#update የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 13 መደበኛ ጉባዔውን በነገው ዕለት ይጀምራል። የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ በ12ኛ መደበኛ ጉባዔ የነበረውን ቃለ ጉባዔ ያፅድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም የክልሉን የፈፃሚ እቅድ እንደሚመለከት ነው የተገለፀው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
"ይህች ሃገር የቆመችው በጠመንጃ ብዛት ሳይሆን በህዝቦቿ #ፀሎት ነው፤ በእስልምና እና በክርስትና ሃይማኖት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በየቤተ እምነታችሁ ለሃገራችሁ ፀሎት አድርጉ፤ ልጆቻችሁንም ስለ ሃገር ፍቅር ስለ አንድነት አስተምሩ!"
ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የልዩ ስልጠና ጥሪ⬆️እባክዎ ለምዝገባና እና ለተጨማሪ መረጃ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አድራሻዎች ይጠቀሙ፡፡
ስልክ - +251 115 589045
ሞባይል - +251903182525
ኢሜይል - [email protected] & [email protected]
በተጨማሪም በማኅበራዊ ገጾቻችን ሊያገኙን ይችላሉ፡፡
ፌስቡክ: www.facebook.com/EFFSAA
ትዊተር: @EFFSAATweets
ሊንክድኢን: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-freight-forwarders-and-shipping-agents-association-effsaa/
ቴሌግራም: https://t.iss.one/EFFSAAChannel

#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ለፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች #ሹመት ሰጥተወዋል፡፡
በዚሁ መሰረት:-
1. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም- በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
2. አቶ መለስ ዓለሙ- በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ም/ዋና አስተባባሪ
3. አቶ ተመስገን ጥሩነህ- የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
4. አቶ ደሴ ዳልኬ- በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርናና የመስኖ አማካሪ በመሆን ከጥቅምት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተሾሙ ሲሆን፣ የተሰጠው ሹመት የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት ያስገባ ነው፡፡
ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

#update ሞቃድሾ⬆️
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ወርቅነህ_ገበየሁ እና የኤርትራ አቻቸው #ኦስማን_ሳላህ ዛሬ ለጉብኝት ሞቃድሾ ገብተዋል። ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቆይታቸው ከሶማሊያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ፦ fbc

#update የዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ⬇️
የትምህርት ሚንስቴር የዩኒቨርስቲዎች የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች የቅበላ ጊዜን ይፋ ማድረጉ ተከትሎ ዩኒቨርስቲዎቹ በወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን መቀበል ይጀምራሉ።
ተማሪዎቻቸውን ያለምንም የትራንስፖርት ችግር ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው እንዲገቡ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ፣ አምቦ እና የጅማ ዩንቨርስቲዎች ለfbc አስታውቀዋል።
ተማሪዎችን ከመናሃርያ ተቀብለው ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ለማጓጓዝ መዘጋጀታቸውን ይፋ ያደረጉት።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለfbc እንዳስታወቀው፥ ጥቅምት 8 እና 10 ነባር ተማሪዎቹን እንዲሁም ጥቅምት 11 እና 12 ደግሞ አዲስ ተማሪዎቹን ይቀበላል።
ለዚህም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ተማሪዎች በሚያርፉባቸው የተለያዩ መናሃሪያዎች በመገኘት ወደ ዩኒቨርስቲው የሚያጓጉዙ አውቶብሶችን ማዘጋጀቱን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና አስታውቀዋል።
አምቦ ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ጥቅምት 12 እና 13 ነባር ተማሪዎችን እንዲሁም ጥቅምት 19 እና 20 ደግሞ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቷል።
ዩኒቨርስቲው አውቶብሶቹን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ከሰሜን፣ ደቡብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ተማሪዎቹን ባዘጋጃጀው አውቶብሶች ወደ ወናው ካንፓስ እና ሌሎች ተጨማሪ ሶስት ካምፓሶቹ ለማጓጓዝ መዘጋጀቱን የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኝነት አስተባባሪ አቶ ሙለታ ሩጉማ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኝነት ሀላፊ ዶክተር አሸናፊ በላይ አስታውቀዋል።
ዶክተር አሸናፊ፥ ከአዲስ አበባ ወደ ዩንቨርስቲው የሚወስዱ የዩኒቨርስቲው ተሽከርካሪዎች እንደሚመደቡ ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው ጥቅምት 12 እና 13 ነባሮችን ጥቅምት 19 እና 20 ደግሞ አዲስ ተማሪዎችን ይቀበላል።
የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የአጭር ርቀት ጉዞ ብቻ የተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች በጊዜያዊነት የረጀም ርቀት እንዲፈቀድላቸው ከሚመከተው ተቋም ጋር እየተሰራ መሆኑን በትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሚንሰትር ደኤታ ዶክተር ሳሙኤል አስታውቀዋል።
በባለስልጣኑ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ ተስፋየ በላቸው፥ የተማሪዎችና የሸኝዎችን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ ቀደም የነበረው የኪሎ ሜትር ገደብ መነሳቱን ገልፀዋል።
ይህም የዩኒቨርስቲዎች ጥሪ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ የሚቆይ ሲሆን፥ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተጀመረ አዲስ አሰራር መሆኑን ነው አቶ ተስፋዬ የተናገሩት።
አሰራሩ በሶስቱም የርቀት ገደቦች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፥ በዚህም ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የአገልግሎቱ ፈላጊዎች ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ ካሉበት ክልል በቀጥታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ወደ ሚገኝበት ክልል አንዲጓዙ ያስችላል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

#update የመን⬇️
በየመን ከሶስት ዓመታት በፊት የእርስ በርስ #ግጭት ተከስቷል፡፡ እንደ ሳኡዲ አረቢያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ያሉ ሀገራት በጦርነቱ እጃቸዉን አስገብተዉ ንጹሀን ዜጎች ላይ የአየር እና የምድር ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል በሚል ከሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ክስ ይነሳባቸዋል፡፡
የመን ወደ ቀድሞ መረጋጋቷ መመለስ ባለመቻሏ የግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ተስተጓጉለዋል፡፡ ከዉጭ ሀገራት የሚላኩ የምግብ እና የሰብዓዊ አርዳታዎችን በጦርነቱ ምክንያት ለየመናዊያን በበቂ ሁኔታ ማድረስ አልተቻለም፡፡
በዚህም ከ13 ሚሊየን በላይ የመናዊያን የከፋ #ረሀብ ስጋት እንደተጋረጠባቸዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተ.መ.ድ) አስታዉቋል፡፡
የዉጭ ሀገር ጣልቃ ገብነት ሀገራት እና እርስ በርስ የሚዋጉ የመናዊያን የረሀብ አደጋ የተጋረጠባቸዉን ዜጎች ለመታደግ ግጭቱን እንዲያቆሙም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ቢቢሲ በዘገባዉ እንዳሰፈረዉ በየመን በተቀሰቀሰዉ ግጭት ከ10ሺህ በላይ ሰዎች #ህይወታቸዉን አጥተዋል፤ ሚሊዮኖች ደግሞ ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ

#update የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የተለያዩ #ሹመቶችን ሰጠ።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ምግባሩ ከበደ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊ፣
2. አቶ እዘዝ ዋሴ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና
3. አቶ ደሴ ጥላሁን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።
ፓርቲው ቀደም ሲል በገጠርና በከተማ አደረጃጀትና ፖለቲካ ዘርፍ ሲገለገልበት የቆየውን አደረጃጀት በማጠፍ ወደ ሁለት ዘርፍ በመጠቅለል የአደረጃጀት ዘርፍ እንዲሁም የፖለቲካ ዘርፍ በሚል አዋቅሮ ሹመቱን መስጠቱንም ነው ያመለከተው።
ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ

WALTA TV! ዋልታ ቴሌቪዥን ከጀዋር መሀመድ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ እየተላለፈ ነው።
walta tv፦ freq=11512 vertical 27500
@tsegabwolde @tikvahethiopia
walta tv፦ freq=11512 vertical 27500
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አማሮ⬆️
ደቡብ ክልል ውስጥ በአማሮ ወረዳና በምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት #ለማብረድ ከገቡ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ሦስቱ #መገደላቸውንና ሁለት መቁሰላቸውንም የተናገሩት አስተዳዳሪው አቶ አማኑዔል አብደላ “ታጣቂዎቹም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰዎች ስለ መሆናቸው መረጃ ደርሶናል” ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ስለጉዳዩ መረጃ እንደደረሳቸው የተናገሩት የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ “ድርጊቱ የተፈፀመው ‘በኦነግ ሠራዊት ነው፤ አይደለም’ የሚለውን በማጣራት ላይ ነን” ብለዋል።
ምንጭ፦ VOA AMHARIC