TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ኮሚቴ በኮንጎ #የኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ ሊወያይ ነው። ኮሚቴው በመጪው ረቡዕ ተሰብስቦ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ ተወያይቶ ዓለም አቀፋዊ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ላይ መድረስ አለመድረሱን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዲጂታል ቴክኖሎጂውን እያዘመነ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንተርኔት ሽያጩ ወደ 21 በመቶ ማደጉ ተገለፀ። አየር መንገዱ አገልግሎት አሰጣጡን #ቀልጣፋ እና #ተደራሽ ለማድረግ የትኬት ሽያጩንም ሆነ የክፍያ አማራጮቹን እያሰፋ ይገኛል። አሰራሩ በአየር መንገዱ የጥሪ ማዕከል፣ ድረ ገፅ እና ሞባይል አፕሊኬሽን ትኬት መቁረጥ የሚያስችል ስርዓት ነው።

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ ስሙን ሊቀይር ነው⬇️

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወታደራዊ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በማስረከብ በአዲስ ስያሜ ሊደራጅ ነው።

ከተቋቋመ ጀምሮ በጥቂት ጊዜ በርካታ የመንግስት ፕሮጀክቶችን እንዲይዝ ተደርጎ የነበረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከብቃት፣ እጦትና ከብክነት ጋር ተያያዘ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።

እጁ ላይ የነበሩ በርካታ የስኳር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ አቅቶት ፕሮጀክቶቹን ሲቀማ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሃይድሮ መካኒካል ስራዎችን ወስዶ መስራት ባለመቻሉም ቢሊየን ብሮች እንደባከኑ ተሰምቷል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኮርፖሬሽኑን አመራሮች ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድበት እያደረገ ነው።

የኮርፖሬሽኑ የኮመርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #አብዱልዓዚዝ_መሀመድ ለfbc፥ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ማስተካከል ነው።

ይህም በሜቴክ ስር ወታደራዊ ምርቶችን ሲያመርቱ የነበሩ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በመስጠት ቀሪዎችን በስሩ የሚያስቀጥል መሆኑንም ይናገራሉ።

በዚህ መሰረት ሜቴክ አዲሱን ስያሜ ይዞ የሲቪልና የንግድ ምርቶችን ብቻ የሚያመርት ሲሆን፥ የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል አዲስ ስያሜ ሊሰጠው እንደታሰበም ተናግረዋል።

ለዚህ አዲስ አደረጃጀት ረቂቅ ደንብ የተዘጋጀ ሲሆን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸቀደ በኋላ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

#ሜቴክ እስካሁን 14 ኢንዱስትሪዎችን ሲያስተዳድር የቆየ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወታደራዊ ምርቶችን የሚያመርቱ አራት ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ በመንግስት ተወስኗል።

ሆሚቾ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሽን፣ ጋፋት አርማመንት እና ልዩ ትጥቆች አምራች ኢንዱስትሪ የተባሉትን ነው ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ የተወሰነው።

ቀሪ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች በሜቴክ ወይም ወደፊት የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ በሚሰጠው ተቋም ውስጥ የሚተዳደሩ ይሆናል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ወታደራዊም የሲቪል ምርቶችንም ስለሚያመርት በማን እጅ መሆን ይኖርበታል የሚለውን ጉዳይ ለማጥናት ኮሚቴ መቋቋሙን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

አዲሱ ኮርፖሬሽንም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ የሚያንደረድሩ ምርቶች ላይ የሚሰማራ ይሆናል ብለውናል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ።

የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ አግኝቶ እንዲቋቋም የታሰበው ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ካፒታሉ እንደሚሻሻልለትም አቶ አብዱልዓዚዝ አንስተዋል።

ሜቴክ ከአመታት በፊት ሲቋቋም በ10 ቢሊየን ብር የተጠየ ካፒታል ነበር፤ ከዚህ ውስጥ የተከፈለው 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ አሁን ወታደራዊ ምርት አምራቾቹ ሲቀነሱ የተከፈለ ካፒታሉ ዝቅ ይላል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም ካፒታሉ ይከፈልለታልም ነው ያሉት አቶ አብዱላዚዝ።

አዲሱ ኮርፖሬሽን ከብቃት ማነስና ከብክነት ጸድቶ ለመሄድም እንደበፊቱ ኮርፖሬሽኑ አቅም ሳይኖር ብዙ ስራን ከመውሰድ ይልቅ፥ የተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ የሰው ሀይሉን በአግባቡ ለመጠቀም ታስቧል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኤርትራው ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በኢትዮጵያ ያደረጉት የሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ አስመራ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 6 እና 8 ቀን 2011 ዓ.ም 2ኛ እና 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል። ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት፥ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ #ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ ካቢኔት‼️

ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን 50% በሴቶች የተዋቀረ ካቢኔት ዛሬ ለስራ አስፈፃሚ አቅርበው #አፀድቀዋል

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲሱ ካቢኔ #ግምት በጥቂቱ‼️

በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የተካተቱ ናቸው ተብሎ የደረሰኝ መረጃ፦

🔹ወ/ሮ ሙፈሪያት - የሰላም ሚኒስትር

🔹ወ/ሮ ፈትለወርቅ - የንግድ እና ኢንድስትሪ ሚኒስትር

🔹ኢንጂነር አይሻ - የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር

🔹ዶክተር ኢርጎጌ - የሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስትር

🔹ወ/ሮ አዳነች አቤቤ - የትራንስፖርት ሚኒስትር

🔹ዶክተር ሂሩት - የከፍተኛ ትምህርት እና የሳይንስ ሚኒስትር

🔹ወ/ሮ ዳግማዊት ደግሞ__________
.
.
ሌሎችም ያልተጠበቁ ሹመቶች ይኖራሉ ተብሎ #ይጠበቃል። የካቢኔ አባላት ቁጥር ከ28 ወደ 20 ይቀንሳል።

🔹ነገ ጥዋት ተጨማሪ የሚደርሱኝን የስም ዝርዝሮች የማቀርብ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እጩ የካቢኔ አባላትን ለምክር ቤቱ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

አዲሱ የካቢኔ አባላትም በብቃት፣ በልምድ፣ በትምህርት ዝግጅት እና ለውጥን መምራት የሚችሉ ተብለው የተመረጡ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።

እንዲሁም አዲሱ ካቢኔ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ለመጀመሪያ በሚባል ደረጃ 50 በመቶ ሴቶች ናቸው የተባለ ሲሆን፥ ይህም ከ20 የካቢኔ አባላት 10ሩ ሴቶች መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት፦

1. ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል- የሰላም ሚኒስትር

2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር- ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር

3. ኢንጂነር አይሻ መሃመድ- የሀገር መከላከያ ሚኒስትር

4. አቶ አህመድ ሽዴ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር

5. አቶ ኡመር ሁሄን- የግብርና ሚኒስትር

6. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ- የገቢዎች ሚኒስትር

7. ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

8. ዶክተር ፍፁም አሰፋ- የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሚኒስትር

9. ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህረት ሚኒስትር

10. ዶክተር ጥላዬ ጌቴ- የትምህርት ሚኒስትር

11. ወይዘሪት የዓለምፀጋይ አሰፋ- የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር

12. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ- የትራንስፖርት ሚኒስትር

13. ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ - የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

14. አቶ ጃንጥራር አባይ-የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር

15. ዶክተር ሳሙኤል ሁርካቶ- የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር

16. ዶክተር ሂሩት ካሳው-የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️የህዝብ የወካዮች ምክረ ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል የስራ መልቀቂያ አቀረቡ። ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል መልቀቂያቸውን በዛሬው እለት እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው ያቀረቡት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቢኔ ሹመቱ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል!
ሰበር ዜና‼️ የጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን 50 % በሴቶች የተዋቀረ ካቢኔ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ #ፀድቋል

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በመካሄድ ላይ ይገኛል!
#update የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ እዲለቀቁ የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ይታወቃል። ዘመቻው ዛሬ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ጦላይ የተላኩት ወጣቶች "እያሰለጠናቸው" እንገኛለን በቀናት ውስጥ ይፈታሉ ብለው ለሚዲያ ተናግረው ነበር። ወጣቶቹ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከጦላይ እንዳልተለቀቁ ለማወቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር አይሻ⬇️

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሾመች። ኢንጂነር #አይሻ_መሃመድ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ሰብሰባ ኢንጂነር አይሻ መሃመድን #የአገር_የመከላከያ_ሚኒስትር አድርጓቸዋል።

ኢንጂነር አይሻ የአፋር ክልል ተወላጅ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በትራንስፎርሜሽናል ሊደር ሺፕ ኤንድ ቼንጅ አግኝተዋል።

በአፋር ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርም ነበሩ። በአሁኑ ወቅትም የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

በዛሬው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባም የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተሾሙት 20 የካቢኔ አባላት መካከል አስሩ ሴቶች ናቸው።

ምንጭ፦ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህ ሳምንት ይለቀቃሉ‼️የአዲስ አበባ #ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣቶቹ በዚህ ሳምንት ይለቀቃሉ‼️

ከአዲስ አበባ ተወስደው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጄኔራል #ደግፌ_በዲ ለቢቢሲ ገለፁ።

ወጣቶቹ የተያዙት "በጎዳና ላይ ንብረት ሲያወድሙና ሁከት ሲፈጥሩ ነው" ያሉት ኮሚሽነሩ መጀመሪያ ከተያዙት ተጣርቶ አሁን በማሰልጠኛ ያሉት 1174 እንደሆኑ ገልፀዋል።

እሳቸው እንደሚሉት የፈፀሙት ተግባር በህግ የሚያስጠይቃቸው ቢሆንም መታነፅ እንዳለባቸው በማመን ለዚህም ከቤተሰብና ከማህበረሰብ ቀጥሎ ሃላፊነት ያለበት መንግስት በመሆኑ ይህን ተግባሩን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

"ማነፅ ብቻ ሳይሆን የወጣቶቹን ማንነት በመገንዘብ ስራ የሌለው ስራ እንዲሰራ፣ ተማሪውም ትምህርቱን እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው እነዚህ ልጆች ላይ ስራ እየሰራን ያለነው"ብለዋል ኮሚሽነሩ።

ይህን ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሚመለከታቸው ትብብር ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊሶች ወጣቶችን በቡድን ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ስለመለቀቁ ለኮሚሽነሩ ከBBC ጥያቄ ተነስቶላቸው ነበር።

ምንም እንኳ እሳቸው ተንቀሳቃሽ ምስሉን ባይመለከቱትም ቦታው ተገልፆ ትክክለኛ መረጃ ከደረሳቸው ተግባሩን በፈፀሙት አካላት ላይ ተጣርቶ #እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።

መሳለሚያ ሞቢል አካባቢ ለግንቦት ሰባት መሪዎች አቀባበል ሲደረግ ሰንደቅ አላማ በመስቀልና ባነሮችን በመለጠፍ ይንቀሳቀስ ነበር።

ያሳደጉትና የክርስትና ልጃቸው በአመፅ ሳይሆን የግንቦት ሰባት መሪዎች አቀባበል ላይ ባደረገው ተሳትፎ ከዚያም የቡራዮውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣቱ መታሰሩን አቶ ዘመነ ሞላ ለቢቢሲ ይገልፃሉ።

ከዚህ ውጭ ልጃቸው ሰላማዊ እንደሆነም ያስረዳሉ። ያሳደጉት ልጃቸው ወጣት ፍስሃ ደምስ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን እናቱ እንደሌለችና የሚኖረው ከአቅመ ደካማ አያቱ ጋር እንደነበር አቶ
ዘመነ ይናገራሉ።

እሳቸው እንደገለፁት የታሰረው ወደ ቤቱ የሚወስድ መንገድ ላይ አመሻሽ ላይ ነው። መጀመሪያ ወደ ተወሰደበት ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ሲጠይቁ ጦላይ መወሰዱን መስማታቸውንና ከዚያ በኋላ ያለ ምንም መረጃ ቤተሰብ ስቃይ ላይ እንዳለ ይገልፃሉ።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ጅምላ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። በማህበራዊ ሚዲያው የአዲስ አበባ ወጣቶች ይፈቱ የሚል ዘመቻም በመካሄድ ላይ ነው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ አስሮ ስልጠና ማስገባት የህግ አግባብነት እንደሌለው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የህግ ባለሙያና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ መንግስት እነዚህን ወታደሮች አስሮ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በመላኩ የጣሳቸው ህጎች አሉ ትላለች።

"ተግባሩ በትንሹ አራት የህገ መንግስቱን አንቀፆች ይጥሳል።የታሰሩ ሰዎች መብት፣ የተከሰሱ ሰዎች መብት ፣ የተጠረጠሩ ሰዎች መብትና ከዚያም ጋር ተያይዞ መደረግ የሚገባቸው ነገሮች በትንሹ አንድ አራት የህገመንግስቱ አንቀፆች ተጥሰዋል። የወንጀል ስነስርዓት ህጉንም ብንመለከት እዚያ ላይም የተጣሱ ነገሮች አሉ" ትላለች።

እሷ እንደምትለው በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ መንግስት ሰዎችን ሰብስቦ ካሰረ ያሰረበትን ምክንያት ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍቃድ መጠየቅ ይኖርበታል። በወሰደው እርምጃ የቀማው የግለሰቦችን ነፃነት በመሆኑ ይህን ደግሞ ያለ ፍርድ ቤት ፍቃድ ማድረግ አይቻልም።

ስለዚህም ግለሰቦቹን ፍርድ ቤት አለማቅረብ፣ የተከሰሱበትን ምክንያት አለማወቃቸውን እንዲሁም የዋስትና መብታቸውን መነፈጋቸው በሃይማኖትና በዘመድ መጎብኘት አለመቻላቸውን የመሰሉ ነገሮች ሲታዩ በእርምጃው ብዙ የመብት ጥሰቶች እንዳሉ ታስረዳለች።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ያጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የተጠሪ ተቋማት ዝርዝር ከላይ ባለው ምስል ቀርቧል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia