TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
OBN⬆️የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ዲቪዥን ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር መከሩ:: የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ዲቪዥን ዳሬክተር #ንጉሴ_መንገሻ የተመራው ቡድን በኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር #መሐመድ_አደሞና ሌሎች ኃላፊዎች ጋር በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡ ሁለቱ የሚዲያ ተቋማት የጋዜጠኝነት የሙያ ልህቀትን ከፍ ማድረግ በሚቻልበትና በጋራ ሊሰሩ በሚቻሉ ጉዳዮች ላይ ተመካክረዋል፡፡

ምንጭ፦ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር #አንቶንዮ_ቪቶሪኖ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ስራን አድንቀው፣ ድርጅቱ በኢትዮጵያ እየሰራ ያለውን ስራ ይበልጥ እንዲያጠናክር መጠየቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከጥቅምት 30 ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ አፍሪካውያን ወዲያው ቪዛ #መስጠት እንደሚጀመር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ #ፍጹም_አረጋ በቲዊተር ገጻቸው አስነብበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁላችሁም የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በቦታው በመገኘት ከእህታችን ከሀያት ጎን እንድትቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
እንዳትቀሩ‼️ዛሬ ቅዳሜ ከ6 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት በቦሌ አከባቢ ለሃያት ኑርሁሴን ሙሉ ገቢ የሚሆን የበርገር ሽያጭ ይደርጋል ሰለዚህ እርስዎም ተጋብዘዋል።

አደራሽ ፦ ቦሌ ኤድናሞል ጋር እና
ቦሌ መድኃኒዓለም ሞል ጋር
@tsegbwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ‼️

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢፌዲሪ ህገመንግስት መሰረት በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ፤ የዜጎች #ሰላምና ደህንነት #እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2011ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት #በሰለማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከወትሮ በተለየ በሁሉም ሀገሪቱ #ዩንቨርሲቲዎች እና #ኮሌጆች በተለያዩ አከባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያካናወነ ሲሆን የመማርና ማስተማር ሂደትም እንዳይስተጓጎል ከሌሎች ጥምር ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተመደባችሁ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋም በመሄድ #ያለምንም የፀጥታ #ስጋት ትምህርታችሁን መማር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ደህንነታችሁ በተመለከተ በሁሉም ዩንቨርሲቲዎችና አካባቢዎች ከወትሮ በተለየ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያደረግን እንደምንገኝ በድጋሜ እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ቦታ ሲሆዱም ሆነ ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ስጋት እንዳይኖር አስቀድመን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት በማድረግ እየሰራን እንደምንገኝና ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንገልፃለን፡፡

©የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ⬆️በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ፣ የክልሉን መንግስት #በመቃወም አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ የክልሉ ልዩ ሀይል በወሰደው እርምጃ ቢያንስ አምስት ሰዎች እንደተጎዱ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በዛሬው ዕለት በሰመራ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች እንዲበተን መደረጉን በስፍራው ከነበሩ ሰዎች ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ⬆️ለሃዩ በርገር Day በሚል የበርገር ሽያጭ እየተከናወነ ይገኛል። ፎቶው ቦሌ ኤድናሞል Chicken hut በአሁን ሰአት ያለውን ድባብ የሚያሳይ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia