TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን ደስ አለን💥💫የTIKVAH-ETH የሞባይል መተግበሪያ(application) ነገ ምሽት 2:00 እናተ ጋር ይደርሳል!!

.የተመረጡ ሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜናዎች
.ስፖርት
.ቢዝነስ
.መዝናኛ

Apk. 4.1 mb (ነገ ምሽት እናሰራጨዋለን) ለአድሮይድ!

ለአይፎን(ios) ተጠቃሚዎች በሚቀጥለው ወር ይቀርባል።

መተግበሪያው፦ የቻናላችንን ተደራሽነት ለመጨመር በማሰብ የተዘጋጀ ነው። የቴሌግራም ቻናላችን #ተጠናክሮ ይቀጥላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ታዋቂ እና አነጋጋሪ መፅሃፍት በገበያ ላይ ዋሉ‼️መፅሀፍቱን በሁሉም መፅሀፍት ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። ተጨማሪ በዚህ ስልክ በመደወል መፅሀፍቱን ማግኘት ይቻላል፦ +251911650882
Forwarded from Betty G
Vote for me
ON

WWW.AFRIMA.ORG

@ITSBETTYG
ሰበር ዜና‼️

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ሀላፊ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር አቶ #ያሬድ_ዘሪሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስት አስታወቀ። ጠቅላይ አቃቤ ህግ #ብርሀኑ_ፀጋዬ ከሌሊቱ 10 ሰዓት በትዊተር ገፃቸው ይፋ እንዳደረጉት ተጠርጣሪው አቶ ያሬድ በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዋል። ዝርዝር መረጃ ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩውሪቲ ዲቪዥን ሀላፊ ኮለኔል #ጉደታ_ኦላና በቁጥጥር ስር ዋሉ። ኮለኔል ጉደታ ኦላና በሜቴክ ውስጥ የተፈፀመ የሙስና ወንጀልን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የአቃቤ ህግ ስራን በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኮሎኔል አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆና ተሾመች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ምሽት ላይ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል። ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአስቸኳይ ስብሰባው ሰሞኑን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት በፈቃዱ ባገለለው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ቦታ በውክልና የፌዴሬሽኑ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉን በፕሬዚዳንትነት ሰይሟል። በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት ለቀሪዎቹ ሁለት ዓመታት የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንት እንደሚያስመርጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሀላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል የነበሩት አቶ #ያሬድ_ዘሪሁን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በትላንትናው እለት በዱከም ከተማ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሀላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አቶ #ያሬድ_ዘሪሁን ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የOBN ሪፖርተር ጫላ በረካ እንደዘገበው ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ሌሊት 5 ሰዓት ላይ #ኮኬት በሚባለው ሆቴል #በሌላ ሰው ስም አልጋ ይዘው ከ22 ሺህ 105 ብር ጋር ነው፡፡ የአቶ ያሬድ ባለቤትና ሹፌራቸው እርሳቸውን በማስመለጥ ተጠርጥረው ቀደም ብለው #በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ያሬድ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሀላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል የነበሩት አቶ #ያሬድ_ዘሪሁን ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ህዳር 5 ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ወደ ኬንያ ለመሸሽ ሲሞክሩ በፌደራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ ክትትል ነው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲዳማ🕊ወላይታ‼️

በሲዳማና ወላይታ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ዕርቀ ሠላም ለማውረድ #በገለልተኛ ሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ካለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የዕርቅ ውይይት በሁለቱ ሕዝቦች ተወካይ ሽማግሌዎች መካከል ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

በተደረገውም ውይይት የሚያቀራርብና እጅግ #ጠቃሚ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት የተደረሰ ሲሆን ይህንን በሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማጠቃለል ከሁለቱም ወንድም ሕዝቦች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ኀዳር 9/2011 ዓ.ም በሀዋሳ #ሲዳማ_ባህል_አዳራሽ የዕርቅ ኮንፈረንስ የሚደረግ ሲሆን ኀዳር 11 /2011 ዓ.ም ተመሳሳይ መድረክ #በወላይታ_ሶዶ ተካህዶ የዕርቅ ኮንፈረንስ እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ዕርቁ በሁለቱም #ወንድም ሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መሻከር በማስወገድ መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለማውረድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም፤የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በጉራጌ ዞን መስቃንና ማረቆ ወረዳዎች መካከል ባለፉት ሁለት ቀናት በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉንና ቤቶች መቃጠላቸውን ከአካባቢው ተፈናቅለው ወደ ቡታጅራ ከተማ የመጡ ዜጎች ተናገሩ። በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች መስከረም 3 እና 4 በተፈጠረ ግጭት ከ20 የማያንሱ ዜጎች ህይዎት ማለፉና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረጽዮን‼️

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በክልሉ ምዕራባዊ ዞን ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ጀምረዋል።

የዞኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ታረቀ ለኢዜአ እንደገለጹት ዛሬ ከቀትር በኋላ የተጀመረው ውይይት በልማት ፣በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

በዞኑ ከሚገኙ አራት ወረዳዎች የተወጣጡት የህዝብ ተወካዮችም በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን በዞኑ የሚታዩ ዋና ዋና የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ያሉበትን ደረጃ እንደሚገመግሙ ተናግረዋል።

ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ ከተወካዮቹ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ላይም ላጋጠሙ ችግሮች የመፍትሔ ሃሳብ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኛው‼️

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ሜጄር ጄኔራል #ክንፈ_ዳኘውን ጨምሮ የስድስት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ነው።

ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ገቢዬ በጡረታ ማገኘው 4 ሺህ ብር ብቻ በመሆኑ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ማለታቸውን ተከትሎ በዚህ ጥያቄያቸው ላይ ፖሊስ ተቃውሞውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

የፌደራል ፀረ ሙስና ስነ ምግባር ኮሚሽን ያስመዘገቡትን ሀብት እና እስከ ህዳር 5 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ድረስ ስሙ ባልተጠቀሰ ባንክ ውስጥ ያላቸው ተቀማጭን በማስረጃነት አቅርቧል።

ጋዜጠኛ ፍጹም የሽጥላ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ ቆሞላታል።

ፖሊስ ለፍርድ ቤት እንዳብራራው፥ ጋዜጠኛ ፍጹም፤ ፍፁም ኢንተርቴይንመንት ለተባለ ድርጅት ባልተገባ ስፖንሰርሺፕ ብር 954 ሺህ 770 ብር የህዝብ ገንዘብ መውሰዷን ገልጿል።

በገንዘቡም የንግድ ድርጅት ከፍተው አፍርተዋል ያፈሩትንም ሀብት ሰውረዋል በሚል መጠርጠሯን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

ፍርድ ቤቱ በአሁኑ ወቅትም የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ይገኛል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

ህዳር 8 እና 9 ቀን 2011 በአዲሰ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች  ጉባኤ  የትራፊክ #መጨናናቅ እንዳይከሰት ሕብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠየቀ።

ጉባኤውን ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት አሽከርካሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጡና መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆኑ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

እግረኞችና አሽከርካሪዎች የሞተረኛ ትራፊክና የእሳት አደጋ የአምቡላንስ ሳይረን ድምጽ ሲሰሙ ቀኛቸውን ይዘው በማሳለፍ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደረጉም ተጠይቋል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከዛሬ ህዳር 6 ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ድረስ ከፓርላማ መብራት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦሎምፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድሽፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድና ኤርፖርት መንገዶች ግራና ቀኝ አቅጣጫ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

ከፓርላማ መብራት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ በፍል ውሃ- ብሄራዊ ቲያትር -ሜክሲኮ አደባባይ-አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ዙሪያ መንገዶችም እንዲሁ።

ከፓርላማ መብራት – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን  ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን፣ ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ሕብረት ዋናው በር ድረስ ያሉት መንገዶች ላይም ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ- መስቀል አደባባይ -መገናኛ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በኮካ ኮላ ድልድይ -በአብነት ተክለ ኃይማኖት -ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ ወይም በኤክስትሪም ሆቴል ቴዎድሮስ አደባባይ -አሮጌ ቄራ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ተጠቁሟል።

በባልቻ ሆስፒታል -አረቄ ፋብሪካ- ጎማ ቁጠባ- ጥቁር አንበሳ -ኢምግሬሽን -አርማ ጋራዥ -በንግድ ማተሚያ -አሮጌ ቄራ አማራጮችም ተጠቅሰዋል።

ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ሳር ቤት -ጎፋ ማዞሪያ-ቄራ ጎተራ- ጎርጎርዮስ -ቦሌ ሚካኤል- ሩዋንዳ -አትላስ- ዘሪሁን ህንጻ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ነው የተገለጸው።

የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ -ዘሪሁን፣ቀለበት መንገድ- ቦሌ ሚካኤል- ሀኪም ማሞ ወደ ጎተራ፣ ቀለበት መንገድ-መገናኛ- ዳያስፖራ አደባባይ-እንግሊዝ ኤምባሲ ፣ ቀለበት መንገድ -መገናኛ- አድዋ ጎዳና -አዋሬ- አራት ኪሎ፣ከፍላሚንጎ-ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መንገዶችን መጠቀም እንደሚቻልም ተጠቅሷል።

ከባድ ተሽከርካሪዎችም ከፓርላማ እሰከ ቦሌ መንገድ እና በአፍሪካ ሕብረት ዙሪያ ያለውን መንገድ መጠቀም ክልክል መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በዱራሜ ከተማ የከምባታ ብሔረሰብ የራሱን ክልል እንዲመሰርት የሚጠይቅ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia