TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አክንዉሚ አዴሲና የሚመራውን የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድኑ የአፍሪካ ልማት ባንክ በመስኖ ልማት፣ በወጣቶች ስራ ፈጠራ፣ በኃይልና በግል ዘርፎች ለኢትዮጵያ ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ ጠንካራ ግንኙነትና ትብብር እንዳላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አጋሮ⬆️አጋሮ ዛሬ በመጠኑም ቢሆን ወደ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው። ትላንትና ውጥረት ውስጥ በዋለችው አጋሮ የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱ ይታወቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባሌ ሮቤ⬆️አክቲቪስት ጃዋር መሀመድ በባሌ ሮቤ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ⬆️የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከpc2 (ጤና ተማሪዎች) ለታዳጊዋ የህክምና ተማሪ ማርያም ተስፋዬ የህክምና ወጪ የ1,315 ብር ድጋድ ማድረጋቸው አሳውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ጥቂት የሠራዊት አባላት ወደ ቤተ መንግስት እንዲሄዱ ከጀርባ በመሆን #ሲያነሳሱ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ሰዓረ_መኮንን አስታውቀዋል።

ቪድዮ፦ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅሰቃሴ ማድረግ #ፈጽሞ አይፈቀድም፡፡›› ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን

ክልከላው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) #የሚያካትት እንደሆነም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔹ዶክተር ዐብይ አህመድ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት🔹

ቪድዮ፦ ድርሻዬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia