TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም‼️

በህገወጥ የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት የተሳተፉ ግለሰቦች ከነመሳሪያቸው #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ለEBC በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ለህገ ወጥ የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት ሲውሉ የነበሩ በአዲስ አበባ ከተማ 34፣ በጅማ ዞን 32 ሲም ቦክሶች ተይዘዋል፡፡

ሌሎች ለዚህ ተግባር የዋሉ መሳሪያዎች እንዲሁም በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሳተፉ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ለህገ ወጥ ዓላማ የዋሉ መሳሪያዎችና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ጥረት በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላትና ህብረተሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃትና በቅንጅት ተሳትፈዋል ብሏል መግለጫው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

“አባ ቶርቤ” በሚል መጠሪያ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድብቅ በመንቀሳቀስ ሰዎችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በዛሬው እለት ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ “አባ ቶርቤ” (ባለሳምንት) በሚል መጠሪያ በመደራጀት ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የፀጥታ ሀይሎችን #ሲገድሉ እና #ሲያስገድሉ ነበር በሚል ነው ተጠርረው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የተጠርጣሪዎቹን ማንነትና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰው ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኸርባል ኮልጌት የተባለ ተመሳስሎ የተሰራ መድሃኒት በህገወጥ መንገድ አምርቶ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ አንድ የኮስሞቲክስ ማምረቻ ባለቤት #በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ክትትል ሲያደርግና ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌዴራል የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት፣ ከኢንተር ፖል እና ከአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃ መሆኑን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አብርሃም ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሶማሌ ላንድ ተነስተው በቶጎጫሌ ወደ ጅግጅጋ ሲያመሩ የነበሩ ኮድ-04046፣ ኮድ-05759 ሁለት ቅጥቅጥ አይሱዙዎች እና ኮድ-39416 የጭነት ተሸከርካሪ ግምታዊ ዋጋቸዉ 550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፤ ምግብ ነክ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነዉ በህገወጥ መንገድ ወደ ጅግጅጋ ለመግባት ሲሞክሩ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች እንዲሁም በጉምሩክ ሰራተኞች ክትትል ታህሳስ 23/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 እስከ ምሽት 2 ሰዓት ባለዉ ጊዜ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ #ደመላሽ_ተሾመ አያይዘዉ እንደገለጹትም በድርጊቱ ተሳታፊ የነበረዉ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ዉሎ አስፈላጊዉ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዉ በቀጣይም ህብረተሰቡ ይሄን መሰል ድርጊቶች በንቃት በመከታተል ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Via~EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጋቦን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ #መክሸፉን ተከትሎ በርካታ ባለስልጣናት #በቁጥጥር ስር ዋሉ። የምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ጋቦን ወታደሮች በዛሬዉ ዕለት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን መቆጣጠራቸዉን ገልፀዉ ነበር። ወታደሮቹ ለጥቂት ሰዓታት ተቆጣጥረዉት በነበረዉ የሀገሪቱ የሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ እንደተናገሩት፣ መፈንቅለ መንSስቱን ያደረጉት ከጎርጎሮሳዉያኑ 2009 ዓ/ም ወዲህ በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ አምባገን አገዛዝ ለማብቃት እና በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ነበር። ይሁን እንጅ፣ ይኸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን የሀገሪቱ የጋቦ መንግስት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ገልጿል። ይህን ተከትሎም የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ እና ሌሎችአራት የጦር መኮንኖች በመዲናዋ ሊብረቪል በሚገኘው የሀገሪቱ ብሄራዊ የሬዲዮ ጣቢያ አጠገብ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ገልፀዋል። የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መህመትና የፈረንሳይ መንግስትn የመፈንቅለ መንግስቱን ሙከራ አዉግዘዉታል። የጋቦ ፕሬዚደንት ቦንጎ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በሞሮኮ ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን እንደደረሰበትና ከፈፃሚዎቹ ጥቂቶቹን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው እንደገለጹት፥ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተደርሶበታል።

በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ከተሳተፉት ውስጥም ጥቂቶቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸወን አስታውቀዋል።

የወንጀሉ ፈፃሚዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በተለያየ መንገድ በእጃቸው እንደሚያስገቡ የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው፥ የወንጀሉ ተሳታፊዎችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ዩንፎርም ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው የጎረቤት አገራትም የደንብ ልብሱ ለወንጀል መፈፀሚያነት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየሰሩ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችም በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በተያዘው ወር ለሚካሔዱት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።
ለዚህም ስኬት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ በማለት ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ #ሰባራ_ባቡር አካባቢ እንጀራ በመጋገር የሚተዳደሩ ግለሰቦች #ባእድ ነገር #በመቀላቀል ለአመታት ለምግብ ቤት በማከፋፈል የቆዩ ሲሆን በአካባቢው ህብረተሰብ ጥቆማ #በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮምዩኒኬሽ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በጅግጅጋና አካባቢው #ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው #ወንጀል ዙሪያ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች #በቁጥጥር ስር የሚውሉ አካለትም መኖራቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ከሀምሌ 28 እሰከ 30 በሶማሌ ክልል በጅግጅግናና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ በጋራ ሲያደርጉት የቆዩትን የምርመራ ስራ አጠናቀዋል።

ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሄርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ዙሪያ የድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት ተጨማሪ ትልልቅ ወንጀሎች እንደተገኙ የታወቀ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ተጨማሪ ግለሰቦች መኖራቸውም ታውቋል።

የምርመራው ውጤት በመጠናቀቁም በቁጥጥር ስር ያሉትን የክልሉን የቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ሌሎች አካላት ላይ ክስ መመስረቱ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

የምርመራ ሂደትንና ውጤቱን በተመለከተም አርብ (ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም) በጠቅላይ ቃቤ ህግ ለጋዜጠኞች #መግለጫ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነጭ ሳር🔝

በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት ተነስቶ የነበረው እሳት #በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ #ሽመልስ_ዘነበ እንደገለፁት #የሀገር_መከላከያ_ሠራዊት እና #የፖሊስ_አባለት ባደረጉት ጥረት የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ እሳቱ የተነሳው "አርፋይዴ" ተብሎ በሚታወቀው የፓርኩ ክፍል ሲሆን 1ሺህ ሄክታር ያህል መውደሙን አቶ ሽመልስ ገልፀዋል ፡፡ #ጂቲዜድ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር እንዲውል የቁሳቁስ አቅርቦት እና አስፈለገውን ወጪ መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ Gamo Zone Adminstration office public Relation unit
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬደዋ‼️

በድሬዳዋ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እንዲረከብ መደረጉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በሰሞኑ ሁከት የተጠረጠሩ 200 ሰዎች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ድሬዳዋ እንዲገባ የተደረገው ባለፉት ቀናት በከተማይቱ የነበረው ሁኔታ ከአስተዳደሩ እና ከፌደራል ፖሊስ አቅም በላይ ስለነበር ነው።

የመከላከያ ሰራዊት ከተማይቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ኮማንድ ፖስቶች በተለያዩ አካባቢዎች ማቋቁሙንም ጽህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።

የጀርመን ራድዮ የድሬዳዋ ዘጋቢ #መሳይ_ተክሉ እንደገለጸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በከተማይቱ ተሰማርተዋል። በመኪና ላይ ሆነው ከሚዘዋወሩት በተጨማሪ በየአካባቢው በተጠንቀቅ ቆመው የሚታዩ እንዳሉ ዘጋቢው ተናግሯል። የሰራዊቱ አባላት ለአደጋ ይጋለጣሉ ለተባሉ የመንግስት ተቋማት እና ድርጅቶችም #ጥበቃ እያደረጉ ነው ብሏል።

በከተማይቱ ያለው ዘጋቢያችን የመንግስት ወታደሮቹ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በድምጽ ማጉያ ሲያስጠንቅቁ ተመልክቷል። በድሬዳዋ ሰሞኑን ሲደረጉ የነበሩ የህዝቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከሚያውኩ ድርጊቶች እንዲታቀቡም ተቃዋሚዎችን ሲያስቡም ታዝቧል።

በድሬዳዋ ላለፉት ሶስት ቀናት ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ጎማዎች በማቃጠል እና ድንጋይ በመደርደር መንገዶችን ዘግተው ነበር። በዛሬው ዕለት በከተማይቱ እንቅስቃሴዎች እንደሚታዩ የገለጸው ዘጋቢያችን መንገዶች መከፈታቸውን እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ስራ መመለሳቸውን ተናግሯል።

በድሬዳዋ ከሰሞኑ በተከሰተው ሁከት ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተጠየቁት የከተማይቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እና ፖሊስ “የተደራጀ መረጃ የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ:- DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia