TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ናዲያ ሙራድ🕊 በፈረንጆቹ 2014 በሃገሯ #ኢራቅ በጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን #አይ_ኤስ ታግታ የቆየችና #የወሲብ ጥቃት ሰለባ የሆነች ወጣት ናት። ከቡድኑ እገታ ከወጣች በኋላም ይህን መሰሉ #ጥቃት እንዲቆምና በጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ #ሴቶችን ለመታደግ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ናዲያ ላደረገችው ጥረት የዘንድሮው የኖቤል #የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
.
.
እኔ ግሌ እስካሁን ድረስ በህይወቴ ውስጥ ካየኋቸው እና ታሪካቸውን ከሰማሁ ድንቅ ሰዎች አንዷ ናት። ከእርሷ ጥንካሬን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ሰላም ወዳድ መሆንን፣ ለሰው ልጅ መኖርን ተምሪያለሁ! ዛሬ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ለናዲያ ያለኝን ትልቅ ክብር ለመገልፀ እወዳለሁ!
.
.
🕊🕊🕊ናዲያ ሙራድ🕊🕊🕊
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ዴኒስ የ2018 የኖቤል የሰላም አሸናፊ!
ዶ/ር ዴኒስ🕊ኮንጓዊው የማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር #ዴኒስ_ሙክዌጊ የዘንድሮው የኖቤል #የሰላም ሽልማት አሸናፊ ነው። በጦርነት ወቅት የሚደርስ #የወሲብ ጥቃትን ለማስቆም ባደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማቱን ያገኙት። ኮንጓዊው ዶክተር የዚህ ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ህክምና በሚሰጥ ክሊኒክ ውስጥ ህክምና በመስጠት የሚፈጸመው የወሲብ ጥቃት እንዲቆም ሲታገሉ መቆየታቸው ተገልጿል።

ዶክተር ዴኒስ ለሰላም ላደረጉት ትልቅ ስራ በቻናላችን ስም እናመሰግናቸዋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢህአዴግ ጉባኤ ሀዋሳ⬇️

የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች በድርጅቱ ስራ አስፈፃሚና ምክር ቤት ውስጥ እንዲሳተፉ በ11ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ ተወሰነ።

የአጋር ድርጅቶች ሊቀመናብርትና ምክትል ሊቀመናብርት በቀጥታ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲሳተፉ ተወስኗል።

እንዲሁም የአጋር ድርጅቶቹ አምስት የስራ አስፈፃሚ አባላት በኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲሳተፉም ነው ጉባዔው #ውሳኔ ያስተላለፈው።

የጉባዔውን መጠናቀቅ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት አቶ ፍቃዱ ተሰማ፥ የአጋር ድርጅቶቹ የሚሳተፉት #ያለድምፅ መሆኑን ተናግረዋል።

አጋር ድርጅቶቹን ወደ ሀገራዊ መድረክ ለማምጣትና አንድ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት በጥናትና እውቀት ላይ ተመስርቶ ውይይት በማድረግ ወደ ኢህአዴግ የመቀላቀሉ ሂደት እንዲጠናቀቅ ጉባዔው ለኢህአዴግ ምክር ቤት ውክልና ሰጥቷል።

ጉባዔው በህግ የበላይነት መከበር ፣ በልማት ስራዎች፣ በወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ላይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ እንዲሰራ አቅጣጫ ማስቀመጡ ተገልጿል።

ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተጀመረው የዲፕሎማሲ ስራም ብሄራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቅ መልኩ ተጠናከሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በየአካባቢው አየተስተዋለ ያለው መፈናቀልና ሰብዓዊ መብት ጥሰት በምንም መልኩ ድርጀቱ እንደማይታገስም አቶ ፍቃዱ በመግለጫቸው አመልክተዋል።

ለዚህም የፀጥታ አካላት ተገቢውን #እርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ እንደተቀመጠም ነው የጠቆሙት።

የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ለማስቀጠል የመንግስት ተቋማት ሪፎርም እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል።

በተለይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚያሰፉ ገለልተኛና ወገንተኝነታቸው ለህዝብ የሆኑ ተቋማት ለመገንባት የሪፎርም ስራዎች በአፋጣኝ
ተግባራዊ እንዲሆኑ ጉባዔው አሳስቧል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢህአዴግ‼️ በየአካባቢው አየተስተዋለ ያለው #መፈናቀልና ሰብዓዊ መብት #ጥሰት በምንም መልኩ ኢህአዴግ እንደማይታገስ ተመለከተ። ለዚህም #የፀጥታ_አካላት ተገቢውን #እርምጃ እንዲወስዱ አቅጣጫ ተቀምጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
*አስቸኳይ የሰብዓዊነት ተግባር ላይ ይሳተፉ*

(ሼር ይደረግ!)

ከቤኒሻንጉል #ለተፈናቀሉ ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በህይወት ለመድረስ የአዲስ አበባ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የእርዳታ ማስተባበሪያ መርሐ ግብር በመልካም ሁኔታ እየሔደ ነው።

የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ መስከረም 28 እና 29 በሀገር ፍቅር ቴአትር ከሚሰበሰበው እርዳታ #በተጨማሪ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ለሚመቻቸው ወገኖቻችን ከዚህ በታች ባሉ ግዚያዊ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ያዘጋጃችሁትን እርዳታ እያስመዘገባችሁ መለገስ ትችላላችሁ።

ለማስታወስ ያህልም የእርዳታ አይነቶቹን በድጋሚ እናስታውቃለን።

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
በመሆኑም ከዚህ በታች በተቀመጡት ተጨማሪ አድራሻዎች ቅዳሜና እሁድን ብቻ የቻሉትን በአቅራቢያዎ መለገስ ይችላሉ።

🔹ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ ~0911219235 ቦሌ ኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ምስራቅ በር ስጋ ቤት @Blen Sahlu

🔹ኮልፌ እና 18 ማዞሪያ ፍቅሩ አብጤ +251911319571

🔹ሰባተኛ የአማኑኤል ታክሲ መያዣ 0911793475 ደንበል ጀርባ ከ ላፓሪዝያን ፊት ለፊት ሶሎሞን ሞባይል +251912634363 @Solomon Mengesha

🔹ፒያሳ ማስታወቂያ ሚንስቴር አካባቢ ተስፋዬ ለማ ~+251912914748
ለበለጠ መረጃ መሐመድ ካሳ ወይንም ያሬድ ሹመቴን በ0930 36 52 44 ማግኘት ይችላሉ።

ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች፤ አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

#ሰብዓዊነት_ይቅደም !!

(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ!)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋልጉን⬆️

"ዘቢባ በሽር ትባላለች ያደረገችው ቢጫ ሻርብ የለበሰችውም እንዲሁ 22 አካባቢ ባቡር ውስጥ ገብታ #ጠፍታብናለች ያያችኋት ሰዎች ተባበሩን። 0936959633 , 0911131844 ቤተሰቦቿ ነን"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ‼️

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በሠላም መጠናቀቁን በማስመልከት በሲዳማ ብሔር ባህላዊ ጫዋታ ( #በቄጣላ) እንደሚበሰር ተገለፀ።

"ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 23-25/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በድል መጠናቀቁን ለማብሠር ነገ ቅዳሜ መስከረም 26/2011 ዓ.ም. በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትሪ ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ እና የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሪ አቶ #ደመቀ_መኮንን ጨምሮ የየሁሉም ክልሎች ርዕሳኔ መስተዳድሮች፣ የእህትና አጋር ድርጅቶች አመራሮች እንዲሁም የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ተሳታፊ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከጧቱ 1:00 ጀምሮ የቄጣላ ትዕይንት ከታዬ በኋላ ጉባዔው በይፋ ይዘጋል።

በመሆኑም በተባለው ሰዓት በቦታው ተገኝታችሁ ትዕይንቱን እንድትከታተሉ የሲዳማ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም25/2011 ዓ.ም
ሀዋሳ,ሲዳማ

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል፣ ቱሪዝም እና መንግስ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከታቹ‼️

(ከፂዮን ግርማ)

ለመምከር አይደለም-የተሰማችኝን ለማካፈል ነው። ዕድሜ ብዙ ነገር ያስተምራል። በዕድሜያችን ላይ የሚጨምረው ሰዓትና የተጓዝንበት ሂደት ለሚቀጥለው ጊዜ #ስህተት እንዳንሠራ ሊታደገን ይገባል።

ጤናማ ባልሆነ ውድድርና #በብሽሽቅ ውስጥ፤ ከተወዳዳሪውና ከተበሻሻቂው ውጪ በማያውቀው ነገር በፅኑ #የሚጎዳ አካል (ሕዝብ) አለ።

ከችግርና ችጋር ጋር እየታገለ ምንም በማያውቀው ነገር ድንገት መከራ የሚወርድበትን አካል ለመታደግ የምታስፈልገው ነገር “ትንሽ” ናት "ጨዋ" #ቃላትን መጠቀም።

ስድብ፣ ማዋረድና ማንቋሸሽ ከታከለበት ውድድርና በብሽሽቅ ወጥቶ በሐሳብና በጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ አስተያየት መስጠት። #በጨዋ ቋንቋ እየታገዙ የሐሳብ ድርና ማግን መሸመን ከልካይ አይኖረውም።

አንደበታችን ለበጎ፣ ጣቶቻችንን ደግሞ #ለመልካም ሥራ እናውላቸው። ተመልሰን #ለማንመጣባት ምድር መጥፎ ነገር ጥለን አንለፍ። #ጤናማ የአደባባይ ላይ ክርክርና የውይይት ባህልን እናዳብር፣ #ቴክኖሎጂን ከመጥፎ ነገር ይልቅ ለጥሩ ነገር እንጠቀም። እጆቻችንን #ለስድብ አናታትራቸው።

#ሼር - በፌስቡክ ገፃቹ ላይ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወ/ሮ ሙፈርያት በምርጫው አልተወዳደሩም – ከምርጫ ራሳቸውን #አላገለሉም። ሦስት ሰው ተጠቆመ።

በዚህም መሠረት፦
🔹ዶ/ር ዓቢይ አህመድ በአቶ ሚሊዮን ማቴዎስ
🔹አቶ ደመቀ መኮንን በአቶ ለማ መገርሳ፣
🔹ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለእጩነት ተጠቆሙ።

በዶ/ር ደብረጽዮን ጥቆማ የሕወሓት እጩነት ተቃውሞ አቅርበው ነበር። ይሁን እንጂ በእጩነት #ይወዳደሩ የሚል በርካታ አባል #የድጋፍ ድምጽ ሰጠ። በምስጢር በጽሁፍ ነው ድምጽ ተሰጠው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ⬆️የዋቸሞ ዩኒ ቨርሲቲ እንዲሁም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ተቋሞቹ ባወጡት ማስታወቂያ ገልፀዋል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬆️

#የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ለመሳተፍ በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ለጉባዔው ተሳታፊዎች የባህላዊ ቁርስ( #ቡርሳሜ ) ግብዣ አድርገዋል። የሀገር ሽማግሌዎቹ ከእንሰት የተዘጋጀውን ቡርሳሜ የተሰኘ ባህላዊ ቁርስ ከእርጎ ጋር ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia