TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ🔝

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና #የሰላም_ኮንፈረንስ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአማራ ከኦሮሚያ ከጋምቤላ ክልሎች የተወከሉ የህዝብ ወኪሎችና አመራሮች እንዲሁም የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኮንፈረንሱ አላማም የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከመከበሩ በፊት የአገራችን ሰላምና መረጋጋት ችግር በሚፈታ እና ለዘመናት ስር ሰዶ የቆየው በመከባበር በመደጋገፍ እና በመቻቻል የተመሰረተውን የህዝቦች ግንኙነትና ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ነው።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊድያ ታፈሰ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታን ትመራለች። ነገ በሚጀመረው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ጋና ከአልጄሪያ የሚያደርጉትን የመክፈቻ ጨዋታ የኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በዋና ዳኝነት ጨዋታውን ትመራለች። በ2016 ካሜሮን ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የመክፈቻ ጨዋታውን መምራቷ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ካፍ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ🔝

"ሠላም ፀግሽ ዛሬ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በቻሪቲ ክበብ አማካኘነት ለተቸገሩ ወገኖች የሚውል አልባሳት ተሰብስቧል እንዲሁም በተማሪው አማካኝነትም ታጥበዋል እነዚህም መልካም ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሁሉን ድጋፋ እንሻለን! ሁላችንም ስንተሳሰብ እንጂ ስንቀማማ አያምርብንም! @henossol"

@tsgabwolde @tikvahethiopia
በሙከራ ላይየሚገኘው የTIKVAH-ETH የሞባይል መተግበሪያ አሁንም ችግሮችን ለመታት እየተሞከረ ነው።

ተጨማሪ የተስተካከሉ ችግሮች፦

- Android 5 ላይ “Unfortunately TIKVAH-ETH stopped working" የሚለው ችግር ተቀርፏል
- የሚጠቀመው የዳታ መጠን ቀንሷል ስለዚህም ካርድ ፍጆታው በደንብ ቀንሷል
- ፍጥነቱ ጨምሯል
- landscape mode ሲሆን crash አያረግም
- ሌሎችም

ይህ ለህዳር ወር የመጨረሻው update ነው። ቀጣዩ update በታህሳስ የሚለቀቅ ይሆናል።

ማን ኛውም አስተያየት ካለ @tikvahethbot
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ🔝

ክቡር ጠ/ሚር #ዐቢይ_አህመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ: ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ: ከጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ እና ከጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተገናኝተው ተወያዩ። ውይይቱም በአህጉራዊ ጉዳዮችና የጋራ የትብብር አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዬጵያ ስላለው የለውጥ ሂደትና ለአህጉሪቱ ስለሚኖረው የልማት አስተዋፅኦ ተወያይተዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታላቁ ሩጫ‼️

ነገ እሁድ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በሚያካልላቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙባቸው #ተለዋጭ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

44 ሺህ ሯጮችን የሚያሳትፈው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከነገ በስትያ መነሻና መድረሻውን ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት አድርጎ ይከናወናል።

ሩጫው ከስድስት ኪሎ አደባባይ ተነስቶ ምኒሊክ ሆስፒታል-ቀበና-እንግሊዝ ኤምባሲ-በሾላ ገበያ ዞሮ በሱመያ መስጊድ-ሲግናል-አቧሬ-ራስ አምባ ሆቴል አድርጎ ወደ አራት ኪሎ በመሄድ ፍጻሜውን ስድስት ኪሎ አደባባይ ያደርጋል።

ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ አካባቢ የሚያልፉ አሽከርካሪዎች የሚጠቀሟቸውን ተለዋጭ መንገዶች ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረት ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ ሽሮ ሜዳ ፈረንሳይ ለጋሲዮን የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ከጊዮርጊስ- በአፍንጮ በር-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአልአቅሳ መስጊድ ወደ መነን አቅጣጫ መጠቀም ይችላሉ።

ከሽሮ ሜዳና ፈርንሳይ መስመር ተነስተው ወደ ስድስት ኪሎ፣ አራት ኪሎና መስቀል አደባባይ የሚጓዙ ደግሞ በተለዋጭነት በአፍንጮ በር- ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን-ቸርችል ጎዳናን ይጠቀማሉ።

እንዲሁም ከሽሮ ሜዳ ተነስተው ወደ መገናኛና ቦሌ አቅጣጫ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች በአፍንጮ በር-ጊዮርጊስ አድርገው በቸርችል ጎዳና ኢሚግሬሽን-በካሳንቺስ-ኡራኤል ቤተክርስቲያን አድርገው ወደ መገናኛ መጓዝ ይችላሉ ብሏል።

በተጨማሪም ከነገ ህዳር 8 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ሩጫው በሚካሄድባቸው መንገዶች ላይ አሸከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ግጭት‼️

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አስተዳደር ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አስተዳደር ዛሬ ለDW ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላት ወደ ሥፍራው መግባታቸውን ተከትሎ ግጭቱ #እየተረጋጋ መምጣቱን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በመስቃን እና በማረቆ ህዝቦች መካከል ባለፈው ረቡዕ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በመሬት ይገባኛል በተፈጠረ አለመግባባት ነበር። ግጭቱ የተከሰተበት ቦታ በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ሰሜን ዲዳ እና ባቶ ፎቶ በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች የነበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም መፈናቀላቸውን የዓይን እማኞች ለDW ተናግረዋል።

 በደቡብ ክልል መስቃን ወረዳ መሰል ግጭት ሲከሰት የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው መስከረም በደረሰው ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙ ይታወሳል።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲአን‼️

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ለሲዳማ መብት መከበር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስታወቀ።

በውጭ የሚኖሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የንቅናቄው አባላት ሀዋሳ ከተማ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበሉ ላይ የሲዓን ሊቀመንበር ዶክተር #ሚሊዮን_ቱማቶ እንደተናገሩት ንቅናቄው ዘመን ተሸጋሪ ጭቆና፣የፍትህ እጦትና የአስተዳደር በደሎች የወለዱት ነው።

ከ1970 ጀምሮ የሲዳማ ህዝብ መብት እንዲከበር ንቅናቄው ረጅምና አድካሚ ትግል ማድረጉንም ገልጸዋል።

የተፈጠረውን እድል ገቢራዊ እንዳናደርግ የሚጥሩና የህዝቦችን ጥቅም በመቃወም አንድነትን የሚፈታተኑ የፖሊቲካ ሃይሎችን መታገል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ትላንት የገባውን የልኡካን ቡድን የመሩት ዶክተር በዛብህ በራሳ በበኩላቸው ንቅናቄው በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ  ሰላማዊ ትግል በማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

ከጄኔቫ የመጡት አቶ ደጀኔ ወልደአማኑኤል በፌዴራልና በክልል መንግስት እንዲሁም በአባሎቻቸውና በደጋፊዎቻቸው የደረገላቸው አቀባበል እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

በፖሊቲካው ዓለም ያለውን ልዩነት በማስወገድ ለሲዳማ የሚታገል አንድ አውራ ፓርቲ እንደሚገነቡና የግለሰብና የቡድን መብቶችን ህዝቡ እንዲረዳ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የክልሉን ርዕስ መስተዳዳር ወክለው የተቀበሏቸው የርዕሰ-መስተዳደሩ አማካሪ አቶ አኒሳ መልኮ እንኳን ወደ ምድራችሁ በደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል፡፡

በሀገሪቱ የመጣውን የፖለቲካ ለውጥ ተከትሎ በውጭ ሀገር ሆነው ለዜጎች ነፃነት፣ ክብርና እኩልነት ሲታገሉ የነበሩ ፓርቲዎች ከበርካታ ዓመታት በኋላ እየተመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በሀገሪቱ የታየውን ለውጥ በመጠቀም ራሱን እንዲያጠናክርና ለሲዳማ አንድነት በመስራት ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ በጋራ እንሰራለን” ብለዋል፡፡

ከአውስትራሊያ፣ ከስዊዘርላንድና አሜሪካን የመጡት የንቅናቄው አመራሮች ትላንት ሃዋሳ ሲገቡ ደጋፊዎቻቸው፣ አባሎቻቸው፣ የዞንና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ እና አዲስ አበባ!!

ድምፃዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን በአዲስ አበባ ስታዲየም #በነፃ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰምቷል። ለአዲስ አበባው ኮንሰርት ምንም አይነት ክፍያ እንደማይቀበል የተነገረ ሲሆን ለሙዚቃው ዝግጅት ከአዘጋጆቹ በተጨማሪ የተወሰነውን ወጪ እራሱ ይሸፍናልም ተብሏል። ህዝቡም ኮንሰርቱን በነፃ እንደሚታደምበት ነው የተገለፀው። ከአዲስ አበባው በአይነቱ የተለየ የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ድምፃዊው #በሀዋሳ ከተማ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ እቅድ እንዳለው ለመስማት ተችሏል። የሙዚቃ ዝግጅቶቹ መቼ ይካሄዳሉ?? የሚለው ግን የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ ኢትዮፒካሊንክ የሬድዮ ዝግጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia