TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራባዊ ኦሮሚያ ግጭት መታየቱ ተሰማ‼️

በምዕራባዊ ኦሮሚያ ክልል በሚገኙት አከባቢዎች የኦሮሞ ነፃ አዉጭ ግንባር /ኦነግ/ ስራዊት ናቸዉ በተባሉና በኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት መካከል ላለፉት ቀናቶች ግጭት መታየቱን የአከባቢዉ የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬሌ ገልጹ።

ግጭቱን ተከትሎ የክልሉ ፕሬስዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ በትላንትናዉ እለት እንደተናገሩት ሁኔታዉ በጣም እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል።

ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ዘመናዊ መሳርያ ከታጠቀዉ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ ስህተት መሆኑን እና ትክክለኛ የትግል ስልት አለመሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ተችተዋል።

አከባቢዉ ላይ ባለዉ የፀጥታ አለመረጋጋት ምክንያት የሰዎች እንቅስቃሴን እና የንግድ ሂደቱን ማገቱንም ገልፀዋል። ጫካ የገቡት እነዚህ ወጣቶች ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ ከሽማግሌዎች ጋር በመሆን እንደሚሞክሩ እንዲሁም ማህበረሰቡ በጠረጴዛ ዙርያ መወያያት እንደለበት አቶ ለማ አሳስበዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ለተከሰተዉና ለሚከሰተዉ ችግር መፍትሄ መስጠት እንደሚያስቸግር ገልፀዋል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች «መንግስት የኦነግ ስራዊት ለማጥቃት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ» በመቃወም ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አልሸባብ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በለድወይን ከተማ አቅራቢያ #አጠቃሁ ብሏል። አንድ ከጠ/ሚሩ ጋር ወደ ፓሪስ ያመሩ እና የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በስልክ ያናገራቸው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን ስለተባለው ጥቃት #እንደማያውቁ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የሀላባ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ወ/ሮ #ሂክማ_ከይረዲን መሀመድን በዛሬው እለት የልዩ ወረዳ ዋና አስተዳደር በማድረግ ሾሟል።

እንዲሁም

የሀላባ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ #ገመዳ ኢ/መሀመድ አብደለ በዛሬው እለት የልዩ ወረዳ ምክትል አስተዳደርና የልዩ ወረዳው መ/ማ/ኢ/ ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሾሟል።

ምንጭ፦ ደኢህዴን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዩኒቨርሲቲ⬆️

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች በከተማው ነዋሪዎች አቀባበል ተደረገላቸው።

የአምቦ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ከተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች አዲስ ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ 5 ሺ ለሚሆኑ ተማሪዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ታደሰ_ቀነዓ፣ አባገዳዎች፣ የእምነት አባቶችና የአምቦ ከተማ ቄሮዎች ለእነዚህ ተማሪዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው አዲስ ከተመደቡት ተማሪዎች ውስጥ አስተያየት የሰጡት ተማሪዎች በአምቦ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተደረገላቸው አቀባበል እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሚላት⬆️

"....ካሚላት ናት። "ስለወደድኳት ረጨኋት" ያለ #አሲድ ደፊ ወንጀለኛ የልጅነት ገጿን፣ ቀለሟን፣ ውበቷን ገፏታል።የህዝብ ርብርብ ሆኖ እንጂ ህይወቷ ንም ሊነጥቅ የሚችል ጥቃት ነበር። ዛሬ በዚህ ምስል እንደሚታየው በሀገሯ መሪ እቅፍ ውስጥ ፈገግታዋ ብቻ ነው የሚታየኝ። በጥንካሬዋ የተቀዳጀችው ውበት ነው ያበራብኝ። ዓብይ በደረሱበት አሻራና ድካ ይተዋሉ። ወጣት ኢትዮጵያውያን በብሩህ መንፈስ ይከተሉታል። መልካም ነገር ፅናት ይጠይቃል፤ ዳርቻ የሌለው ትዕግስት ግድ ይላል። ዐብይ ካሚላን አቋጥረው በማቀፍ ሁላችንንም #አቅፈውናል። እናመሰግናለን። መልካም ጉብኝት ይሁንልዎ! ካሚላም መልዕክታችን ይድረስሽ፦ከዚህ ሁሉ በኋላ ለህይወት ያለሽ ጉጉትና ህይወትሽን እየመራሽበት ያለው ውበት በርካታ ብስጩ ተስፋቆራጭ፣ ተጨናቂና ተካዦችን አንገታቸውን ቀና እንደዲያደርጉና ለህይወታቸው ትርጉም እንዲፈልጉ ያተጋል።"

©ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ በ1999 ዓ.ም ፊቷ ላይ ከፍተኛ የአሲድ ጉዳት ደርሶባት የነበረችውን #ካሚላት_መህዲን አግኝተው አነጋግረዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ተወልደ‼️

"አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀላፊነት ተነስተዋል የሚለውን ነገር ለማጣራት የአየር መንገዱ Chief Operating Officer (COO) የሆኑት አቶ መስፍን ጣሰው ጋር አሁን ደውዬ ነበር። በመልሳቸውም: "እኔ የማውቀው ነገር የለም። #የሀሰት ዜና ይመስለኛል። ቀኑ ሙሉውን ከአቶ ተወልደ ጋር ነው የዋልኩት።" ሌላ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ጋር ጥይቄም "He is in duty" የሚል መልእክት ደርሶኛል። የቦርድ ስብሰባ ግን በዚህ ሰአት እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እስካሁን ያለው ነገር ይህን ይመስላል።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፓሪስ አሁን‼️

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አሕመድን በፓሪስ ኢሊዜ ቤተመንግሥት በወታደራዊ ማርሽ #ከፍተኛ አቀባበል አደረጉላቸዉ። ሁለቱ መሪዎች በአሁኑ ሰዓት በሁለቱ ሃገራት የወዳጅነት ግንኙነት ላይ እየተወያዩ እንደሆን ቦታዉ ላይ የምትገኘዉ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ወኪሏ ሃይማኖት ጥሩነህ ገልፃልናለች።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia