TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድሬዳዋ⬆️ለአርቲክስ እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በድሬዳዋ ከተማ ደማቅ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች የመጨረሻውን #የሰላም ስምምነት አዲስ አበባ ላይ ተፈራርመዋል። ተቀናቃኝ ሀይሎቹ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በተካሄደው 33ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ነው የሰላም ስምምነቱን የተፈራረሙት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትላንት በአንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት ምሽቱን ረግቦ ቢያድርም ዛሬ ከጥዋት አንስቶ ውጥረቱ ማገርሸቱን ለመታዘብ ተችሏል።

📌 የመንግስት ባለስልጣናት ና ታዋቂ ግለሰቦች ህዝቡን በማረጋጋት ይህን ችግር ሊፈቱት ይገባል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብአዴን⬇️

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የድርጅቱን #ስም እና #አርማ ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል።

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፥ ብአዴን ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ መሰረት በማድረግ የድርጅቱን ስም እና አርማ ሊቀይር ነው።

በዚህም መሰረት ድርጅቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ የምርጫ ስያሜዎች በአባላት ሙሉ ተሳትፎና ምርጫ በጉባኤ ውሳኔ ለመቀየር በሁሉም የድርጅቱ መዋቅሮች ለውይይት እንዲወርድ ተደርጓል ብሏል።

ለምርጫ የቀረቡት የቀረቡት ስሞች:-

1.የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አህዴፓ)

2.የአማራ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (አህዴአፓ)

3.የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ)

4.የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አህዴን) የሚሉ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁንም ጥንቃቄ📌 ከዝህ በፊት ብያለሁ። አሁንም ደግሜ እላለሁ! ከትናንሽ አጀንዳዎች እንዉጣ። ስለ ምልክት ሳይሆን ስለሀገር ከልብ እናስብ! #ሀገር ካለች #ባንዲራ መስቀል እና #ሀዉልት መገንባት አይከብድም! ሀገር #ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻዉን ትርጉም የለዉም! አሁን #ሊቢያ ወይም #የመን ላይ ባንዲራ መያዝ ወይም ሀዉልት መትከል ምን ያደርጋል? ችግራችን በባንዲራ ወይም በሀዉልት አይፈታም። የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ።

ጆሮ ያለዉ ይስማ!
.
.
Ammas of eeggannoo📌

Kanaan duras jedheera. Ammas irran deebi'a! Ajandaa xixinnoo keessaa haa baanu. Waan mallattoo dhiifnee waan biyyaa onnee irraa haa yaannu! Biyyi yoo jiraatte alaabaa fannisuu fi siidaa dhaabuun hin dhibu. Yoo biyyi hin jirre garuu alaabaan qophaatti hiika hin qabu! Amma #Liibiyaa ykn #Yemen keessatti alaabaaqabatuun ykn siidaa dhaabuun maal godha? Rakkoon keenya alaabaa ykn siidaan hin hiikkatu! Shira diinaa haa fashalsinu!

Dubbii kana qalbisaa!

©አቶ ታዬ ደንደአ (የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ⬆️በድሬዳዋ ከተማ ለአርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የተደረገው አቀባበል #በሰላም ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

©የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia