TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ⬆️

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ የአለም የህዋ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የባህል ማእከል ፕሮግራሙን ዛሬ ይጅምራል። "በህዋ አለም አንድ ትሆናለች " በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን ማንኛውም የህዋ ሳይንስ ፍላጎት ያለው ፕሮግራሙን መከታተል ይችላል።
በፕሮግራሙ
🔺ኤግዚብሽን
🔺 ትምህርቶች(public lectures) እንዲሁም
🔺ጥያቄ እና መልስ ይኖራል

©Ruth
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሚሴ⬆️ዛሬ ከሚሴ ላይ የነበረው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) ህዝባዊ ስብሰባ ከላይ የምትመለከቱትን ይመስላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከላሊበላ⬇️

"​​የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የመፍረስ አድጋ ከፊትለፊታቸው ተጋርጧል። ምክንያቱም ሸራ ለመወጠሪያ በሚል ሰበብ ከላያቸው ላይ የተቀመጠው ምሰሶ እንዱ ብቻ 3 ቶን የሚሆን ነው። እናም ከህንፃዎቹ አቅም በላይ ስለሆነ እንዲነሳ የሚል ጥያቄ ከ አካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎቹም ለመንግስት ቢ ያመለክቱም እስካሁን በመንግስት በኩል የተደረገ ምንም ነገር የለም። እናም ሁላችሁም ምዕመናን ይህንን የሀገራችንን እንዲሁም የአለምን ቅርስ ከተጋረጠበት አደጋ ለማላቀቅ እና ተገቢው እድሳት እንዲደግረ በአገኛችሁት አጋጣሚ ለሚመለከተው አካል ይድረስልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሰላ⬆️የ2011 የኢሬቻ በዓል በአሰላ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

@tsegabwolde @tikvahiopia
#ኢሬቻ2011⬆️የመልካ አቴቴ ኢሬቻ በዓል በዛሬው ዕለት ተከብሯል። የኢሬቻ በዓል በቡራዩ መልካ አቴቴ፣ በገላን ጨፌ ቱማና በሰበታ መልካ ሰበታ ነው የተከበረው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ ግጭት በተከሰተባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላለፉት 2 ቀናት በአብዛኛዎቹ #መረጋጋት የታየባቸው ቢሆንም ሆሮ ሊሙና ያሶ በተባሉት ቦታዎች ግን አሁንም የፀጥታ ሥጋት መኖሩን የምሥራቅ ወለጋ ዞን የፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ቶሎሣ ለኢቲቪ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው ያለና #ማንነቱን በግልፅ ለመለየት ያልተቻለ የተደራጀ እና የታጠቀ ኃይል ሕዝቡን ሥጋት ውስጥ ከቶታል ያሉት ኃላፊው ችግሩን ለማስቆም መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia