TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬇️

ፖሊስ በቡራዩ ከተማና አካባቢው ከተፈጸመው ወንጀል ጋር በተያያዘ የተለያዩ #መረጃዎችን መያዙን ገለጸ።

በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል በማስተባበር፣ በማነሳሳት፣ ገንዘብ በማከፋፋል እና በመኪና በመሸኘት የተጠረጠሩ እነ #ሳምሶን_ጥላሁን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ ሃሰተኛ መታወቂያ፣ የመንግስት መሃተምና ቲተር እንዲሁም በቤት ውስጥ 74 #ገጀራና ቢላ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩት ሳምሶን ጥላሁን፣ አለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሃሺም አሚር፣ ሽፈራሁ ኢራና እና አሊ ዳንኤል አስተያየት እና መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራን አዳምጧል።

መርመሪ ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለ ጀምሮ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ባንኮች የገንዘብ ዝውውሩን እንዲገለጽ ደብዳቤ መላኩን ገልጿል።

1ኛ ተጠርጣሪ ሳምሶን ጥላሁን የነዋሪዎችን መሬት #በመቀማትና ለሌለች አሳልፎ በመስጠት ግጭት አንዲፈጠር ማድረጉን ፖሊስ መረጃ እንዳለው ገልጿል።

የበርካታ ወጣቶች ፎቶና ሃሰተኛ መታወቂያ የመንግስት #መሃተምና ቲተር በተጠርጣሪው እጅ መገኘቱንም አስረድቷል።

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አቀባበል ድጋፍ በወጡ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ፓስተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሽጉጥ መተኮሱምን ነው ፖሊስ የገለጸው።

ሶስተኛ ተጠርጣሪም በቡራዩ በቤቱ ውስጥ ለወንጀሉ መፈጸሚያ የሚውል 74 ገጀራና ቢላ መያዙን የገለጸው። ፖሊስ የቀሩ ተጠርጣሪዎችም መስከረም 5 #በመንግስት_ተሽከርካሪዎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ማመላለሳቸውንና ገንዘብ ማከፋፈላቸውን ለችሎቱ አብራረቷል።

ለተጨማሪ መረጃ የሟቾችን አስከሬን ምርመራ ውጤት እና የተባባሪ ግብረሃይሎችን በቁጠጥር ስር ለማዋል የ28 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድቤቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ሳምሶን ጠበቃ በበኩላቸው ፖሊስ በተናጠል እና በዝርዝር የያንዳንዳቸውን ተሳትፎ አልገለጸም አሁን ሽብር ድርጊት ነው፣ የተባለውም ተጠርጣሪዎችን በእስር ለማቆየትና ዋስትና ለማስከልከል ነው፤ ፍርድ ቤቱ ይህን ከግምት አስገብቶ ዋስትና ይፍቀድና ክርክሩን በውጭ ሆነው ያካሂዱ ሲሉ ጠይቀዋል።

ተጠረጣሪዎቹ ሁሉም በተናጠል በአንደበታቸው ፖሊስ እያደረገው ያለው ምርመራ አኛን ለማሰር ነው ወንጀሉን አልፈጸምንም፣ አያያዛችንን በተመለከተ ከአይምሮ ህሙማን ጋር ታስረን #ስንሯሯጥ ነው የምናድር፣ ጨለማ ውስጥ ነው የታሰረነው ሰባዊ መብታቸን ይጠበቅ የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበው ምርመራ የሸብር ድርጊት መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን፥ ዋስትና አያሰጠም ሲል ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አከናውኖ እንዲቀርብ ለጥቅምት 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የተጠርጣሪዎችን ሰባዊ አያያዝ በተመለከተም የአዲስ አበባ ፖሊስም ሆነ ፌዴራል ፖሊስ ማስተካከያ አንዲያደረግ ትዛዝ ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል የተጠረጠሩ ከ250 በላይ ተጠርጣሪዎች ለዛሬ በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እየሰጡ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ፖሊስ እስካሁን በተሰጠው የ14 ቀን ጊዜ ከወንጀሉ ውስብስብና ሰፊ መሆን ጋር ተያይዞ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም የተጠርጣሪዎችን ቃል ተቀብሏል፤ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን የምስክርነት ቃል ለመቀበልና ዝርዝር ምርመራ ለማከናወን ተጨማሪ 14 ቀን ጊዜ ጠይቋል።

በዚህም የወረዳው ፍርድ ቤትም ለፖሊስ የስምንት ተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አንዱ #ብሄር ሌላውን መጣብኝ ካለ፣ #ውጣልኝ! #ሂድልኝ! ካለ፣ ይሄኛው የኢትዮጵያ ክፍል #የኔ እንጂ ያንተ አይደለም ካለ፣ ታዲያ ቅኝ ገዥዎችስ ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ!?"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በደቡብ ክልል ሸካና ከፋ ዞኖች የተከሰቱት #ግጭቶች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው አስቀድሞ መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር #ከሃዋሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በእነዚህ ቦታዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እና ግጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

በተለይም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ላይ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የገለፁት።

በእነዚህ ሶስት ዞኖች የዜጎች የመንቀሳቀስ እና ንብረት የማፍራት #መብት መገደቡን አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ ወደ ሶስቱም አካባቢዎች መርማሪዎችን ቢልክም ምርመራ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን እና መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ነው የተናገሩት።

የፀጥታ አካላትም ግጭቶቹን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ እየወሰዱ አለመሆናቸውን ከአካባቢዎቹ መርማሪዎች ለኮሚሽኑ በስልክ ያደረሱት መረጃ እንደሚጠቁምም ገልፀዋል።

አሁን ላይ በይፋ በግጭቶቹ #የሞቱ እና #የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርንም በዚህ ምክንያት በአግባቡ ማጣራት አለመቻሉን በማንሳት ይህም የችግሩን ስፋት እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ችግሩ በተፈጠረባቸው እነዚህ አካባቢዎች ገብቶ የማረጋጋት ፣ ህግ እና ስርዓትን እንዲሁም የዜጎችን መብት የማስከበር ስራ እንዲያከናውን ነው የጠየቁት።

እስካሁን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ግጭት ካለባቸው አምስት ወረዳዎች መካከል በሁለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመግባቱ የተሻለ ሁኔታ እየታየ መሆኑን ዶክተር አዲሱ አስታውቀዋል።

በእነዚህ መከላከያ በገባባቸው ቦታዎችም ኮሚሽኑ ከነገ ጀምሮ ምርመራ እንደሚጀመር ነው ያስታወቁት። ምርመራውንም በኃላፊነት መንፈስ ያከናውናል ብለዋል።

ዶክተር አዲሱ በመግለጫቸው በተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን መነሻ በማድረግ ችግሮቹ ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ለመከላከልና ሲከሰቱም በዘላቂነት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ኮሚሽኑ አድርጎ ለመንግስት ማቅረቡን አስታውቀዋል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነቀምት⬆️

"ሰላም ጸጋ፣ ዛሬ፣ የነቀምት ቡርቃ ጋሪ መካነ እየሱስ ቤተክርስትያን አገልጋዮች እና ወጣቶች፣ ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን እራት አብልተዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updateሀዋሳ የኢህአዴግ ጉባኤ⬇️

-የኢሕአዴግ ጉባዔ ለውጡን #በአዎንታዊነት የገመገመ መሆኑ ተገለጸ።

- መፈጸም የማይችሉ አመራሮችም ሆኑ የግንባሩ አባል ፓርቲዎች መቀጠል #የለባቸውም የሚል #ቀይ_መስመር ተለይቷል

▪️የኢሕአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የጥልቅ ተሃድሶ ያለበትን ደረጃና የመጀመሪያ ደረጃ ትሩፋቶችን በማድነቅ እየገመገመ መሆኑንና ቀጣይ የለውጡ አቅጣጫን በተመለከተ በመወያየት ላይ እንደሚገኝ የጉባዔው ቃል አቀባይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡

በተለይም ኢሕአዴግ የአመራር ለውጥ ከማድረጉ በፊት ራሱ ግንባሩና አገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደነበሩ፣ በአገሪቱም #የመበተን አደጋ ተጋርጦ እንደነበር መገምገሙን አክለዋል፡፡
የአመራር ለውጥ ከተደረገ በኋላ ግን ብዝሃነትን፣ #ኢትዮጵያዊነትንና በማኅበረሰቡ ላይ ተስፋን የሚጭሩ የፖለቲካ ተግባራት መፈጸማቸውን፣ ይህም በአገሪቱ የፖለቲካ መረጋጋት መፍጠሩ በጉባዔው እንደተገመገመ ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ጉዳይ ላይ ግምገማው እንደቀጠለ የወደፊት የፖለቲካ ሪፎርሙ አቅጣጫ ተቋማዊ መልክ እንዲይዝና በግምባሩ አባል ድርጅቶችና አመራሮች መካከል መልካም ግንኙነትና የዓላማ አንድነት መፍጠር የጸጸት ዶሴውን መዝጋት፣ በይቅርታና ቅን ልቦና ወደፊት መሄድ እንደሚገባ መገምገሙንና ውይይቱም መቀጠሉን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

በመደመር ፍልስፍና ላይ ግልጽነት የፈጠረ ውይይት መደረጉንና የማይታለፉ ቀይ መስመሮችን በተመለከተ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከቀይ መስመሮቹ መካከል መፈጸም የማይችሉ አመራሮችም ሆኑ የግንባሩ አባል ፓርቲዎች እንደማይቀጥሉ፣ ሥርዓት
አልበኝነትን አለመታገስ እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በጉባዔው ላይ የተነሱ የልዩነት ሐሳቦችን ሳይጠቅሱ ያለፉ ሲሆን፣ ከጋዜጠኞች ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን #እንደማይቀበሉ በመግለጽ መግለጫውን አጠናቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቲ⬆️መስከረም 29 እና 30 እንደነበር የተገለፀው የ2011 ዓ.ም ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ምንጭ፦ የዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው ሁሉ⬆️

"እኛ አመልካቾች በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ቀበሌ 06/07 በቤት ቁጥር 737, 738, 739, 741 ልዩ ቦታው ቤላና ፈረንሳይ መገንጠያ(ቀድሞ 11ቀበሌ የአሁኑ የፌዴራል ካምፕ ፌት ለፊት) እስከ1983 ዓ.ም ድረስ ስንጠቀምበት የነበረውን የጋራ መጠቀሚያ ሽንት ቤት እና ማዕድ ቤት እንዲሁም መተላለፊያችንን መንገድ በማጥበብ የሬሳ ማውጫ እንኳን በማሳጣት በቦታው የቀድሞ የቤቱ ባለቤቶች በላያችን ላይ ሌላ ቤት ሰርተው እየተጠቀሙበት ይገኛል። የሚገርመው እነዚህ ቤቶች በ G.I.S ላይ እንደሌሉ እና የኛ የቀድሞው የጋራ መጠቀሚያንና ባዶ ቦታን ነው የሚያሳየው። ይህንን ችግራችንን ለረጅም አመታት ለወረዳ 03 እና ለየካ/ክ/ከ ብናመለክትም መጥተው ከማየትና ከንፈር ከመምጠጥ በስተቀር ምንም አይነት መፍትሔ አላገኘንም። ብሎም ቅሬታችንን ለከንቲባ ለህዝብ ቅሬታ አመልክተን በስልክ እና በደብዳቤ በ15 ቀን ውስጥ መፍትሔ ሰጥታቹ አሳውቁን ቢባሉም ይሄው አመታትን አስቆጠርን። በ21ኛው ክፍለ ዘመን መሀል ከተማ ተቀምጠን በፖፖ እየተጠቀሙ አስፓልት ዳር እየተደፋ ለአካባቢው ሰው እና ለሕፃናት ችግር እየፈጠረብን ይገኛል። እንዲሁም የአካባቢው ሕፃናት ለተለያዩ በሽታዎች እየተዳረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖብናል። ስለዚህ የሚመለከተው አካል ቦታው መጥታቹ በማየት መፍትሔን እንድታሰጡን ስንል በትህትና እናመለክታለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዩጋንዳ #የመብረቅ አደጋ ደርሶ የሶስት ተማሪዎች ህይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው በሰሜን ምዕራብ ዮምብ ግዛት ነው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬆️

የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬው ምሽት በሃዋሳ ከተማ ለሚገኙና በኢህአዴግ 11ኛው ጉባኤ ላይ ለታደሙ ጉባኤተኞች እና ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ለመጡ እንግዶች የእራት #ግብዣ አደረጉ።

በእራት ግብዣው ላይ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለጉባኤው ስኬት ምርቃትና ጸሎት ያደረጉ ሲሆን የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብም ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የውጭ ዝርያ ያላት ከ40-60 ሊትር መታለብ የምትችል የ7ወራት ጊደር በስጦታ አበርክተዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩም ምስጋና በማቅርብ ንግግራችውን የጀመሩ ሲሆን: በንግግራቸውም ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ ላም ግን ድምጽ #ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች። #ኢህአዴግም እንዲሁ ብዙ ሳያወራ ብዙ ልማት ወደማምጣት የሚሽጋገርበት ጉባኤ እንደሚሆና በስኬትም እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia