TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢትዮጵያ #ወታደራዊ ሃይሏን ለማዘመን በምታደርገው ጥረት የሕዋ ሃይልን የመከላከያ ሃይሏ አንድ አካል ለማድረግ ማቀዷን ብሉምበርግ በዘገባው አስነብቧል፡፡ “ዘመናዊ ጦርነት የየብስ፣ አየር፣ ባሕር፣ ሳይበር እና ጠፈር (ሕዋን) ያካተተ በመሆኑ ይህንኑ ከግምት ያስገባ መከላከያ ሃይል #እየገነባች ነው፡፡ በቅርቡ የተከለሰው የሀገሪቱ መከላከያ ፖለሲ ባሕር ሃይልን እና ወደፊት ደሞ የሳይበር ደኅንነትን እና ጠፈር ሃይልን የሚያካትት ይሆናል” የሚል ምላሽ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ማግኘቱንም አክሎ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ብሉምበርግ(wazemaradio)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ገላን ወረዳ ‘’የገዳ መጫ” የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ዝግጅቱ #መጠናቀቁን የወረዳው  የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የፊታችን #እሁድ በሚከበረው በዓል ከኦሮሚያ ክልል 10 ዞኖች የተውጣጡ አባገዳዎችና ሌሎች እንግዶች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡ በዓሉ #ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከወረዳውና ከኢጃጂ ከተማ የተመለመሉ ፎሌዎችና ቄሮዎች ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አባያ ሀይቅ‼️

የእምቦጭ አረምን ከአባያ ሐይቅ ማስወገድ ከመጀመሩ በፊት በቂ ጥናት እንደሚያስፈልግ የጋሞ ጎፋ ዞን ደንና አከባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ #ዮሰፍ_ኩማ ለኢዜአ እንዳሉት ሐይቁ በውስጡ አዞን ጨምሮ የተለያዩ ተሳቢ እንስሳት በመያዙ አረሙን በሰው ጉልበት ለማስወገድ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

መስሪያ ቤታቸው ባለፈው ዓመት በካሄደው የዳሰሳ ጥናት ከ1 ሺህ 705 ሄክታር በላይ የሐይቁ ክፍል በእምቦጭ መያዙ ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ክረምት ለመከላከል ጥረት ቢደረግም አረሙ በሐይቁ ላይ በእጥፍ መጨመሩን አስረድተዋል፡፡

ሐይቁን ከእምቦጭ አረም የመከላከል ስራ ከዞኑ አቅም በላይ መሆኑን ያስታወቁት  አቶ ዮሱፍ “አጥኝ ቡድን እንዲቋቋም ለሚመለክታቸው የክልልና የፌዴራል ተቋማት ጥያቄ ቀርቦ  ምላሽ እየተጠበቀ ነው “ብለዋል፡፡

አረሙ በሐይቁ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ ለማስወገድ ባለ ድርሻ አካላትን ያሳተፈና በጥናት ላይ የተመሰረተ መፍትሔ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የደቡብ ክልል አካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ቀቀቦ በበኩላቸው ሀይቁን ከእምቦጭ አረም የመከላከል የንቅናቄ ስራ በአጭር ጊዜ እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡

በሀይቁ አዋሳኝ አካባቢ የተውጣጡ ዘጠኝ አባላት ያለው ቡድን በመጪው ሰኞ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ አምርቶ የጣና የእምቦጭ አረም አወጋገድ ልምድ ቀስሞ እንደሚመለስ አመልክተዋል፡፡

የአባያ ሀይቅ ረግረጋማ አካባቢዎች አስቸጋሪነት፣ አዞን ጨምሮ የተለያዩ እንስሳት አደገኛነትና በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አጋጥሞ የነበረው አለመረጋጋት በመከላከል ስራው ላይ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ከጣና እምቦጭን ለማስወገድ የተዘጋጁ ማሽኖች የአባያን ረግረጋማ ቦታዎች በምን አይነት መልኩ ለማስወገድ እንደሚቻል ልምድ የሚገኝበት መሆኑን አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

አረሙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ባለስልጣንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ጥናቶችን ማድረጉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ የአርባምንጭ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አረሙን ማስወገጃ ጀልባ ሰርቶ ባለፈው ዓመት የሙከራ ስራ መጀመሩን አውስተዋል፡፡

አቶ ሳሙኤል እንዳመለቱት ከጣና ሀይቅ የሚገኘውን ተሞክሮ በመውሰድ ውጤታማ ስራ ለማከናወን ዝግጅት ተደርጓል፤ ባለፈው ዓመት በተደረገው የመከላከል ስራ ከ36 ሄክታር በላይ አረም ማጽዳት ተችሏል፡፡

በውስጡ ከ54 በላይ ብዝሃ ህይወት የያዘውና ከስምጥ ሸለቆ ሐይቆች በስፋቱ ቀዳሚ የሆነው አባያ ሐይቅ በአረሙ ከተጠቃ አንድ አመት ቢሆንም እስከአሁን ከሙከራ ውጭ አጥጋቢ የሆነ የመከላከል ስራ አለመከናወኑ ተመልክቷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢ‼️

ቻይና በአለም #የመጀመሪያውን ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢ ይፋ አደረገች፡፡ ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢው ማሽን የሰው መልክ ያለው ሮቦት ነው፡፡

ሮቦቱ በቻይና ብሔራዊ የዜና ተቋም በሆነው ሽንዋ ዜናዎችን ሲያነብ የድምጽ አወጣጡ፣ የፊትና የእጅ እንቅስቃሴ እውነተኛ ሰውን እንደሚመስል ለመመልከት ተችሏል፡፡

‹‹ሶጎዮ›› በሚባል የቻይና የኢንተርኔት መረብ እና በሽንዋ የበለፀገው ሮቦት እረፍት ሳያደርግ በቀን ለ24 ሰዓት መረጃን የማቀበል አቅም አለው ተብሏል፡፡

ሮቦቱ በቻይንኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች መረጃዎችን ለተመልካቾች እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ጋርዲያን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በመቀለ ከተማ ከ77 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የ11 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ግንባታ ሥራ ለማከናወን #ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍትህ‼️የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ መፅሄት የመጀመሪያዋ እትም ዛሬ ገበያ ላይ ትውላለች።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ለ7 ሚሊዮን ህዝብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የ‹‹ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል›› ይመርቁታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ መሪዎች ያቀረቡት የጋራ መግለጫ። #ባህር_ዳር-ኢትዮጵያ!

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሼክ አላሙዲን ነገር⁉️

"ቢቢሲ ዛሬ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም እነ ሼክ አላሙዲንን ከሳዑዲ ልዑላውያን ጋር ደምሮ ያሳረዉ የሳዑዲ መንግስት በታሳሪዎቹ ላይ የከፋ #ድብደባ እና #ማሰቃየት እንዲሁም #ግድያ እየፈፀመ ነዉ ሲል ዘጋቢ ፊልም ሰርቷል። ከሟቾች ዉስጥ ጄኔራል አሊ አልካታኒ አንዱ ናቸዉ። ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሚባለዉ እና ፖለቲካዊ አመለካከቱ ሊበራል ነዉ ተብሎ ሲወደስ የነበረዉ በቅጽል ስሙ ኤም ቢ ኤስ የተባለዉ የሳዑዲ አልጋወራሽ በእርሱ ትዕዛዝ የታሰሩ ባለሀብቶችና ንጉሣውያን ቤተሰቦች በድብደባ ምክንያት የደረሰባቸውን ጉዳት በሌላ ሆስፒታል እንዳይታከሙ በሪትዝ ሆቴል ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል ከፍቷል። ይህ ዘገባ የተሰራዉ በቅርቡ ቱርክ በሚገኘዉ በሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ
በጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ላይ የተፈፀመዉን ግድያ ጋር ተንተርሶ ነዉ። አላሙዲን ምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? የኢትዮጵያ መንግስት ያለዉ መረጃ
ምንድነዉ? ከአላሙዲን ጋር ሲበሉ ሲጠጡ ሲያተርፉ ሲነግዱ ያዙን ልቀቁን ሲሉ የነበሩ የት አሉ ? አላሙዲ ታሰረ አልታሰረ ጉዳያቸዉ አይደለም። ነገር ግን በእርሳቸዉ እርዳታ ህክምና ላገኙ እርዳታ ለተደረገላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን ቤት ተሰርቶ ለተሰጣቸዉ ድሆች ስንል የመሐመድ ቢን ሰልማን ሰለባ እንዲሆኑ አንሻም። በሙስና የሚጠየቁ ከሆነም በፍርድ ቤት በአግባቡ መሆን አለበት ከጥላሁን ገሠሠ እስከ ካሚላት ላደረጉት በጎ ምግባር እናመሰግናለን።"

©Hailemelekot Agizew
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ‼️

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ለቀጠናው ሰላም በትብብር እንደሚሰሩ ገለጹ።

መሪዎቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ትስስር ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የሶስቱ አገራት መሪዎች ባደረጉት ውይይት ከዚህ ቀደም በአስመራ ተፈርሞ የነበረው የወዳጅነትና ትብብር ስምምነቶች አተገባበርና ውጤት ላይ ተወያይተዋል፡፡

መሪዎቹ በሶማሊያ እየመጠ ያለውን ሰላምና መረጋጋት አድንቀው ለቀጣይም ለሶማሊያ መንግስትና ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የሶስቱ አገራት መሪዎች ኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ለማንሳት ያለውን ሀሳብን እንደሚደግፉም ገልጸዋል፡፡

መሪዎቹ ለቀጣናው ሀሉን አቀፍ ትብብርና ሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ መንግስትና የኢትዮጵያ ህዝብ ላደረጉላቸው አቀባበል አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia