TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅማ ዩኒቨርሲቲ⬆️

በአሁን ሰዓት የጅማ ዩኒቨርስቲ(JiT) ተማሪዎች በምእራብ ኦሮሚያና በቤንሻንጉል ድንበር ላለው #ግጭት መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥ በሰላማዊ ሰልፍ እየጠየቁ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ⬆️

"ሰላም ፀግሽ በአሁኑ ሰዓት በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ካምፖስ በምእራብ ኦሮሚያና በቤንሻንጉል ድንበር ላለው ግጭት መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል። ለሊሳ ነኝ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከJiT...

"ሰላም ጸጊሽ በጅማ ቴክኖሎጂ ኢኒስትቲነዩት የተደረገው ሰልፍ በሰላም #ተጠናቆል ሁሉም ተማሪ ወደ ክፍል እየገባ ነዉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት አገር በቀል የሆኑ የግጭት አፈታት እሴቶችን ማጎልበት እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ። እርቅ ላይ የሚሰሩ #ሴቶችን ማፍራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ኮንፈረንስ ''ሴቶች ዘረኝነትን በመጠየፍ ለሰላማችን ግንባር ቀደም ሚናችንን እንወጣ'' በሚል መሪ
ቃል ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ(IoT)⬆️በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ምንም በማናውቀቅ ምክንያት የተወሰኑ ወጣቶች የመማሪያ ክፍላችንን ለቀን እንድንወጣ አድርገውናል በዚህም የመደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ተስተጓጉሏል ብለዋል። ስለተፈጠረው ጉዳይ የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር ለመጠየቅ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም።

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሰኝ የማቀርብ ይሆናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም #በዘላቂነት ለመከላከል የማስወገጃ ማሽኖችና የአርሶ አደርሩን ጉልበት በመጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ #ባምላክ_ተሰማ የ2018 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልሱን የዋንጫ ጨዋታ የፊታችን #አርብ በቱኒዚያው ኤስፔራንስ እና በግብፁ አል ሃህሊ መካከል ቱኒዝ ላይ የሚደረገው ከባዱን ፍልሚያ በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት ካፍ ወስኗል። አርቢተር ባምላክ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ VAR -ቪዲዮ ህግ ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አርቢትር ይሆናሉ።

ምንጭ፦ ethio kickoff
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባድ ማሳሰቢያ‼️ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የምትማሩ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በፌስቡክ የሚፃፉትን መረጃዎች #እንደወረደ ከመቀበል #ተቆጠቡ። የዚህችን ሀገር #ሰላም መሆን የማይፈልጉ አካላት #በተመቻቸ ቦታ ሆነው ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እየተሯሯጡ እንዳለ በግልፅ ማየት ይቻላል። በፌስቡክ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግስት ተገቢውን እና እጅግ በጣም ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ቻናላችን አጥብቆ ይጠይቃል።

🚫በፌስቡክ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ መልዕክቶችን አጥብቀን እንቃወማለን🚫
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፀረ ጥላቻ ንግግር‼️

መንግስት በያዝነው አመት "የጸረ-ጥላቻ ንግግር" #ወንጀል ህግ ለማውጣትና ለመተግበር ማቀዱን አዲስ የተቋቌመው የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia