ጥቆማ ለአዲስ አበባ ፖሊስ‼️
ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከትላንት በስቲያ አርብ ሁለት ህንዳዊያን(አንዱ ቀይ የወጣት ቁመና ያለው ሌላኛው ደግሞ ጠይም ፀጉሩ ትንሽ ነጣ ነጣ ያለ) በአንድ ፋርማሲ ውስጥ በመግባት ተቸግረናል ይህ ስልክ ይዛችሁ ብር አበድሩን አሁን መጥተን እንከፍላለን በማለት 5,000 ብር ገደማ ይዘው ተሰውረዋል። ስልኩ ሳምንሰንግ ኖት 9 #ኮፒ ነው። ህንዳዊያኑ ሌሎች አካባቢዎችም በመዘዋወር ተመሳሳይ የማጭበርበር ድርጊት ሊፈፅሙ ስለሚችሉ የከተማይቱ ፖሊስ ጉዳዩን እንዲከታተለው ለመጠቆም እንወዳለን።
ለፖሊስ ተጨማሪ መረጃ- የያዙት ስልክ ቁጥር፦ 0945 42 47 85
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ኢንጂነር ታከለ ኡማ...
"በዛሬው እለት በከተማችን በተደረገዉ የቡና ክለብ እና ኢትዮ—ኤርትራ ወዳጅነት ሩጫ #በሰላም ተጠናቋል። በዚህ አጋጣሚ የከተማችን ወጣቶችና እሩጫዉን ላስተባበሩት ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።"
@tsegabwolde @tikvahehiopia

ሩጫው በሰላም ነው የተጠናቀቀው‼️
የኢትዮ ኤርትራ የሰላም የአንድነትና የፍቅር ሩጫ #ያለምንም እንከን በሰላም መጠናቀቁን የሩጫው አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተሳተፉበት ሩጫ የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች በማስተሳሰር በኩል ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
የሩጫው አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈረ እንዳሉት ሩጫው የኢትዮ ኤርትራ የፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲጎለብት መሰል መርሃ ግብሮች የሚያበረክቱት አስተዋዕኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ etv

አስቸኳይ‼️
ባቱ(ዝዋይ) መግቢያ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ40 ደቂቃ በላይ መንገድ ተዘግቷል። በደረሰኝ መረጃ የትራፊክ ፖሊስም ሆነ ሌላ አካል በቦታው አልተገኘም። በዚህ ተጓዦች ለመቆም ተገደዋል የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ እናቀርባለን።
የአደጋውን ዝርዝር መረጃ እንደደረሰኝ አቀርባለሁ።

ደራ⬆️ከአዲስ አበባ በ220 ኪ.ሜ በምትገኘው ደራ አካባቢ ከፍተኛ የሆን የመሰረተ ልማት ችግር አለ። በተለይ በመቶ ሺዎች በሚኖሩበት አካባቢ በመንገድ ችግር ምክንያት ህዝቡ እየተሰቃየ ነው። በዛው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት መንግስት አካባቢያችንን ይይልን ብለዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፓሬሽን(ሜቴክ) የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ቁጥር ዛሬም ጨምሯል። በተጠርጣሪዎች ላይ ያለው መረጃም ገና #ተጠናክሮ አላለቀም። ከዚህ በኃላም በቁጥጥር ስር የሚውሉ እንዳሉ እና #የሚለቀቁም ሊኖሩ እንደሚችሉ ሸገር 102.1 ዘግቧል። ይህንን መረጃ በተመለከተ ነገ አልያም ከነገ በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ‼️
ድሬዳዋ በሚፈለገው ደረጃ እንዳታድግና በየደረጃው የሚገኘውን ሕዝብ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን #እንቅፋት የፈጠረው ሕገ-መንግሥታዊ እውቅና የሌለው ቻርተር በአስቸኳይ ሊነሳላት እንደሚገባ የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ።
የህግ ባለሙያዎቹና ”ሳተናው” የተባለ የድሬዳዋ ወጣቶችን ያካተተ ኅብረት ከድሬዳዋ አመራሮች ጋር በማህበራዊና በምጣኔ ሃብታዊ፣ በመልካም አስተዳደርና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ባለሙያዎቹና ወጣቶቹ በዚሁ ጊዜ ከተማዋ ዕድገቷ ተጠብቆና ነዋሪዎቿም የልማትና የምልካም አስተዳደር ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት አስተዳደራዊ መዋቅር ሊፈጥርላት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ምንጭ፦ ena

ጋሞ ጎፋ‼️
በጋሞ ጎፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች የፀረ-ቢጫ ወባ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የአለም ጤና ደርጅት ገለፀ።
የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር #ዮሐንስ_ዳምጠው በቅርቡ የቢጫ ወባ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ተከስቶ የ10 ሰዎች #ህይወት ማለፉን
ገልፀው በሽታው ወደ አጎራባች አካባቢዎች እንዳይዛመት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሽታው ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን እንዳይዛመት የወላይታ ዞን አጎራባች በሆኑት ቦረዳና ቁጫ ወረዳዎች በቅርቡ የፀረ-ቢጫ ወባ ክትባት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
ቢጫ ወባ በአለም በገዳይነት ከሚታወቁ በሽታዎች ቁጥር አንድ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ዮሐንስ መከላከያ ክትባቱን የወሰደ ሰው በበሽታው እንደማይጠቃ ተናግረዋል፡፡
የፀረ-ቢጫ ወባ ክትባት ዕድሜያቸው ከ ዘጠኝ ወር በላይ ለሆኑ የሚሰጥ ስለሆነ የአከባቢው ነዋሪ ክትባቱ በሚሰጥበት ወቅት ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ እንዲከተብ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ዮሐንስ ዳምጠው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

#update በሐሰተኛ ደረሰኝ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጽመዋል የተባሉ 124 ድርጅቶች #እየተመረመሩ ነው። በሕገወጥ ድርጊታቸው ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰብ አልተቻለም ተብሏል።
Source: JAD Business Group
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Source: JAD Business Group
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ‼️
ትላንትና በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ ሩጫ ላይ ቦንብ ፈነዳ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ልታውቁት ይገባል። ሩጫው በሰላም ተጀምሮ በሰላም ነው የተጠናቀቀው።

#update አማራ ክልል⬇️
በአማራ ክልል የሚገኙ ከተሞች የመብራት ኃይል #እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ።
የፌዴራል መንግስትም በክልሉ ያለው ኢ-ፍትሃዊ የመብራት አቅርቦች ችግር እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሚገኙ ከተሞች በመብራት ኃይል አቅርቦትና እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ተግባር ማከናወን አልቻሉም።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ የሚገኙ ከተሞች ከሌሎች ክልሎች አንጻር ፍትሃዊ የኃይል ስርጭት እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
ክልሉ በከተሞች ያለው የመብራት አቅርቦት እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠይቋል ያሉት አቶ ፈንታ፤ የፌዴራል መንግስት ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
የቢሮው ሃላፊ አሁን እየታየ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭትና አቅርቦት ችግር ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት ችግር በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ የማሰራጫ መስመሮችን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

ከቦንጋ...
"ሀይ ፀግሽ ዛሬ መንገድ ተከፍቶ በከፊል እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ሆኖም ግን ዘላቂ መፍትሔ ይፈልጋል። Esa ነኝ ከቦንጋ"

አዲስ አበባ‼️
አዲስ አበባ #ጎዳና ቤቴ የሚሉ ዜጎች #እየበዙባት ነው ተባለ፡፡ ውሎ እና አዳራቸውን ጎዳና ያደረጉ ዜጎች መብዛት ከራሳቸው አልፎ በከተማዋ ጭምር የተለያዩ ማህበራዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ቀውሶች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡
በመሆኑም ይህን ሀገራዊ ችግር ለመቀነስ የሚመለከታቸው አካላት እጅ ለእጅ ተያይዘው መረባረብ እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል፡፡
መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች ጎዳና የወጡ የማህበረሰቡ አባላትን ለማንሳት ማህበራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ
ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ማህበራዊ ጥበቃ ፈንድ እና ልማታዊ ሴፍትኔት ኤጀንሲ ሲናገሩ እንደሰማነው ከሆነ በ2011 ዓ.ም መግቢያ ላይ ባደረገው የሃብት ማሰባሰብ መርሃ ግብር የ34 ሚሊዮን ብር እርዳታ ከባለሃብቶች ቃል ተገብቶለት ነበር፡፡
ነገር ግን እስካሁን መሰብሰብ የተቻለው 6 ሚሊዮን ብር መሆኑን ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡
ሌሎቹ ቃል የገቡትን እንዲሰጡ ቢጠየቁም የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ አልከፈሉም ተብሏል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት ጎዳና ላይ የወጡ ዜጎች እንዲነሱ ቢደረግም አሁንም ድረስ ቁጥሩ እየጨመረ እንጂ ሲቀንስ አይታይም ብሏል ኤጀንሲው፡፡
ሰዎቹን ከጎዳና ላይ ለማንሳት በቂ ጥናትና ዝግጅት አለማድረግ ወደ ጎዳና እንዲመለሱ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ሰምተናል፡፡
በየጎዳናዎቹ ጥጋጥግ ኑሮአቸውን ያደረጉ አብዛኛዎቹ ዜጎች ማለትም ከ90 በመቶ በላዮቹ ከመላው አገሪቱ ገጠሮች ስራ አጥነትና ድህነት የገፋቸው መሆናቸው ሲነገር ሰምተናል፡፡
ኤጀንሲው በየጎዳናው የወደቁ ዜጎችን ማቋቋም በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት ውይይት አድርጓል፡፡
ኤጀንሲው በዚህ ዓመት ከ5 ሺ በላይ ሰዎችን ከጎዳና ለማንሳት ማቀዱን በውይይቱ ወቅት ተናግሯል፡፡
እነዚህን ዜጎች የተለያዩ ስልጠናዎችና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ ለ1 ዓመት ካቆየሁ በኋላ በድርጅቶች እንዲቀጠሩና የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
ለዚህም የባለሃብቶች እና የረጂ ድርጅቶችን እገዛ ጠይቋል፡፡ የአዲስ አበባ ጎዳና ነዋሪዎችን ቁጥር በዘላቂነት ለመቀነስ ከክልሎች ጋር ሆኖ በጋራ መስራት እንደሚገባም ሃሳብ ቀርቧል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1

#Update በኦዞን ንጣፍ የተከሰተውን ጉዳት በ50 ዓመታት ሙሉ በሙሉ ማገገም እንደሚችል ሳይንቲስቶች #አረጋገጡ። በኦዞን የአየር ንጣፍ ላይ ተከስቶ የነበረዉን ጉዳት በ50 ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንዲያገግም ማድረግ እንደሚቻል የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን‼️
ህዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ ብሔሮች ከራሳቸው በተጨማሪ የአንድ ሌላ ብሔር ባህላዊ አለባበስና ጭፈራ ትርዒት እንደሚያሳዩ ተጠቆመ፡፡
የ13ኛው የኢትዮጵየ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ዝግጅት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የክልሎች ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች የበዓሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ትላንት በአዲስ አበባ ተገምግሟል።
የበዓል ዝግጅት አስተባባሪ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኑረዲን ማህሙድ እንዳሉት፤ በዓሉ አገራዊ አንድነት፣ ሰላምና መቀራረብ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ነው።
ከነዚህም መካከል የራስ ብቻ ሳይሆን አንዱ ብሔር የሌላውንም ባህል ጨምሮ እንዲያሳይ ለማድረግ ሁሉም የቤት ስራ ወስዶ ዝግጅት እንዲጀምር መደረጉ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በዚህም መሰረት ትግራይ ክልል ከራሱ በተጨማሪ የኦሮሞ ህዝብን ባህል የሚያሳይ ትዕይንት ለማሳየት፣ ኦሮሚያ ክልል ደግሞ ከደቡብ ብሔሮች መካከል የተወሰኑትን መርጦ፣ ደቡብ ደግሞ የአማራን አማራ ደግሞ የሱማሌን ለማሳየት ፍቃደኛ መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።
ሁሉም ክልል ከራሱ በተጨማሪ የሌላውን ክልል አንድ ወይም ከዚያ በላይ ብሄር ባህላዊ አለባበስ ጭፈራና ትዕይንቶችን ለማሳይት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ከዚህም ሌላ በዓሉ ሲከበር አገራዊ አንድነት የሚያጠናክሩ ምክክሮች በማድረግ እንዲሆንና ሲምፖዚዬሞች እንዲዘጋጁ በመወሰኑ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጽሁፎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ደግሞ ግጭቶች ተከስተው በነበሩባቸው አካባቢዎች ላይ ሁሉም የሚሳተፍበት ህዝባዊ መድረክ በማዘጋጀት ውይይትና እርቅ እየተደረገ እንደሆነ አመላክተዋል።

ኢራቅ‼️
በኢራቅ የካቢኔ አባላት #በፌስቡክ ማስታወቂያ ተመረጡ፡፡ የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር #አደል_አብዱል_ማህዲ በበይነ መረብ ከተወዳደሩ 15 ሺ ሰዎች መካከል የካቢኔያቸው አባል የሚሆኑ 5 ሰዎችን መርጠዋል። ይህ በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ውስጥ ያልተለመደ የቅጥር መንገድ መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ማህዲ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተዋወቀ ሲሆን ከሚያስፈልጉት 14 የካቢኔ አባላት መካከል 5ቱ በዚህ መንገድ ተመርጠዋል።

የኢቦላ ወረርሽኝ‼️
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ያገረሸው ኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና #አሰከፊ ነው ሲል የአገሪቷ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቀዋል።
ከባለፉት አራት ወራት ጀምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ሲያልፍ ወደ 300 የሚሆኑ የተጠረጠሩ ህመምተኞች ተገኝተዋል።
ወረርሽኙን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች #ክትባት ተሰጥቷል።
ይሁን እንጂ የአገሪቱ ፖለቲካዊ #አለመረጋጋትና የጤና ባለሙያዎች ላይ በተለያየ ጊዜ ጥቃት በመድረሱ ለዓመታት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ተፈታትኖታል።
የጤና ጥበቃው ሚንስትር ኦሊ ኢሉንጋ በዚህ ሰዓት 319 በበሽታው የተያዙና 198 ሞት መመዝገቡን ገልፀዋል።
"ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ ያለ አሳዳጊ ለቀሩ ሕፃናትና ለተበተኑ የቤተሰብ አባላት የተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ ፤ መፅናናትን እመኛለሁ፤ በፀሎትም አስባቸዋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ እንደተናገሩት ግማሽ ያህሉ ተጎጂዎች 800 ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት የሰሜናዊ ኪቩ ግዛት ቤኒ ነዋሪዎች ናቸው።
አገሪቱ በአውሮፓውያኑ 1976 ካጋጠማት ስሙ በውል ካልታወቀው ወረርሽኝ በኋላ የአሁኑ በጣም አሰቃቂውና አስፈሪው ነው።
ኢቦላ ከሰውነት ከሚወጣ ፈሻሽ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖች አማካኝነት ይተላለፋል፤ ምልክቱም ጉንፋን መሳይ ህመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ውስጣዊና ውጫዊ መድማት ናቸው።
ምንጭ፦ OBN