TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ:- ከክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ከክቡር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን ከጎርጎራ ጀምሮ ደንቢያ እና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎችን እና በሊቦ ከምከም ወረዳ አግት ቅርኛ ቀበሌ ላይ በመገኝት በጣና ሀይቅ ዙሪያ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን #የእንቦጭ አረም ወረራ ጎብኝተዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ⬆️በሌሎች ክልሎች የተመደቡ የትግራይ ክልል ተማሪዎች ድህንነት #ያሳስበናል በሚል ሮማናት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ሰልፍ ተደርጎ ነበር።

©Bit(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የርብ ግድብ ተመረቀ‼️

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ በዛሬው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን የርብ ግድብ #መርቀው ከፍተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸው ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዋና አቃቤ ህግ አቶ #ብርሃኑ_ፀጋዬ፣ የቀድሞውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ #ታዬ_ደንደአን
በመተካት የተሾሙትን አቶ #ዝናቡ_ቲኑን እንኳን ወደ ተቋማችን በደህና መጡ በሚል የመልካም ምኞት መግለጫ መቀበላቸውን ከትዊተር ገፃቸው ላይ አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የርብ ግድብ ምረቃ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ በርብ ያደረጉት ንግግር፦

• ዛሬ ጠዋት ከጣና ጀምረን ደንቢያ አካባቢና ሊቦከምከም አካባቢ እምቦጭ የሚባል ብቻየን ካልኖርኩ የሚል ጠላት ጎብኝተናል፡፡ የገባኝ ሚስጥር እንደ ጣልያን ርብ ላይ እንደሚሸነፍ ተረድቻለሁ፡፡

• ጠላቶቻችን በዚህች ቅድስት ሀገር ላይ ጦርነት ቢያውጁም አሸንፈው አያውቁም፡፡ እምቦጭንም እናሸንፈዋለን፡፡

• ኢትዮጰያ የአፍሪካ ውኃ ማማ ካስባሏት አካባቢዎች አንዱ ይህ አካባቢ ነው፡፡ ነገር ግን ውኃ፣ ጉልበትና መሬት እያለ አቀናጅተን አልተጠቀምንም፡፡

• እርሻን እንደ ቅርስ ባለማዘመን ከሚተቹ ሀገራት አንዷ ነች፡፡ እያሻሻልን መሄድ ሲገባን ዛሬም አርሶ አደሮች ብዙ ጉልበት እያፈሰሱ ትንሽ ምርት የሚያገኙ ናቸው፡፡

• ይህንን የእልህ የሆነ ዝናብ፣ ፀሐይ፣ እምቦጭ በጋራ እንደምናሸንፍ እንድንችል በጋራ እንድንቆም ይገባል፡፡ አሁን ለኢትዮጵያ የሚያዋጣው መደመር ብቻ ነው፡፡ እንደ እምቦጭ ሁሉም ለእኔ ከሆነ ተያይዞ መጥፋት ነው፡፡

• በግድቡ አገዳ፣ ፍራፍሬ ፣ አትክልት አሳ፣ እያመረቱ መጠቀም ይገባል፡፡ይህንን ግድብ እውን ለማድረግ ሕይወት ጭምር የከፈላችሁ ናችሁና በአግባቡ መጠቀም ይችላል፡፡ የጎንደርን ውብ አካባቢ ቱሪስቶች እንዲጎበኙ ለማድረግ ሁላችንም እንሥራ፡፡

• ስትፈጠርም የዳቦ ቅርጫት የሆነች ኢትዮጵያን ሀብቷን አቀናጅተን እንሥራ፡፡መስኖ ከሀገራዊ ኢኮኖሚው አራት በመቶ ብቻ ነው የሸፈነው፤ ስለዚህ ይህንን ማሻሻል አለብን፡፡ አሁን ተቋቋመው የመስኖ ኮሚሽን ግድብ ጀምረው የሚጨርሱ ተቋራጮችም ስላሉ ድርሻውን ይወጣል፡፡

• የአካባቢው አርሶ አደሮች የሚያስፈልጋችሁን የቴክኖሎጂና የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

• በእምቦጭ ላይ በምናደርገው ዘመቻ በድጋሜ እንገናኛለን፤ እመቦጭ መሆን አያስፈልግም፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia