TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጎንደር⬆️

"ሰላም ፀግሽ የአርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር የስብሰባ አዳራሽ ከህዝቡ ጋር ጠንከር ያለ ውይይይት አድርጓል። ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ከህዝቡ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ፀግሽ ፍፁም ኢትዮጲያዊነት የነገሰበት ልዩ ፍቅር ከጎንደር ህዝቦች ለ ግ-7 ለጋዜጠኛ ነኣምን ዘለቀ ለጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተወልድ ለነፃነት ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ እና ለመላው የንቅናቄው አባላት ልዩ ምስጋና አቅርቦአል። አንድ የጎንደር ነዋሪ ለጋዜጠኛ ነኣምን ዘለቀ የጣት ወርቁን አውልቆ ሲለግስ የተመለከተ የንቅናቄው ደጋፊ jaguar የእጂ ሰአቱን አውልቆ ለነዋሪው ስጦታ ሰጦኣል ይህም ድባቡ ፍፁም ፍቅርን የተላበሰ ነበር።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመድሀኒአለም⬆️

"ፊላንስ መድሀኒአለም አካባቢ ያሉ ወጣቶች ነዋሪዎቹን በማስተባበር የምግብና የአልባሳት ድጋፍ እያሰባሰቡ ነዉ።" (12:00)
.
.
በአሁን ሰዓት የእራት ማብላት ስነ ስ ርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዋሽ⬆️

"የኦነግ ሰራዊት አዋሽን ተሻግሯል፥ የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ የመደመር ጥሪን ተከትሎ ወደ አገሩ በመመለስ ላይ የሚገኘው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር/ ኦነግ ሰራዊት ዛሬ ከሰአት ላይ አፋር ክልል አዋሽ7 ከተማ ሲደርስ በከተማው ህዝብና መንግስት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በከተማ መስተዳድሩም ምሳ ግብዣ ተደርጎላቸው 10:30 ወደ አዳማ ተሸኝተዋል። መልካም የመደመር ጉዞ! S ነኝ ከ Awash7"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ📌አሁንም አካባቢያችን ላይ ስጋት አለ የምትሉ ችግሩ ሳይመጣ እና ስርሳይሰድ በፍጠነት ለፖሊስ ጥቆማ አድርሱ።

የፌደራል ፖሊስ #አመራር ስልኮች ናቸው፦
09-44-70-37-45
09-12-33-72-00
09-44-05-46-80
09-11-60-80-24

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ፦
011 416 6711
011 416 6722
011 416 6715

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፦
+251115521355

ነፃ፦ 991

ሌላው የፀጥታ አካላት ምላሻቸው ፈጣን ሊሆን ይገባል። ትላንት የፀጥታ አካላት ፈጣን እርምጃ ባለመውሰዳቸው ብዙ ሰዎች በየአካባቢው ተጎድተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትናትናው ዕለት በቡራዩ አሸዋ ሜዳ፣ ከታ እና ፊሊ ዶሮ አካባቢው #በንፁሀን ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ አወገዙ።

ጥቃቱ በዜጎች አንድነት ላይ የተቃጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ይህን ጥቃት ባደረሱ አካላት ላይ አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ድርጊቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪዎች ተጣርቶ ለህግ እንድሚቅርቡና ተመጣጣኝ ቅጣት እንድሚያገኙም ገልጸዋል።

የጸጥታ አካላትም ጉዳዩን በአስችኳይ እንዲያጣሩና ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አመራር ሰጥተዋል።

ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸው ለቤተሰቦቻቸው #መጽናናትን ተመኝተዋል።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እደግመዋለሁ‼️በየዋህናት ወይም ባለማውቅ እንዲሁም ሆን ብለው ለጥፋት እየተንቀሳቅሱ ያሉ ህዝቡን ለእርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ ሁሉም ማለት ይቻላል ምንም ችግር የሌለባቸው ቦታዎች የሚኖሩ፤ አንዳንዶቹም ውጭ የሚኖሩ የሀገር ሰላምን የማይፈልጉ፤ ዝም ሲል የሚቃጠሉ ብዙዎች አሉና በአስቸኳይ ከፌስቡክ ራቁ‼️

📌ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ....ሳትባባሉ አንድነታቹን አጠንክሩ።

📌ወላጆች ልጆቻችሁን ሰብስቡ፣ አባቶች ምከሩ፣ እናቶች ገስፁ፣ የሀይማኖት አባቶች ተግታችሁ ህዝቡ ስለ ሰውነት አስተምሩ፣ አክቲቪስቶች አስተምሩ፣ በየአካባቢው የምትኖሩ ወንጀለኞችን አሳልፋችሁ ስጡ!

‼️መንግስት #ጠበቅ ያለ እርምጃ ይውሰድ‼️

ኢትዮጵያ ትንገዳገድ ይሆናል እንጂ፤ በፍፁም #አትወድቅም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዊንጌት⬇️

"ሀይ S F እባላለው ከዊንጌት ከጠሮ መስጂድ ነው የማወራህ የሂሻ ሰላት ከሰገድ በኃላ የመስጂዱ ኮሚቴ ለተፋናቀሉ ህብረተሰብ የሚለበሱ ብርድልብሶችና ሌሎች አልባሳትን አሰባስቦ ወስዶላቸዋል።"

@tsegabwolde @tikahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ በአዲስ አበባ ዙሪያ #የጸጥታ አካላት ጉዳዩን በአስችኳይ እንዲያጣሩና ተገቢውን ህጋዊ #እርምጃ እንዲወስዱ #አመራር ሰጥተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዳማ የኦነግ(ABO) ወታደሮች ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የአዳማ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው አቀባበል አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethioipia
#update በአዳማ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ምልኩ የኦነግ(ABO) ወታደሮች ደማቅ #አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ፖሊስ #ፍትህን ለማሰከበር የቆመ ባለሙያ ነው፡፡ ፖሊስ ስለፖለቲካ #አይመለከተውም፡፡ የምርጦች
ስብስብ መሆን አለበት›› ዶክተር ኮማንደር ደመላሽ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ ለሁሉም ሰው ይድረስ!

ፊሊጶስ፤ ሚኪሊላንድ፤ ቃሌ እና ብስራት ትምህርት ቤቶች የተጠለሉ ቁጥራቸው 9740 (ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ አርባ) ዜጎች በቂ ራት አግኝተዋል። ችግሩ መኝታ ነው። ቀዝቃዛ ሲሚንቶ ላይ ነው የተኙት። በቻላችሁት አቅም ካርቶንም ቢሆን የኮልፌ እና አስኮ አካባቢ ነዋሪዎች በፍጥነት አምጡልን።

ከገፈርሳ የተፈናቀሉ ዜጎቻችን መድሐኔአለም ትምህርት ቤት ደርሰዋል። ራት አልበሉም። ተጨማሪ 5 ቦታዎች መድረስ አልቻልም።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ምንም በቂ ጥበቃ ሊያደርግ አልቻለም። ከ1 ሰዓት በፊት ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ቶክስ ነበር። ተጨማሪ ኃይል መጥቶ ትምህርት ቤቶቹን በአግባቡ መረከብ አለበት።

የአዲስ አበባ በተለይም የኮልፌ የሚኪሊላንድ እና የአስኮ ወጣቶች ፖሊስንም መንግስትንም ተክተው በርትተው ወገኖቻችንን እያገዙ ነው።

የህጻናት ምግቦች እና ዳይፐር እጥረት አሁንም መፍታት አልቻልንም።

ድረሱልን!!

©Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
📌ጥቆማ ለፖሊስ

ጀሞ 3 ከምሽቱ ከ1:30 ጀምሮ ችግር ተፈጥሮ ነበር ልክ እንደሌሎቹ ቦታዎች አሁን ላይ ረገብ ያለ ቢመስልም ነዋሪዎች አስተማማኝ ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልዕክት📌የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው ወደ ከተማዋ የገቡትን ወገኖች ልክ እንደዛሬው ነገም አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዳትዘነጉ።

ተባብረን ከፈጣሪ ጋር ይህን ጊዜ እናልፈዋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia