TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) በእጁ ከገቡት ማስረጃዎች ተነስቶ የጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጂን ግድያ #ያዘዘው አልጋወራሹ መሀመድ ቢን ሳልማን ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ ተዘገበ። ካሾጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢስታንቡል ቆንስላ ጽ/ቤት የገባው ከሞቱ አራት ቀን በፊት በኢትዮጵያ የመስቀል በዐል ዕለት ነበር።

ምንጭ፦ አልጀዚራ(በአለምነ ዋሴ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህፃን በናያስ ህክምና ...🙏

ከሳምንት በፊት ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ ህፃን በናያስ በህንድ ሙባይ SRCC የህፃናት ሆስፒታል ደርሶ ቀዶ ጥገና ተደርጎለታል። ህፃን በናያስን ቀዶ ጥገና ያደረገው ዶክተር ፕራዲፕ ካውሺኪ ሁሉም ነገር በስኬት መጠናቀቁን ለህፃን በናያስ አባት መምህር በድሉ ተናግረዋል። ለህፃን በናያስ የህክምና ውጪ ለማገዝ ቻናላችን ሲሞክር ነበር። ዘመቻ በተጀመረ ሁለት እና ሶስት ቀናት 50 ሺ ብር ለማግኘት ተችሏል። (የመምህር በድሉ የስራ ባልደረቦች የሆኑ የአአዩ መምህራን ጨምሮ) ከዚህ በኋላ ያለውን 100 ሺ ብር ገደማ ቤተሰቦቹ በብድር እንዳገኙ ነግረው ኛል።

የህፃን በናያስ አባትም ይህን ብለዋል፦

"ፀግሽ ቢያንስ የኛ ልጅ በምንም ቢሆን ህክምናውን አግኝቷል። ሌሎች እንደዚህ እድል ያላገኙ በጣም ብዙ ህፃናት እንዲያገኙ ለሌሎች ብትጀምር በጣም ደስ ይለናል። እኛ ብድሩን ሰርተን መክፈል አያቅተንም ጤናውን ይስጠን እንጂ። ያላቸውን ሁሉ ለማድርግ እጃቸውን ለዘረጉልን በፀሎትም ከኛ ጋር ለነበሩ ለመላው የኢትዮጽያ ህዝቦችን የከበረ ምስጋናችንን እቅርብልን። እግዜር ይስጥልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ‼️

የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይኤ መሐመድ ቢን ሰልማን ከጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ግድያ ጀርባ እጃቸው መኖሩን አረጋገጥኩ ብሏል። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ምንጭ አድርጎ የዘገበው ሲ ኤን ኤን አልጋ ወራሽ #መሐመድ_ቢን_ሰልማን በቱርክ የሳዑዲ ኤምባሲ ውስጥ ጋዜጠኛው እንዲገደል ቀጥተኛ ትእዛዝ መስጠታቸውን አጋልጧል። የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን «ኻሾግጂ እንደ አደገኛና አክራሪ ኢስላሚስት ነው የማየው» ብለው ለአሜሪካ መናገራቸው በቅርብ መዘገቡ ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ADI 2 በኔ እምነት ጥላችሁ በTsegab Wolde ባዶ አካውንት እንዲከፈት የጠየቃችሁ #ብቻ ይህን ተቀላቀላቀሉ @tikvahaid2 በአሁን ሰዓት ለአንድ የአፋር ሎጊያ ልጅ የእገዛ ስራ እየሰራን ነው።

እናቱን በስልክ ሳወራቸው እንዲህ አሉኝ "ዝም ብሎ ከቤት እየወጣ ስለሚሄድ ልጄን መኪና እንዳይበላብኝ ብዬ አስሬዋለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና አካል ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ኀብረተሰቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ጥሪ አቅርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ‼️

በጅቡቲ የኢትዮዽያ የቀድሞ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ በጅቡቲ ቆይታቸው የታዘቡትን ለLTV እንደተናገሩት የሌሎች መንግስታዊ ድርጅቶች ገመና "ሜቴክ #ማረኝ ያስብላል" ብለዋል።

የስኳር ኮርፖሬሽን ከውጭ የገዛው 10 ሺ ኩንታል ስኳር #አሸዋ በመሆኑ ምክንያት በጅቡቲ የሚገኙ የቀን ሰራተኞች አሸዋ አንሸከምም በማለታቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

ከውጭ የተገዛ ስንዴ ኮረት/ድንጋይ በመሆኑ ምክንያት የጅቡቲ ወደብ ማሸጊያ ማሽንን መስበሩንም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማይጨው🔝በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን፣ የማይጨው ከተማ ነዋሪዎች ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። ሰልፈኞቹ የራያ ህዝብ የልማት እንጅ የማንነት ጥያቄ የለውም ሲሉ ተደምጠዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀረር🔝

"ፀግሽ ዛሬ ሀረር ፈዲስ የሚባል አካባቢ የስላሴ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ የሙስሊም አባቶች ተገኝተው ነበር። #ኢትዮጵያዊነት" ሶል ከሀረር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ🔝

አፍሪካ ለተጠናከረ የንግድና የህዝቦች እንቅስቃሴ ዲጂታል እድሎችን በኢ-ገቨርናንስ ማእቀፍ ስር በአፋጣኝ መጠቀም እንዳለባት ጠቅላይ
ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የአፍሪካ ህብረትና የተባብሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዛሬ ባዘጋጁት የጎንዮሽ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

ስብሰባው "ዲጂታል ማንነት ለ2030 የልማት አጀንዳና ለአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063" በሚል ርእስ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በተለይም ዲጂታል ምጣኔ ሀብት እያሳየ የሚገኘውን እድል ከግምት ውስጥ በማስግባት የአፍሪካን ልማት በትክክለኛ ህገ ደንቦች የሚመራ ዲጂታል አሰራር ከፍ ማድረግ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስምረውበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተባብሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዲጂታል ማንነት ኢኒሼቲቭ አማካሪ ቦርድ ተባባሪ #ሊቀመንበር ናቸው።

ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia