TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update⬆️ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ መክፈቻ ስነ ስርዓት አስመልከተው #የእራት_ግብዣ አደረጉ፡፡ የእራት ግብዣው ላይ የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የዲፕሎማቲከ ማህበረሰብ እና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ‼️በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ #የፀጥታ_ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ህዝባዊ #ውይይት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚዛን ቴፒ ዪኒቨርስቲ (ቴፒ ካምፓ)⬇️

"በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የሚደረገዉ ዉይይት በቴፒ ካምፓስ ከአካዳሚክ ስታፎች እና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ዛሬ ጥዋት ተጀምሯል። ዉይይቱም ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚደረግ ይሆናል፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
*በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ኮርተናል*

*እንዲህ ነው ሰብዓዊነት! እንዲህ ነው ኢትዮጵያዊነት*

(ሼር ይደረግ)

ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የአዲስ አበባ እና አካባቢው ነዋሪዎች አስቸኳይ #እርዳታ እንድናሰባስብ በጠየቅነው መሰረት፤ በዛሬው እለት በርካታ ገር ልብ ያላቸው ወገኖቻችን የተለያዩ እርዳታዎችን በመያዝ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተገኝተዋል። ቸር አምላክ ብድራችሁን ይክፈል።

የእርዳታ ማሰባሰብ ስራው በነገው እለትም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:30 ድረስ ይቀጥላል። ነገ የእርስዎ ተራ ነው! እንጠብቅዎታለን!

ለማስታወስ ያህል፦

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)

ለበለጠ መረጃ፦ መሐመድ ካሳን ወይም ያሬድ ሹመቴን በቀጣዩ ስልክ ማግኘት ይችላሉ። 0930 36 52 44 በድጋሚ ለበጎ ምግባር አድራጊዎች በሙሉ ያለንን የከበረ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን። ቸር አምላክ ይስጥልን!!

#ቅድሚያ_ለሰብዓዊነት

(ደጋግመው ሼር እንዲያደርጉ እንማፀናለን)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
164,000የቤተሰባችን አባላት በየቀኑ እየበዙ ይገኛል። ለዚህ ሁሉ እየከፋላችሁት ላለው ውለታ ምስጋና ይድረሳችሁ። ሁላችሁንም በሀገር ውስጥም በውጪ ያላችሁ ፈጣሪ ያክብርልኝ!

ጉዞው ይቀጥላል➡️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስንከራከር #እንደማመጥ ትሁት ሆነን የማናውቀውን ነገር ከሌሎች #እንማር!

©አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥሪ ለሀዋሳ ከተማ ተማሪዎች‼️የTIKVAH-ETH 4ኛ አመት የመማሪያ መፅሀፍት የማሰባሰብ ዘመቻ እንደቀጠለ ይገኛል። በአለን ኢትዮጵያ አስተባባሪነት መፅሀፍት በየትምህርት ተቋማቱ እየተሰባሰበ ይገኛል።

የሀዋሳ ከተማ ተማሪዎች እና ነዋሪዎች ቤታችሁ ካሉ የመማሪያ መፅሀፍት መካከል በመለገስ ለሀገራችን ኢትዮጵያ በስጦታነት እናበርክት!

ከ1-12ኛ ክፍል ያሉ ማንኛውም የመማሪያ መፅሀፍትን መለገስ ይቻላል!
ከ1 መፅሀፍ ጀምሮ!

አለን ኢትዮጵያ ማህበር አስተባባሪዎች፦
0926429534(ተስፋማሪያም @Physicaltes)
0935932153(ብስራት @EATTB)
0916424992(ጌትነት @Getzone)
0934727411(ዮርዳኖስ)

አለን ኢትዮጵያ‼️

ኑ! ጎዳና የወጡትን ወገኖቻችን በማንሳት ለአዲሲቷን ኢትዮጵያ እንገንባ!!!

@alen_leethiopia
@alen_leethiopia2
ለበለጠ መረጃ እና አባል ለመሆን ለመትፈልጉ፦

✆0926429534(@Physicaltes)
✆0935932153(@EATTB)
✆0968647591(@AUCplan )
✆0912955247(@Elisweet)
✆0916453033( @agi_i )
.
.
.
@tsegabwolde @tikvabethiopia
#Update ለአምስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ወደ አረብ ሀገራት የሚደረግ የውጪ ሀገር የስራ ስምሪት ነገ ረቡዕ #ይጀምራል። ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለፀው ስምሪቱ የሚደረገው የሁለትዮች የጋራ ስምምነት ከተደረሰባቸው ሀገራት ማለትም ሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ እና ኳታር ጋር ነው።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikavhethiopia
#update አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ በተያዘው 2011 ዓ.ም. #በስራ ላይ የሚውል ይሆናል።

©ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲሱ ትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ዙሪያ የተብራራ እና ግልፅ መረጃ እንደደረሰኝ የማቀርብ ይሆናል። በተለያዩ መንገዶች ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ልትጠነቀቁ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ በተያዘው 2011 ዓ.ም. #በስራ ላይ የሚውል ይሆናል።

©ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ
@tsegabwolde @tikvahethiopia