TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሁን አዲስ አበባ⬆️ነገ በአዲስ አበባ የሚጠበቀው የኦነግ አቀባበል ካለምንም #ችግር እንዲጠናቀቅ በከተማ ደረጃ ምን ያህል በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን፣ ከፀጥታና ደህንነት፣ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ ተሳደብ፣ ቀስቅስ፣ ሰዎችን አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው ተባላ ...ነገ ሀገር #ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ የምትበላው ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት #ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።
.
.
ዛሬማ ሰላም ነው #ፎክር እንጂ...የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ ህፃናት #ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ...የዛሬዋን ቀን #ትረግማታለህ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።

.
.
ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር...አቅራራ...ህዝብ ቀስቅስ...ተነሳ በለው፣ ግደለው በል!
.
.
የለኮስከው #እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን #ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ!

#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
❗️ዛሬ እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም❗️

እናንተ ግጭትን ለማብረድ ከመሞከር ይልቅ በተነሳው እሳት ላይ ቤንዚን እየጨመራችሁ ያላችሁ ግብዞች ሆይ!!

ይህ እውነት የተፃፈው ለእናንተ ነው፡፡ በዚህ ርኩሰት ተግባር ከቀጠላችሁ…

እንዲመጣ እየወተወታችሁት ያላችሁት ክፉ ቀን ቢመጣ እንዲህ እንዳሁኑ ፌስቡክ ላይ ተጥዳችሁ #መዘብዘብ አይታሰብም። ያኔ ምኞታችሁ ዛሬን በህይወት መክረም ብቻ ይሆናል።

ያኔ አይደለም እንደልባችሁ #ወጥታችሁ መግባት ይቅርና ሱቅ ደርሶ መመለስ ቅንጦት ሊሆንባችሁ ይችላል፡፡ ምክንያቱም እንዲነድ ያቀጣጠላችሁት እሳት ወላፈን. .. ከቤታችሁ ወጣ እንዳላችሁ ሊበላችሁ ይችላል። ለነገሩ እያቀጣጠላችሁት ያለው እሳት.....ከቤታችሁም ሆናችሁ ከሰል አድርጎ ሊያስቀራችሁ ይችላል።

ያኔ ሀገሪቱ በትናንሽ ባለጠመንጃ መንግስታት የምትመራ ስለምትሆን እንደልብ የምትተቹት መንግስት አይኖራችሁም። ይህ ነገር አሁን አይገባችሁም።

እናንተን ምናልባት የሚገባችሁ…⬇️

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት በመድሃኒትና በምግብ እጦት #ሲያልቁ ያዩ እናቶች... ልጆቻቸውን ለማትረፍ ወደ ስደት በሚያደርጉት ጉዞ የአውሬና የሽፍታ ሲሳይ ሆነው ሲቀሩ ያኔ ይገባችኋል።

አስፓልቶች በታንክ ታርሰው..... ከተማይቱ በህንፃ ፍርስራሽ ተሞልታ በዘሩ ምክንያት በየቀኑ በየጎዳናው የሞተው ቀባሪ ያጣ አስከሬን ሽታው አገሩን ሲሞላው ያኔ ይገባችሁ ይሆናል።

እመኑኝ ....ዛሬ ላይ ለተፋችኋት እያንዳንዷ #ብጥብጥ ቀስቃሽ መልእክታችሁ መፈጠራችሁን #እስክትረግሙ ዋጋ ትከፍልባታላችሁ። ለኃጥዓን የወረደው ለፃድቃን ይተርፋል እንደሚለው ቅዱስ መፅሃፉ ዳፋችሁ ለሁሉም ሲሆን ያኔ ይገባችሁ ይሆናል ።

ያ እንዲመጣ የምትፈልጉት ቀን ሲመጣ. .. #ክልላችሁ ወይም #ከተማችሁ አያድናችሁም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የላካቸው ሰላም አስከባሪ #ወታደሮችም ከመጣባችሁ መዓት ፈፅሞ ሊያስጥሏችሁ አይችሉም ።

ምናለፋችሁ ዛሬ እንደዋዛ #እያቀጣጠላችሁት ያላችሁት እሳት ለጎረቤት ሃገራትም ይተርፋልና ክልሌ መሸሸጊያዬ ብላችሁ #እንዳታስቡ

ዛሬ በሀገር ሰላም በድንገት በህዝቦች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶችን ላጋጋላችሁበት አንድ ቀን #በቁጭት እና #ፀፀት የደም እምባ እያነባችሁ በህይወታችሁ ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ፡፡

አሁን እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም፡፡ ስለዚህ ያች እንድትመጣ እየጠራችኋት ያለችው ቀን ሳትመጣ፣ በዚች በመልካሟ በዛሬዋ ቀን ላይ ሳላችሁ ምርጫ አላችሁና አስቡበት።

ልቦና ይስጠን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ጠብቅልን!

©ቂርቆስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ኃይል የከተማ አስተዳደሩ #አይታገስም" – ኢ/ር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ አስጠነቀቀ⬇️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ሚስማር የተተከለበትን ዱላ የያዘ አንድም ሰው #እንዳልመለከት ብሏል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በመዲናዋ የተከሰተውን አለመግባባት በተመለከተ ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራሁ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በህዝብ መገልገያ ንብረት፣ በመናፈሻዎች፣ በግንቦች፣ በአውቶብስ መጠበቂያዎች እና በአጠቃላይ ባንዲራ መቀባት #ፈፅሞ የተከለከለ እንደሆነ ፖሊስ ኮሚሽኑ ለሸገር ተናግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ሚስማር የተተከለበትን ዱላ የያዙ ግለሰቦችን እንደተመለከተና #እርምጃ እንደተወሰደ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በኋላም ፖሊስ ኮሚሽኑ አላስፈላጊ የሆኑ ድርጊቶችን ከተመለከተ ፖሊሳዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል፡፡

የዲፕሎማት መቀመጫ ትልልቅ ጉባኤዎች የሚሰሙባት እና የአፍሪካ መዲና ለሆነችው አዲስ አበባ ደረጃዋን የጠበቀ ሰላምና ፀጥታ እንዲፈጠር ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራ እንደሆነ ለሸገር ተናግሯል፡፡

©Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር ታከለ ኡማ⬆️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ለወጣቱ ጥሪ አቀረቡ።

በሂልተን ሆቴል ተገኝተው ከሁለቱ አስተባባሪ ወጣቶች(የአግ 7 እና ኦነግ) ጋር ውይይትና ምክር የሰጡት ከንቲባ ታከለ በከተማዋ የሚታየው ተግባር የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ ሀይሎች እንዳሉ መንግስት #ጠንቅቆ ያውቃል በመሆኑም ይህንን የከተማው አስተዳደር #እንደማይታገስና ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የሁላችን ሀገር ለሁላችን የምትበቃ በመሆኗ በግለሰብ ፣ በቡድን እና በፓርቲ ደረጃ የሚመጡ እንግዶችን በጨዋነት መልኩ ተቀብለን ማስተናገድ አለብን ለዚህም ወጣቶች ሀላፊነታቸውን ተወጡ ብለዋል።

©አሀዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

#ቄሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ #ወጣቶች ተወካዪች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወጣቶቹ ከም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰንደቅ አላማን ምክንያት በማድረግ የተፈጠረውን አላስፈላጊ ግጭት #አውግዘዋል

ነገ የሚደረገው አቀባበል በሰላማዊ እና በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን በትብብር ለመስራት #መስማማታቸውንም ገልፀዋል።

©አሀዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvaethiopia
ከባህር ዳር⬆️

"ፀግሽ አሁን ባህር ዳር አየር ማረፊያ ነው። የግንቦት7 አመራርን ለመቀበል እየጠበቅን ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#udate ትላንት ኢንሴኖ ላይ የነበረው ውጥረት ወደ ቡታጀራ ከተማ ተሻግሮ ዛሬ የንግድ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ ውሏል። የፀጥታ አስከባሪዎች ሁኔታውን ለመቆጣጠር ወደ ከተሞቹ የገቡ ሲሆን ነዋሪው የፀጥታ ሀይሉ ይበልጥ ሊጨመር ይገባል ሲል መልዕክታቸውን ልከዋል።

📌በዚህ አጋጣሚ ወጣቶች ከስሜታዊነት ወጥተው የሀገርን ሰላም ሊያስጠብቁ ይገባል። የሀይማኖት አባቶችም ወጣቱን ሊመክሩት ይገባል።

ከክልሉ መንግስት የሚሰማውን ተከታትዬ አደርሳችኋለሁ።
@tsegabwolde @tikvajethiopia
#update አብዲ ኢሌ⬇️

ፖሊስ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር #አብዲ_መሐመድ ጨምሮ በሌሎች ተከሳሾች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ 14 ቀን የምርምራ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ተፈቀደለት።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ጨምሮ የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት 19ኛ ተረኛ ምድብ ችሎት በተጠርጣሪዎች የቀረቡትን አቤቱታ ሰምቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እይጠየቀን አይደለም ምግብና ህክምናም በአግባቡ እያገኘን አይደለም የሚል #ቅሬታ በጠበቆቻቸው በኩል እቅርበዋል።

መዝገቡ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ የያዘ ነው እንደኃላፊነታችን መጠን ሊለያይ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። የዋስትና መብታቸውም እንዲከበር እንዲሁ። ፍርድቤቱ የቀረቡት ጉዳዮችን በተመለከተ ፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት ስለማየሰጣቸው ይህን ጥያቄ #ውድቅ በማድርግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በመሆኑም ቀጣይ የቀጠሮ ጊዜ መስከረም 18 እንደሚሆን ፍርድቤቱ ወስኗል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ⬆️የተሻሻለው የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#udate ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ⬇️

ሰሞኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በአርማ እየተመካኘ እየተፈጠረ ያለው አምባጓሮ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራቱ በፊት መንግሥት #አፋጣኝ #እርምጃ እንዲወስድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠየቁ።

ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ "ትናንት አስከፊውን አገዛዝ ከጫንቃችን አሽቀንጥረን ለመጣል ያደረግነው ብርቱ ተጋድሎ በጎመራ ማግሥት የለውጡን ሂደት መደገፍና አገሪቱን እንደ አገር የማስቀጠሉ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ሲገባ በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ የሚታዩት ግጭቶችና ሥርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው እሰጣገባ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል። ቢዚህም ሳቢያ በተፈጠረ ፉክክር "ትውልዱን ለግጭት ማነሳሳት ፍፁም ሊወገዝ የሚገባው እኩይ ተግባር ነው" ሲሉ አውግዘዋል።

ኦፌኮና ሰማያዊ በመግለጫቸው ላይ ጨምረውም "እያንዳንዳችን ፍላጎታችንንና ድጋፋችንን ለምንሻው አካል እየሰጠን አንዳችን የአንዳችንን ሃሳብም ሆነ መልካም ድርጊትን እያከበርን የተጀመረውን ለውጥና ሽግግር መደገፍ ወሳኝ ነው" ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በአርማ እየተመካኘ የሚፈጠር አምባጓሮ ባስቸኳይ እንዲቆምና ወጣቱ ትውልድ በፍቅርና በመቻቻል ዘመኑን እንዲዋጅ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአባገዳ መሪዎች ወጣቶችን #እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን! #ቄሮዎች በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንግዶች በመኪና እየዞሩ እነዚህን መፈክሮች እያሰሙ ይገኛሉ...⬇️

እኛ ኢትዮጵያን እንወዳታለን!
#ዘረኝነትን እንጠላለን!
#ጥላቻን እንጠላለን!
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እንወዳችኋለን!
.
.
እኛ አማራን እንወዳለን!
እኛ ደቡብን እንወዳለን!
እኛ ትግራይን እንወዳለን!
እኛ ጉራጌን እንወዳለን!
እኛ ሱማሌን እንወዳለን!
.
.
እኛ ዘረኛ አይደለንም!
ለብዙ ዘመናት ዘረኛ ተብለናል እኛ ግን ዘረኛ አይደለንም!
እኛ የመጣነው ኦነግን ለመቀበል ብቻ አይደለም፤ እኛ የመጣነው #ፍቅርም ልናስተምር ነው!
ኢትዮጵያ #እናታችን ናት!
.
.
እኛ አሸባሪዎች አይደለንም!
እኛ ሀገር #አናፈርስም!
እኛ ኢትዮጵያን እንወዳታለን!
ኢትዮጵያ እናታችን ናት!
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች #እንዳችኋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia