TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
5,000 ብር ድጋፍ! የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆነ ስሙን መግለፅ የማያስፈልግ ወዳጃችን ለህፃን በናያስ ህክምና ወጪ የሚሆን የ5,000 ብር ድጋፍ አድርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በርሊን⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ በበርሊን ከታደሙበት ስብሰባ አፍታ ወስደው በበርሊን ከተማ ብራንደርን ቡርግ አደባባይ የተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸውን በድንገት አግኝተዋቸዋል፡፡ የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ዶች ቬሌ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንገት ከጠባቂዎቻቸው እና ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ወደ አደባባይ ብቅ ሲሉ የተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን በጩኸት ድጋፋቸውን ገልፀውላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በርሊን⬆️

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ ጀርመን የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር ተገናኝተዋል።

ዛሬ ረፋድ የፈረንሳይ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በርሊን የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመራሂተ መንግስት አንጌላ መርክል ጋር ከሚያደርጉት የሁለትዮሽ ውይይት በተጨማሪ የቡድን 20 አባል አገራት የአፍሪካን ልማት ለማገዝ በመሰረቱት “ኮምፓክት አፍሪካ” በሚሰኘው ጉባኤ ላይ የሚካፈሉ ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አንዋር መስጊድ⬇️

አንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት  ቦንብ በመወርወር የሽብር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሳሽ #አህመድ_ሙስጠፋ_አብዶሽ የራሳቸውን ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በማሰብ፣ በመንግስት ላይ ተፅእኖ ለማሳደርና ህብረተሰቡን ለማሸበር እንዲሁም በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተረጋገጠውን የሃይማኖት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸን አስተሳሰብና አስተምህሮት እምነት ውጪ ሌላ አስተምህሮት መኖር የለበትም የሚል ዓላማ በመከተል ቀኑና ወሩ ባልታወቀ

በ2007 ዓመተ ምህረት ተከሻሽ በሚጠቀምበት የሞባይል ስልክ ቁጥር በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የተዋወቀውንና ያልተያዘውን ግብረ-አበሩን ሼክ አሊ ሀይደር ጋር በመነጋገር ሀበሽ እስላም አይደለም ይህን ተግባር ካሳካህልኝ 100 ሺህ  አሰጥሃለሁ በማለት ተከሳሽ ከሚኖርበት ሶማሌ ክልል ልዩ ቦታው ኤረር ጎታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በመነሳት አዲስ አበባ ሂዶ በአንዋር መስጊድ ላይ ቦንብ እንዲያፈነዳ በግብረ አበሩ በኩል ተልዕኮ እንደተሰጠው የወንጀል ዝርዝሩ ያስረዳል፡፡

ተከሳሽም ተልዕኮውን ለመፈጸም አዲስ አበባ በመግባት የአንዋር መስጊድን ሁኔታ አጥንቶ ለግብረ አበሩ ማህበራዊ ድረ-ገጽ መልዕክት የላከለት ሲሆን ፥ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት በአንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት በመስጊዱ ውስጥ ተሰብስበው በዝየራ ላይ በነበሩት ሰዎች ላይ ቦንቡን በመወርወር በ24 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት በማድረሱ በሽብርተኝነት ወንጀል ድርጊት በመፈጸም ክስ ተመስርቶበት ቆይቷል።

የፌደራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ 30 ሰዎችን የምስክርነት ቃልና የተጎጂዎችን የህክምና ማስረጃ እንዲሁም የተከሳሽን የእምነት ቃል ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት የ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንደበየነበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦቦ ለማ መገርሳ⬆️

መንግስት ከዚህ በኋላ የህዝቡን ደህንነትና ህገመንግስቱን የሚጥሉ አካላትን እንደማይታገስ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ አስታወቁ።

ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ መገርሳ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሉት።

በመግለጫቸውም ሰሞኑን በምእራብ ኦሮሚያ ዞኖችና በቄለም ወለጋ በኦነግ ስም በመታጠቅ ህዝቡን ለችግር እየዳረገ ያለ አካል በአፋጣኝ ከዚህ ተግባር #እንዲታቀብ አሳስበዋል።

መንግስት እስካሁን እንዲህ አይነቱን ተግባር በትእግስት ሲመለከት ነበር ያሉት አቶ ለማ፥ ከዚህ በኋላ ግን መንግስት የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ እና ህገ መንግስቱን ለማስከበር እንደሚሰራ ለኦቢኤን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ እና የሀገር ሽማግሌዎች በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ እና እጃቸው ያለበት ሰዎች ይህን ተግባራቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ በማቅረብ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ በማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ እየተስተዋለ ያለውን የፀጥታ ችግር በአፋጣኝ ለመፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የሁለቱ ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች ተወያይተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ተገናኝተው ነው የተወያዩት።

በውይይታቸውም በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የዜጎች መፈናቀል #ለማስቆም ተስማምተዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል የተደረሰው ስምምነትም በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲሆን ከስምምነት መድረሳቸውም ታውቋል።

ምንጭ፦ OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባን ከመቀለ የሚያገናኘው ዋና መንገድ በአማራና በትግራይ ክልሎች ድንበር ላይ #በመዘጋቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ ተገቷል።

ምንጭ፦ ETHIOPIA LIVE UPDATE
@tsegabwolde @tikvahethiopia