TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️Miss Grand Ethiopia 2018 #ሳምራዊት_አዝመራው ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ማይናማር ከተማ ዛሬ ለሊቱን ትበራለች። በቻናላችን ስም መልካም ዕድል እንመኝላታለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኖቤል 2018⬇️

የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ነገ ረፍድ ይፋ ይደረጋል። ምርጫውን የሚያከናውነው 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ የዘንድሮ የኖቤል #የሰላም_ሽልማት ዕጩዎች ቁጥር 331 መሆኑን አሳውቋል።

ከእነዚህም መካከል 216 ግለሰቦች ሲሆኑ 115ቱ ደግሞ ቡድኖች መሆናቸውን ኮሚቴው ጠቁሟል።

በኖቤል ሽልማት አሰራር መሰረት ዕጩዎች ለህዝብ ይፋ የሚደረጉት ከ50 ዓመታት በኋላ ነው።

ዕጩዎቹ እነማን እንደሆኑ ባይታወቅም በርካቶች የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት ማን ሊያሸንፍ እንደሚችል የራሳቸውን ግምት እየሰጡ ይገኛሉ።

የሁለቱ ኮሪያ መሪዎች የአሸናፊነቱ ቅደሚያ ግምት ከተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል። የሰሜን ኮሪያው መሪ በሰብዓዊ መብት አያያዘቸው በተደጋጋሚ ቢወቀሱም ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ጋር በመሆን በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየውን ውጥረት ለማርገብ የወሰዷቸው እርምጃዎች የሽልማቱ ተመራጭ ያደርጋቸዋል የሚሉት በርካቶች ናቸው።

ሌላው ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው መሪዎች መካከል እንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

ትራምፕ በኮሪያ ባህረሰላጤ ሰላም ለማስፈን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ኒኩለር ቦንም ከማበልጸግ እንድተቆጠብ ላደረጉ ያላሰለሰ ጥረት ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሏል።

የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል እስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ይገኙበታል።

የሳውዲ ዜግነት ያለው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ ፣ ''የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም እስልምናን ዘልፏል'' በሚል ክስ ላለፉት 6 ዓመታት በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ይገኛል።

በስፔን መንግሥት ሕጋዊ እውቅና ባልነበረው ሕዝበ ውሳኔ ካታላኖች በካርለስ ፑይግዴሞንት እየተመሩ ከስፔን ተገንጥለው ሃገር ለመመስረት ሙከራ አድርገው ነበር። ሕዝበ ውሳኔውን ተከትሎም ካርለስ ከስፔን ሸሽተው በቤልጅም እየኖሩ ይገኛሉ።

ከግለሰቦቹ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሽልማቱን ሊያሸንፍ ይችላል ከተባሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ
ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር #ዐብይ_አህመድስ ከዕጩዎቹ መካከል እንዱ ሊሆኑ አይችሉም?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኖቤል ሽልማት እንዲያገኙም ጭምር ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኖቤልን የሰላም ሽልማትን የጊዜ ሰሌዳ ስንመለከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ነገርን አጠያያቂ ያደርገዋል።

የኖቤል ኮሚቴ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ነው፦

🔹መስከረም፡- በፈረንጆች መስከረም (ሴፕቴምበር) የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ እጩዎችን ለመቀበል ይሰናዳል። እጩ የመቀበሉ ሥራ ለቀጣይ ስድስት ወራት ይጸናል። እጮዎቹን መጠቆም የሚችሉት ከላይ የተዘረዘሩት ብቁ ጠቋሚ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ናቸው።

🔹የካቲት፡- በየካቲት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ያበቃል። ከየካቲት 1 በፊት ያልተጠቆመ በዚያ ዓመት እጩ መሆን አይችልም።

🔹መጋቢት፡-ኮሚቴው የእጮዎችን ዝርዝር ያቀርባል። ከእጮዎቹ ውስጥ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑትን ብቻ ለተጨማሪ ማጣሪያ ይቀርባሉ።

🔹ጥቅምት፦ በጥቅምት መጀመርያ ኮሚቴው አሸናፊውን በድምጽ ብልጫ ይመርጣል። ይግባኝ የማይባልበት ምርጫ ነው ታዲያ።

🔹በታኀሳስ፦ 10 (በፈረንጆቹ) በኦስሎ ኖርዌይ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል።

የኖቤል ሽልማት ከአንድ ዓመት ዘለግ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሂደት ነው። ኾኖም ጥቆማ የመቀበያ ጊዜ ከፈረንጆች መስከረም ጀምሮ ለ6 ወራት የሚዘልቅ ነው። ይህ እንግዲህ መጪውን የመስከረም ወር ሳይሆን የ2017ቱን ወር አንድ ብሎ የሚጀምር ነው።

የእጩ መስኮቱ ከተዘጋ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ ቢያንስ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ዐድል ጠባብ ያደርገዋል። ምናልባት የኖቤል ኮሚቴው በመጨረሻዎቹ ጊዜያት እጩ የመጨመር ሥልጣን ስላለው ያ ተግባራዊ ከሆነ
ጠባብ እጩ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቀላሉ ነገር መንግስትን #መጣል ነው፤ ከባዱ ነገር ሀገር #መገንባት ነው!

አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ASTU⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል።
25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች📌የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የመግቢያ ቀንን በደጋሚ እያራዘሙ በመሆኑ በዩኒቨርስቲዎቻችሁ ድረ ገፅ እና የፌስቡክ ገፅ ላይ አዳዲስ ማስታወቂያዎችን እድትከታተሉ።

▪️ምንም የጥሪ ለውጥ ያላደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ካሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተቋማችሁ ለመግባት ዝግጅት አድርጉ!
@tsegabwolde @tikvahthiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስከረም 30 ከኬንያ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ #በባሕር_ዳር ዝግጅት ያደረገ ነው፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ኬንያ ጋናን አሸነፋ ለውድድር የቀረበች ቡድን በመሆኗ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀናል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በሐረር ከተማ በነዋሪዎች ዘንድ ተደጋጋሚ #ቅሬታ ሲፈጥር የነበረውን የተከማቸ ደረቅ ቆሻሻ የማንሳት ሥራ መጀመሩን የከተማው ማዘጋጃ ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ፦ አክሱም ዩኒቨርሲቲ⬇️

ውድ የአክሱም ዩንቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ ቀደም ሲል የነባር መደበኛ ተማሪዎች የመመዝገብያ ቀን ጥቅምት 12-13, 2011 ዓ/ም ኣ እንዲሁም የአዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች የመመዝገብያ ቀን ከጥቅምት 17-18, 2011 ዓ/ም መሆኑ መግለፃችን ይታወሳል።

ይሁን እንጁ የመመዝገብያ ቀኑ በድጋሜ #እንደተራዘመ ከይቅርታ ጋር እየገለፅን የትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን ማስታወቅያ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

የኤክስቴንሽን ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች ቀደም ሲል በተገለፀው ማስታወቅያ የሚካሄድ መሆኑን እናሳስባለን!

ምንጭ፦ Dr. Kiros Guesh
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር‼️ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ቀን በድጋሚ እንዲራዘም አድርጓል። ምክንያቱ ለምን እንደሆነ የተገለፀ ነገር የለም። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ-ዶ/ር ዐብይ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2011 የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ፍጹም #ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን በሚቻልበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች እና ከክልል አመራሮች ጋር #መወያየታቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጎን ለጎን በትናት ምሽት ከአመራሮቹ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ ወቅት የትምህርት ዘመኑ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን የተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት፣ የክልል አመራሮችና #የጸጥታ አካላት ኃላፊነት እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ከጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስትር ማስታወቁ #የሚታወስ ነው።

በዘንድሮ አመት ከ149 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች #ዩኒቨርስቲዎች በሚያወጡት መርሃግብር መሠረት ጥሪ እንደሚደረግላቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል!
ሰበር ዜና‼️

የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ይፋ ሆነ ከግንቦት 27-30/2010 ዓ/ም በተሰጠው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ /የ12ኛ ክፍል ፈተና 154,010 ወንዶች እንዲሁም 127,964 ሴቶች በድምሩ 281,974 ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን በሐምሌ 24/2010 ዓ/ም ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ኤጀንሲያችን ውጤቱን ከገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ለምደባው የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያካሂድ ቆይቶ ምደባውን በዛሬው ዕለት 25/01/2011 ዓ/ም ከ8 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይደርጋል፡፡

ምደባው የተማሪዎችን ውጤት፣ የፊልድ እና የዩንቨርስቲ ምርጫ፣ የዩንቨርስቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የወንዶችና የሴቶችን ምጥጥን ማዕከል
ባደረገ እንዲሁም የልዩ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን /በማጥባት ላይ የሚገኙ ሴቶችን፣ ዓይነ ስውራንን፣ መስማት የተሳናቸውን፣ አካል ጉዳተኞችን/ በተጨማሪም የጤና እክል ያለባቸው እና ከታወቀ የመንግስት ሆስፒታል የሜዲካል ቦርድ ማረጋገጫ ያቀረቡት ላይ የማጣራት ስራዎችን ካካሄደ በኋላ ተከናውኗል፡፡

በዚሁም መሰራት በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥቡን አሟልተው ያለፉ 138,283 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ 75,338 የማህበራዊ በድምሩ 213,621 ናቸው፡፡

ከነዚህም መካከል 98,576 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና 51229 የማህበራዊ ሳይንስ በድምሩ 149,805 ተማሪዎች በቅዱስ ጳውሎስ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ባሉት 43 የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኤጀንሲያችን በ43ቱ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት /ዩንቨርስቲዎች/ ምደባ ይካሄድባቸዋል ተብለው የሚጠበቁት 9,5681
የተፈጥሮ ሳይንስ፣ 51,066 የማህበራዊ ሳይንስ በድምሩ 146,747 ተማሪዎች ይሆናሉ፡፡

ኤጀንሲው ከላይ የተጠቀሱትን የማጣራት ስራዎች በማከናወን ሂደት ውስጥ በመቆየቱ ምክንያት ምደባው ዘገየ በማለት ቅሬታችሁን
ስታሰሙ ለነበራችሁ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦች ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየቅን ተማሪዎች #በተመደባችሁባቸው የትምህርት ተቋማት በምትሄዱበት ወቅት የነገዋ ኢትዮጵያ በእናንተ ትከሻ ላይ መሆኗን በመገንዘብ በትምህርታችሁ ላይ ብቻ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ በመሆን ለሀገራችን እድገት እና ልማት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታበረክቱ ዘንድ ኤጀንሲችን ከአደራ ጭምር መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

ተማሪዎች ምደባችሁን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

መልካም ዕድል!

ምንጭ፦ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopja