TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ተቋም ከሙላት ኢንጂነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የእምቦጭ አረም #ማስወገጃ ማሽን በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው ተመርቆ ዛሬ ስራ #ጀምሯል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የዳባት ጤና ጣቢያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊዎች ዛሬ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረጉት የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ በሞዛይክ #Save_Tana እና #Save_Lalibela የሚል ጽሁፍ በመስራት እና በመዝሙር በማሰማት #አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አባያ ሀይቅን እንታደግ‼️በአባያ ሀይቅ ላይ እየደረሰ ያለውን #ጉዳት ለህዝብ ለማስገንዘብ እና ትኩረት እንዲሰጠው እየተደረገ የሚገኘው የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ 2ኛ ቀኑን ይዟል።

"የእንቦጭ አረምን ከሃይቁ እናስወግድ"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ዛሬ የተካሄዱ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ውጤቶች፦

🔹ስሑል ሽረ 0-0 ወላይታ ድቻ
🔹ፋሲል ከነማ 3-1 ሀዋሳ ከተማ
🔹ደደቢት 0-2 ኢትዮጵያ ቡና
🔹ደቡብ ፖሊስ 1-2 መከላከያ
🔹ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-1 ባህር ዳር ከተማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የመቐለ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በ15 በመቶ የሚያሳድግ የማስፋፊያ ኘሮጀክት #ተመረቀ፡፡ ለኘሮጀክቱ ግንባታ 361.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት‼️

በነቀምቴ የዘንድሮ #ኢሬቻ በዓል አከባበር በአገሪቱ የዲሞኪራሲ ሥርአት ግንባታው እያበበ ስለመምጣቱ የታየበት ነው ሲሉ አባ ገዳዎች ገለፁ።

በነቀምቴ ሀዲያ የኢሬቻ በዓል ዛሬ በድምቀት #ተከብሯል

የሌቃ አባ ገዳ አስፋው ከበደ በወቅቱ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት በአካባቢው የኢሬቻ በዓል በድብቅና በውስን ግለሰቦች ብቻ ሲከበር ቆይቷል።

“በዛሬው እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በይፋና በድምቀት በዓሉን አክብሯል” ያሉት አባ ገዳ አስፋው የዘንድሮ የበዓሉ አከባበር በአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያበበ ስለመምጣቱ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል ።

አባገዳ ምስጋኑ ለሚ በበኩላቸው “የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በአገሪቱ የፍቅርና የአንድነት ጉዞ በተቀጣጠለበትና የዴሞኪራሲ ስርአት ግንባታው ማበብ በጀመረበት ወቅት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ” ብለዋል ።

አባገዳዎች፣ ቄሮዎችና መላው ታዳሚ  በዓሉን በፍቅርና በአንድነት እንዳከበሩት የገለጹት አባገዳ ምስጋኑ ህዝቡ በበዓሉ ላይ ያሳየውን የመከባበርና የአንድነት ባህል በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎም አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል።

የዘንድሮ የኢሬቻ በዓልን ህዝቡ በብዛት ተግኝቶ በነጻነት ማክበሩ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እየተረጋገጠለት መሆኑን ያሳያል ያሉት አባገዳ ምስጉን ህዝቡ የህግ የበላይነትን በማክበር ለባህላዊ እሴቱ መጎልበት የድርሻውን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ወጣት ሙሉዓለም ታደሰ በበኩሉ “የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል ያለ ማንም ወገን ጣልቃ ገብነት በህብረተሰቡ ዘንድ በሰላም ተከብሯል ” ብሏል ።

“በዓሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናከሩበት ነበር ” ሲልም ወጣቱ  ገልጿል ።

”ዘንድሮ የኢሬቻ በዓል ከወትሮ በተለየ መልኩ  ከአዳማ፣ ከቦረናና ከሌሎች አካባቢዎች የተወከሉ ወጣቶችና የአገር ሽማግሌዎች የታደሙበት ነበር”  ያለው ደግሞ ወጣት ድንቃ ገእሳ ነው ።

በበዓሉ ክብረ በዓል ላይ ከተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች መታደማቸው ከዚህ ቀደም የነበረው የስጋትና የፀጥታ ችግር እየተፈታ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑንም ገልጿል።

በነቀምቴ “በሃዲያ” በሚባል ሥፍራ ዛሬ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ በርካታ ህዝብ መታደመበት ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል 15 ባለሞተር ዊልቸሮችን በእርዳታ አበርክተዋል፡፡ በቀዳማዊት እመቤቷ ጋባዥነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከሉን ጎብኝተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethio
ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ‼️

የኤርትራ ህዝብና መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ለተፈጠረው ሰላምና ወዳጅነት መጠናከር ከምንም በላይ ቅድሚያ እንደሚሰጡት ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የሰላም ሂደቱ ኢትዮጵያ የኢትዮ- ኤርትራን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመቀበሏ ዙሪያ የተገደበ አይደለም።

ሂደቱ በኤርትራውያን ፅናትና በኢትዮጵያ በተፈጠረው ለውጥ በመታገዝ አዲስ የወዳጅነት ምዕራፍ የተገለጠበት ነው፡፡

ይህ እርምጃ የውጭ ኃይሎች ቀጣናውን ለመቆጣጠር የነበራቸውን ምኞት ያመከነ ጭምር ነው፡፡

አዲሱ የሰላም ንቅናቄ በመላው የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ራዕይ በመሰነቅ ትርጉም ያለው መስተጋብርና ትብብር ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለዓመታት ችግርን በፅናት ተጋፍጦ በመጨረሻ ለድል በቅቷል ያሉትን ህዝባቸውን ስለቁርጠኝነቱ በእጅጉ አመስግነውታል፡፡

ምንጭ፡- የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አዕምሮ የሌለው ሕዝብ #ሥርዓት የለውም፤ ሥርዓት የሌለው ሕዝብ የደለደለ ሃይል የለውም፤ የሃይል ምንጭ ሥርዓት እንጂ የሠራዊት ብዛት አይደለም፤ ሥርዓት ከሌለው ሰፊ መንግሥት ይልቅ በሕግ የምትኖር #ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች።"

▪️ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update ጋምቤላ⬆️

ወደ ጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ ሄደው የነበሩ ስምንት ጋዜጠኞች “በመንግሥት ባለሥልጣናት ተደበደብን፣ ተዋከብን፣ ታገትን፣ ያለአግባብ በቁጥጥር ሥር ዋልን” ሲሉ #አቤቱታ አሰምተዋል። የወረዳው አስተዳደር አስተባብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ ውስጥ “ነዋይ እያፈሰስንና የልማት ሥራ ላይ ተሠማርተን ሳለን ወከባ፣ ሙስናና እንግልት ይደርስብናል” ሲሉ ቁጥራቸው በርከት ያለ ባለሃብቶች ቅሬታቸውን እየገለፁ ናቸው።

ባለሃብቶቹ አቤቱታና በጋዜጠኞች ላይ የደረሰውን ወከባና ጥቃት አስመልክቶ የወረዳው አስተደዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ የጋዜጠኞቹን ክሥ ሙሉ በሙሉ አስተባብለው ከአንድ ባለሃብት ላይ ‘ያለአግባብ ተሰጥቶ ነበር’ ያሉትን የከሰል ምርት ፍቃድ ወረዳው ከማንሣቱ በስተቀር ለባለሃብቶች ጥበቃ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ጋዜጠኞቹ ያቀረቡትን አቤቱታ ቃላቸውን ተቀብሎና ከወረዳው ባለሥልጣናትም ጋር እየተፃፃፈ መሆኑን የገለፁው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።

ፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በዚህ የጋዜጠኞቹ አቤቱታና በሌሎችም ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች አሠራርና የሕግ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቪኦኤ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ቀጠሮ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወላይታ ሶዶ⬇️

በወላይታ ሶዶ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ችግር  ንብረት ለወደመባቸውና #ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች በክልሉ መንግስት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ #ድጋፍ ተደረገ፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ተጎጂዎችም ድጋፉ ተስፋ ከመቁረጥ እንዳዳናቸው ተናግረዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ #ባታላ_ባራና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር የንብረት ጉዳት መድረሱን አስታወሰዋል፡፡

ከተጎጂዎች መካከል አብዛኞቹ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች የተሰማሩ ሲሆን በንግድ ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤቶችና በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት የማጣራትና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መሰራቱን ገልጸው በተገኘው መረጃ መሰረት ለ89 ተጎጂ ግለሰቦች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተጎጂዎቹ ራሳቸው ባቀረቡትና ከአካባቢው ህብረተሰብ በተሰበሰበ መረጃ እንዲሁም በንግድ ፈቃዳቸው ላይ ያስመዘገቡት ካፒታልና የገቢ ግብር ማህደርን መነሻ በማድረግ የማጣራት ሥራው መከናወኑንም አቶ ባታላ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት የክልሉ መንግስት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎ ከ11 ሚሊዮን 478 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤና የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ታልጎሬ ታደሰ በበኩላቸው የተሰበሰበውን መረጃ መሰርት በማድረግ እንደጉዳታቸው መጠን ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

“እስከ 10 ሺህ ብር ጉዳት ያቀረቡ 34 ተጎጂዎች ገንዛባቸው ሙሉ በሙሉ እንዲተካላቸው የተደረገ ሲሆን ቀሪዎቹ 55ቱ የጉዳታቸውን 50 በመቶ እንዲያገኙ ተደርጓል” ብለዋል፡፡

ባለሁለት ጎማ የሞተር ብስክሌት ለተቃጠለባቸው ወገኖች ምትክ እንዲገዛ መወሰኑንና በመኖሪያ ቤታቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ደግሞ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው ተጎጂዎች መካከል ወይዘሮ ምህረት መሸሻ በከተማዋ ጤና ጣቢያ ሰፈር የህጻናት አልባሳትና ኮስሞቲክስ ይነግዱ እንደነበረና በዕለቱ በድንገት በተፈጠረው ችግር መዘረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ወይዘሮ ምህረት ችግሩ ከደረሰ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ቢቆዩም ድጋፉ ሥራቸውን ዳግም ለመጀመር የሚያስችልና ተስፋ ከመቁረጥ እንደታደጋቸው ገልጸዋል፡፡

በሶዶ ከተማ መሃል ከተማ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ ኑሪ ባዲ በበኩላቸው ድንገት በተፈጠረው ችግር  በህገ-ወጦች ቢዘረፉም የመንግስት ድጋፍ ዳግም ወደስራቸው ለመመለስ እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡

ችግሩ ሰላም የማይፈልጉና በሁከት ሰበብ ለዘረፋ የተዘጋጁ ነውጠኞች ያደረጉት መሆኑን ጠቁመው የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ ነዋሪውና የከተማው ጸጥታ ኃይል ያደረገው ርብርብ የማይረሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማዋ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች መንግስትና የከተማዋ አስተዳደር ከቃል ባለፈ ተጨባጭ ድጋፍ ባለማድረጋቸው ተቸግረናል ሲሉ ያቀረቡትን ቅሬታ ኢዜአ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በጋምቤላ ከተማ የሚፈጸሙ የተለያዩ ወንጀሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የሕብረተሰቡ ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበት የከተማዋ ከንቲባ አቶ #ቺቢ_ቺቢ አሳስበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ ለክልሉ #ሰላምና #ፀጥታ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ⬇️

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የሰው ህይውት #አልፏል ተብሎ በድብቅ /በሽፋን/ በተከፈቱ በውስን ማኅበራዊ ሚዲያዎች (በTwitter እና Facebook) እየተገለፀ ያለው መረጃ የሃሰት እና ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን #እናረጋግጣልን

በመቐለ ከተማም ሆነ በዩኒቨርስቲያችን በተማሪ ላይ ምንም አይነት ጥቃት እና አደጋ ያልደረሰ መሆኑን በድጋሜ እናረጋግጣልን።

ባደረግነው ማጣረት የውሸት መረጃዎቹ እየተሰረጩ ያሉት በድብቅ /በሽፈን/ በተከፈቱ ውስን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሆን፣ በአገረችን የተጀመረውን ሰላማዊ የመማር እና ማስተማር ሂደት #ለማወክ
/ለማበላሸት/ ዓላማ ያደረገ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ ባደረግነው ዳሰሳ በትግረይ ክልል በሚገኙ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ የመማር ማስተማር ኢደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደቀጠለ ነው።

እነዚህን የውሸት መረጃዎች በጋራ በመከላከል እና ትክክለኛ መረጃዎችን ብቻ በመስጠት እና በማሰረጨት ሃላፊነታችንን እንወጣ።

ይህን መልዕክት Share በማድረግ ለሌሎች እናስተላልፍ!
፨፨፨
The safety of our students and providing quality academic service are utmost priority of our university. We Really Care!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 25/2011
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። ከዚህ ቀደም አቶ ፍፁም አረጋ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ሀላፊነታቸው ሊነሱ እንደሆነ መረጃ አቅርበን ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia