TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦብነግ⬆️

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ወደ አገር ቤት ተመልሶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግስት ጋር መስማማቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ገለፁ፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ “በዛሬው እለት በኤርትራ አስመራ በነበረን አገራዊ ተልኮ ለረጅም አመታት የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ከነበረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ጋር ባደረግነው ድርድር ወደ አገር ቤት ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ከስምምነት ደርሰናል” ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእናተው ጥያቄ መሰረት አንዳችን ለአንዳችን የምንቆምበት የመልካም እና የድጋፍ ተግባራት ላይ የምንሳተፍበት መድረክ ተመቻችቷል።

TIKVAH-AID‼️
ይህን ይጫኑት @tikvahaid

መልካምነት መልሶ ይከፍለናል!
#update አቶ ተስፋዬ ኡርጌ⬇️

ፍርድ ቤቱ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ በሆኑት አቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ የ15 ቀናት #የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ 1ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ውሎው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ በመስጠት ለጥቅምት 27 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መርማሪ ፖሊስም የምርመራ ስራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ገልጿል።

አቶ ተስፋዬ በአዲስ አባባ በሰኔ 16ቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን #የቦምብ ጥቃት በማሰተባበር፣ በመምራትና በቦምብ ፍንዳታ የሚሳተፉ አካላትን በመመልመል ነው የተጠረጠሩት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላልይበላ⬆️የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለላልይበላ ዉቅር-አብያተ ክርስቲያናት ጥገና የሚዉል 30 ሚሊዮን ብር #መመደቡ ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1000 አባላት በ1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ‼️

በእናተው ጥያቄ መሰረት አንዳችን ለአንዳችን የምንቆምበት የመልካም እና የድጋፍ ተግባራት ላይ የምንሳተፍበት መድረክ ተመቻችቷል።

TIKVAH-AID‼️
ይህን ይጫኑት @tikvahaid

መልካምነት መልሶ ይከፍለናል!
#uptade በሐረር ከተማ ውሃ ከተቋረጠ ከ2 ወር በላይ እነደሆነው ቢቢሲ #ያነጋገራቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሀረር⁉️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደብረ ብርሃን መንገድ ላይ ጫጫ የሚባል ቦታ የመኪና አደጋ መድረሱን ከስፍራው መረጃ ደርሶኛል። በአደጋው ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃዎችን አጣርቼ አሳውቃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ራያ አላማጣ⬇️


በራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ አንስተው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መሀከል ሶስቱ #መሞታቸው ተሰማ፡፡

የራያ አላማጣ የከተማው አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ሀብቶም ወረታ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 እንደተናገሩት፣ የማንነት ጥያቄን መሰረት በማድረግ በተነሳው ተቃውሞ በፀጥታ ሀይሉና በነዋሪው መሀል #ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

ትናንትና እሁድ የማንነት ጥያቄ እና የመልካም አስተዳደር ጎድሏል ያሉ የራያ አላማጣ ወጣቶች በከተማዋ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ለወራት የዘለቀው የራያ የማንነት ጥያቄ ጉዳይን በቅጡ ለመፍታት ለምን ከሚመለከታቸው ጋር አልተወያያችሁምና አልፈታችሁም ያልናቸው የከተማው አስተዳዳሪ ጥያቄው የጥቂቶች ነው ብለዋል፡፡

የራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ ላለፉት ወራት በሰፊው ከመደመጥ አንስቶ `የራያን ህዝብ እናድን” የሚሉ ዘመቻዎችና ሰልፈኞች በርክተዋል፡፡

በትናንትናው እለት በራያ አላማጣ ከተማ ለሰልፍ የወጡ ወጣቶች የሞቱት ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር በተፈጠረው ግጭት መሆኑንም አቶ ሀብቶም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከህግ ውጪ በሆነ መንገድ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን መጋዘኔን ሰብረው ገብተዋል ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የእርምት #እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከማዕከሉ የተፃፈው ደብዳቤ ደርሶኛል መፍትሄ እንዲሰጥበትም ለሚመለከተው ክፍል ደብዳቤውን መርቼያለሁ ሲል ለሸገር ተናግሯል፡፡

ባለፈው ሐሙስ ከሰዓት በኋላ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ወደ ባህል ማዕከሉ በመግባት አንድ መጋዘን ሰብረው በመግባት በውስጡ ያለውን 6 ሚሊዮን ብር የተገመተ የግንባታ ቁሳቁስ ወደ ውጭ አውጥተው ሜዳ ላይ ጥለውታል ይላል ከባህል ማዕከሉ የተፃፈ ደብዳቤ፡፡

ጉዳዩ በተከሰተ ማግስት የባህል ማዕከሉ ለፌዴራል ፖሊሰ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ እንዳስረዳው የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ወደ ማዕከሉ የገቡት ከባህል ሚኒስቴር እውቅና ውጪ በሆነ መንገድ ነው፡፡

6 ሚሊዮን ብር ይገመታል የተባለውና ከመጋዘኑ ያወጡት የግንባታ እቃ ፌሮ፣ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ቆርቆሮና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

አባላቱ ወደ ሰበሩት መጋዘን ገብተው ካለፈው ሐሙስ ጀምረው እየኖሩበት ሲሆን ወደ ውጭ አውጥተው የጣሉት ንብረትም አደጋ ላይ መሆኑን እወቁት ይላል ማዕከሉ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፃፈው ደብዳቤ፡፡

በመሆኑም ኮሚሽኑ የተፈጠረውን ችግር በመረዳት በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስድና ሁኔታው ወደ ቀደመው ቦታ እንዲመለስ ባህል ማዕከሉ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡

እስካሁን ግን የተቀየረ ነገር እንደሌለ ከባህል ማዕከሉ ሰራተኞች ተሰምቷል፡፡
ስለ ጉዳዩ ምላሽ አንዲሰጠን የጠየቅነው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ደብዳቤ እንደደረሰውና ለሚመለከተው ክፍል መምራቱን ለሸገር 102.1 ተናግሯል፡፡

6 ኪሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ማዕከል 5 ሺ ሄክታል ቦታ ላይ ያረፈና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እውቅና ተሰጥቶት የተቋቋመ መስሪያ ቤት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል ምክር ቤት⬇️

ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ የ9 የካቢኔ እና የ3 የዞን ዋና አስተዳደር #ሹመት በማደቅ ተጠናቀቀ᎓᎓

ምክር ቤቱ በ3 ቀናት ቆይታው 16 አጀንዳዎችን የተመለከተ ሲሆን የክልሉ መንግስት የስራ አስፈፃሚ የ2011 ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድን ጨምሮ የተለያዩ የሴክተር መስሪያ ቤቶችን ዕቅዶች አዋጆችና ደንቦችን በመወያየት #አፅድቋል᎓᎓

ምከር ቤቱ በዕድሜ ምክንያት በክብር ለተሰናበቱ የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ምትክ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እንዲሁም ወይዘሮ የምስራች ብርሃኑን ምክትል አፈ ጉባኤ በማድረገ ሾሟል᎓᎓

ከዚህ በተጨማሪ በምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል አቅራቢነት 9 የካቢኔ አባላትና 3 የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች ተሹመዋል᎓᎓

ሹመቱን ከወትሮው ለየት የሚያደርገው ለካቢኔ አባላት 50 በመቶ የሴቶችን ተሳተፎ ለማሳደግ በተቀመጠው መሰረት ከ9 ከተሾሙ አዳዲስ የካብኔ አባላት 6ቱ ሴቶች ናቸው᎓᎓

በዚህም መሠረት፦

1ኛ/ዶክተር አብርሃም ተከስተ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ንግድ፣ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ

2ኛ/አቶ ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሄር የውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ

3ኛ/ወይዘሮ ሊያ ካሳ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ

4ኛ/ወይዘሮ ገነት አረፈ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

5ኛ/ ወይዘሮ አሰፉ ሊላይ የገቢዎችና ልማት ባለስልጣን ኃላፊ

6ኛ/አቶ ተኪኤ ምትኩ የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

7ኛ ወይዘሮ አልማዝ ገብረጻድቅ የኮንስትራክሽን፣መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

8ኛ/ ወይዘሮ ብርክቲ ገብረመድህን የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ እና

9ኛ/ ዶክተር ጸጋብርሃነ ተክሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል።

እንዲሁም አቶ ኢያሱ ተስፋይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፣አቶ ረዳኢ ሐለፎም የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና አቶ ርስኩ አለማው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ⬇️

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ምክንያታዊ ያልሆኑ ጥያቄዎችን ወደ ብሄር #ግጭት ከሚለውጡ አካላት ራሳቸውን ሊጠብቁ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ #አሳሰበ

ዩኒቨርሲቲዎች የልህቀት ብቻ ሳይሆን የባህል ልውውጥ ትልቅ መድረኮች መሆናቸው እሙን ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጥላቻ እና ልዩነትን የሚዘሩ አካላት እነዚህን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ኢላማ አድርገው ሁከት እና ግርግር እንዲነሳ #ሲጥሩ ተስተውለዋል።

ተቋማቱን ከምርምር ማዕከልነት ወደ ግጭት መናኸሪያነት ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ምክንያታዊ ያልሆኑና የግለሰብ ጉዳዮችን አግዝፈው ወደ ብሄር እና ሀይማኖት ተኮር ግጭት ሲቀይሩም ታይቷል።

fbc ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችም፥ አሁን ላይ የጥፋት ተልዕኮ ካነገቡ ሀይሎች ራሳችን ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል።

መከባበር እና አብሮነትን ማስቀጠል ቀዳሚው ተግባር መሆን እንዳለበትም ያነሳሉ።

ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው ጥያቄ እና ሀሳባቸውን በዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለፅ እንዳለባቸው ጠቅሰው፥ ለሚነሱ ጥያቄዎችም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርበት ለሀገር እና ወገን የሚበጁ ጉዳዮች የሚመከሩበት መድረክ ሊመቻች ይገባል ባይ ናቸው፤ የትምህርት ዘመኑ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ በመጥቀስ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት፣ ትብብር እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ደመቀ አጭሶ በበኩላቸው፥ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ምክንያታዊ በሆነ የሀሳብ ሙግት እንደሚያምኑ ይናገራሉ።

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል እና ተማሪዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በሚፈቱበት ሁኔታ ተከታታይ #ምክክሮችን ያደርጋልም ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በነገው እለት በመማር ማስተማር ሂደቱ እና የሀገሪቱን ሰላም አስጠብቆ ማስጠቀል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለአዳዲስ ተማሪዎቹ ገለጻ ያደርጋል።

በዩኒቨርሲቲው ተምረው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎችም የማነቃቂያ መልዕክት ያስተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፥ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርቲስ ለገሰ አብዲ‼️
#update በአፋን ኦሮሞ የመሲንቆ ዘፈኖች የሚታወቁት አርቲስት #ለገሰ_አብዲ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

አርቲስት ለገሰ አብዲ በሰላሌ ያያ ቀጨማ የሚባል አከባቢ ነው የተወለዱት፡፡አርቲስቱ በህይወት ዘመናቸው በሀገር ፍቅር ቲያትር፣ ብሔራዊ ቲያትር፣ የፖሊስ ኦርኬስትራና ሌሎች ባንዶች ውስጥ ሰርተዋል፡፡

አርቲስት ለገሰ አብዲ የአራት ወንዶችና የሶስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
3000 አባላት 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ‼️

በእናተው ጥያቄ መሰረት አንዳችን ለአንዳችን የምንቆምበት የመልካም እና የድጋፍ ተግባራት ላይ የምንሳተፍበት መድረክ ተመቻችቷል።

TIKVAH-AID‼️
ይህን ይጫኑት @tikvahaid

መልካምነት መልሶ ይከፍለናል!