TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሚመለከተው ሁሉ⬆️

"እኛ አመልካቾች በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ቀበሌ 06/07 በቤት ቁጥር 737, 738, 739, 741 ልዩ ቦታው ቤላና ፈረንሳይ መገንጠያ(ቀድሞ 11ቀበሌ የአሁኑ የፌዴራል ካምፕ ፌት ለፊት) እስከ1983 ዓ.ም ድረስ ስንጠቀምበት የነበረውን የጋራ መጠቀሚያ ሽንት ቤት እና ማዕድ ቤት እንዲሁም መተላለፊያችንን መንገድ በማጥበብ የሬሳ ማውጫ እንኳን በማሳጣት በቦታው የቀድሞ የቤቱ ባለቤቶች በላያችን ላይ ሌላ ቤት ሰርተው እየተጠቀሙበት ይገኛል። የሚገርመው እነዚህ ቤቶች በ G.I.S ላይ እንደሌሉ እና የኛ የቀድሞው የጋራ መጠቀሚያንና ባዶ ቦታን ነው የሚያሳየው። ይህንን ችግራችንን ለረጅም አመታት ለወረዳ 03 እና ለየካ/ክ/ከ ብናመለክትም መጥተው ከማየትና ከንፈር ከመምጠጥ በስተቀር ምንም አይነት መፍትሔ አላገኘንም። ብሎም ቅሬታችንን ለከንቲባ ለህዝብ ቅሬታ አመልክተን በስልክ እና በደብዳቤ በ15 ቀን ውስጥ መፍትሔ ሰጥታቹ አሳውቁን ቢባሉም ይሄው አመታትን አስቆጠርን። በ21ኛው ክፍለ ዘመን መሀል ከተማ ተቀምጠን በፖፖ እየተጠቀሙ አስፓልት ዳር እየተደፋ ለአካባቢው ሰው እና ለሕፃናት ችግር እየፈጠረብን ይገኛል። እንዲሁም የአካባቢው ሕፃናት ለተለያዩ በሽታዎች እየተዳረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖብናል። ስለዚህ የሚመለከተው አካል ቦታው መጥታቹ በማየት መፍትሔን እንድታሰጡን ስንል በትህትና እናመለክታለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዩጋንዳ #የመብረቅ አደጋ ደርሶ የሶስት ተማሪዎች ህይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው በሰሜን ምዕራብ ዮምብ ግዛት ነው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬆️

የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬው ምሽት በሃዋሳ ከተማ ለሚገኙና በኢህአዴግ 11ኛው ጉባኤ ላይ ለታደሙ ጉባኤተኞች እና ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ለመጡ እንግዶች የእራት #ግብዣ አደረጉ።

በእራት ግብዣው ላይ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለጉባኤው ስኬት ምርቃትና ጸሎት ያደረጉ ሲሆን የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብም ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የውጭ ዝርያ ያላት ከ40-60 ሊትር መታለብ የምትችል የ7ወራት ጊደር በስጦታ አበርክተዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩም ምስጋና በማቅርብ ንግግራችውን የጀመሩ ሲሆን: በንግግራቸውም ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ ላም ግን ድምጽ #ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች። #ኢህአዴግም እንዲሁ ብዙ ሳያወራ ብዙ ልማት ወደማምጣት የሚሽጋገርበት ጉባኤ እንደሚሆና በስኬትም እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️Miss Grand Ethiopia 2018 #ሳምራዊት_አዝመራው ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ማይናማር ከተማ ዛሬ ለሊቱን ትበራለች። በቻናላችን ስም መልካም ዕድል እንመኝላታለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኖቤል 2018⬇️

የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ነገ ረፍድ ይፋ ይደረጋል። ምርጫውን የሚያከናውነው 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ የዘንድሮ የኖቤል #የሰላም_ሽልማት ዕጩዎች ቁጥር 331 መሆኑን አሳውቋል።

ከእነዚህም መካከል 216 ግለሰቦች ሲሆኑ 115ቱ ደግሞ ቡድኖች መሆናቸውን ኮሚቴው ጠቁሟል።

በኖቤል ሽልማት አሰራር መሰረት ዕጩዎች ለህዝብ ይፋ የሚደረጉት ከ50 ዓመታት በኋላ ነው።

ዕጩዎቹ እነማን እንደሆኑ ባይታወቅም በርካቶች የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት ማን ሊያሸንፍ እንደሚችል የራሳቸውን ግምት እየሰጡ ይገኛሉ።

የሁለቱ ኮሪያ መሪዎች የአሸናፊነቱ ቅደሚያ ግምት ከተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል። የሰሜን ኮሪያው መሪ በሰብዓዊ መብት አያያዘቸው በተደጋጋሚ ቢወቀሱም ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ጋር በመሆን በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየውን ውጥረት ለማርገብ የወሰዷቸው እርምጃዎች የሽልማቱ ተመራጭ ያደርጋቸዋል የሚሉት በርካቶች ናቸው።

ሌላው ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው መሪዎች መካከል እንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

ትራምፕ በኮሪያ ባህረሰላጤ ሰላም ለማስፈን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ኒኩለር ቦንም ከማበልጸግ እንድተቆጠብ ላደረጉ ያላሰለሰ ጥረት ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሏል።

የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል እስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ይገኙበታል።

የሳውዲ ዜግነት ያለው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ ፣ ''የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም እስልምናን ዘልፏል'' በሚል ክስ ላለፉት 6 ዓመታት በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ይገኛል።

በስፔን መንግሥት ሕጋዊ እውቅና ባልነበረው ሕዝበ ውሳኔ ካታላኖች በካርለስ ፑይግዴሞንት እየተመሩ ከስፔን ተገንጥለው ሃገር ለመመስረት ሙከራ አድርገው ነበር። ሕዝበ ውሳኔውን ተከትሎም ካርለስ ከስፔን ሸሽተው በቤልጅም እየኖሩ ይገኛሉ።

ከግለሰቦቹ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሽልማቱን ሊያሸንፍ ይችላል ከተባሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ
ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር #ዐብይ_አህመድስ ከዕጩዎቹ መካከል እንዱ ሊሆኑ አይችሉም?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኖቤል ሽልማት እንዲያገኙም ጭምር ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኖቤልን የሰላም ሽልማትን የጊዜ ሰሌዳ ስንመለከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ነገርን አጠያያቂ ያደርገዋል።

የኖቤል ኮሚቴ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ነው፦

🔹መስከረም፡- በፈረንጆች መስከረም (ሴፕቴምበር) የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ እጩዎችን ለመቀበል ይሰናዳል። እጩ የመቀበሉ ሥራ ለቀጣይ ስድስት ወራት ይጸናል። እጮዎቹን መጠቆም የሚችሉት ከላይ የተዘረዘሩት ብቁ ጠቋሚ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ናቸው።

🔹የካቲት፡- በየካቲት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ያበቃል። ከየካቲት 1 በፊት ያልተጠቆመ በዚያ ዓመት እጩ መሆን አይችልም።

🔹መጋቢት፡-ኮሚቴው የእጮዎችን ዝርዝር ያቀርባል። ከእጮዎቹ ውስጥ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑትን ብቻ ለተጨማሪ ማጣሪያ ይቀርባሉ።

🔹ጥቅምት፦ በጥቅምት መጀመርያ ኮሚቴው አሸናፊውን በድምጽ ብልጫ ይመርጣል። ይግባኝ የማይባልበት ምርጫ ነው ታዲያ።

🔹በታኀሳስ፦ 10 (በፈረንጆቹ) በኦስሎ ኖርዌይ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል።

የኖቤል ሽልማት ከአንድ ዓመት ዘለግ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሂደት ነው። ኾኖም ጥቆማ የመቀበያ ጊዜ ከፈረንጆች መስከረም ጀምሮ ለ6 ወራት የሚዘልቅ ነው። ይህ እንግዲህ መጪውን የመስከረም ወር ሳይሆን የ2017ቱን ወር አንድ ብሎ የሚጀምር ነው።

የእጩ መስኮቱ ከተዘጋ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ ቢያንስ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ዐድል ጠባብ ያደርገዋል። ምናልባት የኖቤል ኮሚቴው በመጨረሻዎቹ ጊዜያት እጩ የመጨመር ሥልጣን ስላለው ያ ተግባራዊ ከሆነ
ጠባብ እጩ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቀላሉ ነገር መንግስትን #መጣል ነው፤ ከባዱ ነገር ሀገር #መገንባት ነው!

አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ASTU⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል።
25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች📌የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የመግቢያ ቀንን በደጋሚ እያራዘሙ በመሆኑ በዩኒቨርስቲዎቻችሁ ድረ ገፅ እና የፌስቡክ ገፅ ላይ አዳዲስ ማስታወቂያዎችን እድትከታተሉ።

▪️ምንም የጥሪ ለውጥ ያላደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ካሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተቋማችሁ ለመግባት ዝግጅት አድርጉ!
@tsegabwolde @tikvahthiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ቀን መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia