TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬም እደግመዋለሁ...ሰዎች #እናስተውል! ስለ ሀገር ክብር እና ስለ #ባንዲራ ክብር የምናወራው ሰላማዊ ሀገር #ሲኖረን ብቻ ነው። ከሌሎች ሀገራት ትምህርት መውሰድ ካልቻልን ነገ እኛም የነሱ ዕጣ ይደርሰናል። ዛሬ ቆም ብለን ካላስተዋልን ነገ እኛን እንኳ የሚቀብረን እናጣለን! ዛሬ በደንብ ካላሰብን ለታሪክ ነጋሪ እንኳን በዚህች ምድር ሰው አይኖርም።
.
.
ተው ግን ፈጣሪን ክፉኛ አናስቀይመው፤ የለመነውን ምንም ሳይሰስት እየሰጠን እኛ ግን ያለንን ባለማወቃችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እያመራን ነው።
.
.
በምታምኑት አምላክ ስም መሬት ላይ ተደፍቼ ልማፀናችሁ የቴሌግራም እና የፌስቡክ አርበኞች #ለምስኪን ህፃናት ህይወት ብላችሁ ህዝብን ለጥፋት ከመቀስቀስ ተቆጠቡ! በምታምኑት አምላክ ይሁንባችሁ ነገሮችን እያጋነናችሁ ህዝቡን ለጥፋት አትገፋፉት! ለምስኪን ህፃናት ቀጣይ ህይወት ብላችሁ አደብ ግዙ!

ፍቅር ይሻለናል!
አንድነት ይሻለናል!
ፈጣሪን መፍራት ይበጀናል!
ከስሜታዊነት መውጣት ይበጀናል!
እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ ከሚል ስሜት መውጣት ይበጀናል!

ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን!
#ETHIOPIA

ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ለሚገነቡ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች የግንባታ ማስጀመሪያ የመግባቢያ ስምምነት ከክልሎቹ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በትናንትናው ዕለት ፈርመዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከተመረቀ አንድ ወር ያልሞላው #የረጲ ሀይል ማመንጫ ስራ አቆመ። ከቆሻሻ ሀይል የሚያመነጨው ይህ ተቋም ከታቀደውና ከዲዛይኑ ሀይል የማምረት አቅም በግማሽ ያህል ብቻ መስራት ቢጀምርም አሁን ያላለቁ ስራዎችን ለማከናወን በሚል ስራ ማቆሙን ሪፖርተር ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢህአዴግ⬇️

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ #መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ ለfbc እንዳስታወቀው፥ ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተገመገሙና ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ ድርጅቱ ከመስከረም አጋማሽ በኃላ በሚካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚቀርብ ሪፖርት ላይም ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በወቅታዊ ድርጅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ነጥብ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ
-ወንድ 362
-ሴት 345

በህብረተሰብ ሳይንስ
-ወንድ 345
-ሴት 335

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች ከባንዲራ ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ግጭት አስመልክተው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ የሰጡት ማብራሪያ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦቦ ለማ መግርሳ⬇️

የአሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአዲስ አበባ በሰንደቅ አላማምክንያት የተፈጠረው ችግር መፈጠር #ያልነበረበት እና #መቆም ያለበት ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ መጋጨት በሌለብን ጥቃቅን ጉዳዮች ሊያጋጩን የሚፈልጉ አካላት በመኖራቸው ህብረተሰቡ #ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡

በመሆኑም ወደ ሀገርቤት የሚመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶቹን በምንቀበልበት ወቅት ያልተገባ ፉክክርና #ግጭት ውስጥ መግባት የለብንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ህብረተሰቡ የፈቀደውን ይህ ይሻለኛል ብሎ የወሰነውን ሰንደቅ አላማ መጠቀመም እንደሚችል ጠቅሰው የትኛውም አካል ግን በሌላው
ላይ የራሱን ሃሳብም ይሁን አርማ የሚጭንበት ወቅት ላይ አይደለንም ብለዋል፡፡

አቶ ለማ #ከስሜት ውስጥም በመውጣት የሀገራችንን አንድነት እና እድገት ለማስቀጠል በመቻቻል ልንረባረብ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የትኛውም አካል ሃሳቡን በነጻነት እንዲገልጽ የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ እና ይህንንም ተከትሎ በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር ቤት በመግባት ላይ እንደሚገኙ አስታውሰዋል።

©obn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የኢህአዴግ ምክር ቤት #መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል። ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተገመገሙና ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia