንደነበር  አስታውሰው  አንድ ጄሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ድረስ  መግዛታቸውን ያመላከቱት ደግሞ  አቶ ኢበሳ ሲራጅ  ናቸው፡

 አሁን በአንጻንራዊ  መሻሻሉን  አመላክተው  በሳምንትና  በሁለት  ሳምንት  እንደሚመጣ ጠቁመዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የቴክኒክና ኦፕሬሽን የስራ ሂደት ኃላፊ አዲል በከሪ መሃመድ ሐረር ከድሬዳዋ፣ ኤረርና ሐረማያ አፋባቴ ከተሰኙ ስፍራዎች የከርሰ ምድር ውሃ እንደምታገኝ ጠቁመው ከድሬዳዋ አካባቢ ከሚመጣው በስተቀር የኤረርና ሐረማያ አፋባቴ የከርምደር ውሃ ምንጮች ለማሟያነት እንጂ የከተማዋን ህዝብ ውሃ ፍላጎት የሚያሟሉ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት የሚያጋጥመው የውሃ እጥረት ድሬዳዋ አካባቢ የሚገኘው የውሃ ጉደጓድ መጠን የመቀነስና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንደነበር ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንደ አማራጭ የሚያገለግሉት በኤረርና ሐረማያ አፋባቴ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የካሳ ጥያቄዎች በማንሳት የውሃ መስመሩን አቋርጠውት እንደነበር አስታውሰዋል።

ባለስልጣኑ ለአካበባው ማህበረሰብ የቦኖ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ ስራዎች ቢሰሩም ከዋናው መስመር የመጠቀም አዝማሚያዎች ስላሉ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በሌ በኩል በድሬዳዋ ያሉ የውሃ ጉድጓዶችን ጥልቀት ከ150 ሜትር ወደ 500 ሜትር በማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ ፖል የሌላቸውን በመትከል የውሃ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መውልዲ!!

1 ሺህ 493ኛው የነብዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል በእምነቱ ተከታዮች በታላቁ #አንዋር መስጅድ ተከብሯል። በበዓሉ መክፈቻ ላይ ቁርአን የተቀራ ሲሆን በታዳጊ ተማሪዎች ነሺዳ ቀርቧል። የነብዩ መሐመድ የህይወት ታሪክና ያከናወኗቸውን ተግባራት የተመለከተ ትምህርት በሃይማኖት አባቶች የተሠጠ ሲሆን መንዙማና ዱአ /ፀሎት/ በበዓሉ አከባበር የተከናወኑ ተግባራት ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሜቴክ ሰራተኛ‼️

"ሰላም ፀግሺ ስሜ E ይባላለሁ። የምፅፍልህ ከደ/ዘይት ነው፡፡ የሜቴክ ሰራተኛ ነኝ ከደጀን አቭዬሺን ኢንዱስትሪ ነገር ግን ሰሞኑን ከተያዙት የሜቴክ ሃላፊዎች ጋር ሰራተኞችን እንደ #ሌባ ማየት ጥሩ አይደለም። በወረደ ደሞዝ ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን ሌላ መ/ቤት እንኳን እንዳንወዳደር የስራ ልምዳችንን እያዩ የሜቴክ ስለሆነ አይጠሩንም፡፡ እዚጋ መታወቅ ያለበት በጣም ትልቅ አቅምና የስራ ዲሲፒሊን እንዲሁም የፈጠራ አቅምና የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸው ምርጥ ሰራተኞች ነው ያሉት ስለዚህ አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ የሚለው አባባል እየደረሰብን ስለሆነ ማንም የበላይ አመራርና ሃላፊ በፈፀመው ሌብነት ታቺ ያለው የኔ ቢጤ ሰራተኛ 15 ቀን የማያቆይ ደሞዝ እየተከፈለው ስማችን አይጥፋ ወንጀለኛን ወንጀለኛ ስንል እየለየን ይሁን እባክህ ለሁሉም አድርስልኝ፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶ/ር ደብረፅዮን መግለጫ‼️

"አንዳንድ ሚድያዎች በተለይም ደግሞ ኢዜአ እና FBC መግለጫዎችና መረጃዎች በማዛባት የትግራይ ህዝብና መንግስት ገፅታ የማበላሸት ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡

ይህ የሚድያ ብሮድካስቱ ህገ-ደምብ የጣሰና ፈር የለቀቀ አካሄድ መለዉ የአገሪቱ ህዝብ እዉነተኛ መረጃ የማግኘት ህግ-መንግሰታዊ መብቱ የነፈገ ተግባር በትናንትናው ዕለት በወቅታዊ ጉዳይ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ር/ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ደብረፅየን ገ/ሚካኤል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በማዛባት አሁንም ቀጥለውበታል፡፡

በዚህ የተንሸዋረረ #የእብደት አካሄድ የሚደናበር የኢትዮጵያ ህዝብ አለ ብሎ ማሰብ በራሱ ሞኝነት ነው፡፡ ሰለሆነም ለህገ-መንግስቱና ለብሮድካስቱ ስርአት መጠበቅ በመታገል ህዝባዊ ሃላፈነታቹ ለመወጣትና በእኩልነት የብዙሃን ድምፅ ለማስተናገድ የተዛባዉ መረጃ በአስቸካይ ሊታረም ይገባል፡፡"

የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ቃል አቀባይ #ሊያ_ካሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ🔝በአማራ ክልል #ደብረብርሃን ከተማ የተዘያዙት 52 ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኢትዮጵያውያን የጠበበን ቦታ ሳይሆን #ፍቅር ነው፡፡›› በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የሀይማኖት መሪ የሆኑት ሃጂ #ሙስባ_ሙሃመድ_አሚን

@tsegabwolde @tikvahethiopia