TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በስራ ሰዓት ስብሰባ⬆️

የየካ ክ/ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። የሚገርመው ደግሞ ቀኑ "02/10/2010" ማስታውቂያው የወጣው "02/01/2011" ነው።
.
.
ብዙ ሰው የሚያስተናግደውን አጥቶ እየተንገላታ ነው።

©ጥኡመ
@tsegabwolde
#update አዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች ያለውን ጉዳይ እየተከታተልኩ ነው። በተለይ ፓስተር አካባቢ ውጥረት እንደነበር ሰምቻለሁ። እንዲሁም የንግድ ተቋማት መዝጋታቸውን በስልክ ያናገሩኝ የቻናላችን አባላት ገልፀውልኛል።

📌ዝርዝር መረጃዎችን በተለይ ትክክለኛ መነሻውን እና ስለ ደረሱ ገዳቶች በቂ እና የተጣራ መረጃ ከቦታው እንደደረሰኝ የማቀርብ ይሆናል።

▪️በዚህ አጋጣሚ ወጣቶች ከስሜታዊነት በራቀ መልኩ #ችግሮች ካሉ #በመነጋገር እና #በመግባባት ሊፈቱት ይገባል ለማለት እወዳለሁ።
.
.
የመንግስት አካላት እና ታዋቂ አክቲቪስቶች ወጣቶችን በማረጋጋት ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

እመለሳለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️65ኛው የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል።

ፎቶ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁንም ጥንቃቄ📌 ከዝህ በፊት ብያለሁ። አሁንም ደግሜ እላለሁ! ከትናንሽ አጀንዳዎች እንዉጣ። ስለ ምልክት ሳይሆን ስለሀገር ከልብ እናስብ! #ሀገር ካለች #ባንዲራ መስቀል እና #ሀዉልት መገንባት አይከብድም! ሀገር #ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻዉን ትርጉም የለዉም! አሁን #ሊቢያ ወይም #የመን ላይ ባንዲራ መያዝ ወይም ሀዉልት መትከል ምን ያደርጋል? ችግራችን በባንዲራ ወይም በሀዉልት አይፈታም። የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ።

ጆሮ ያለዉ ይስማ!
.
.
Ammas of eeggannoo📌

Kanaan duras jedheera. Ammas irran deebi'a! Ajandaa xixinnoo keessaa haa baanu. Waan mallattoo dhiifnee waan biyyaa onnee irraa haa yaannu! Biyyi yoo jiraatte alaabaa fannisuu fi siidaa dhaabuun hin dhibu. Yoo biyyi hin jirre garuu alaabaan qophaatti hiika hin qabu! Amma #Liibiyaa ykn #Yemen keessatti alaabaaqabatuun ykn siidaa dhaabuun maal godha? Rakkoon keenya alaabaa ykn siidaan hin hiikkatu! Shira diinaa haa fashalsinu!

Dubbii kana qalbisaa!

©አቶ ታዬ ደንደአ (የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️መድሀኒአለም አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ውጥረቱን #ለማርገብ እና ህዝቡን #ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ፎቶ፦ አንተነህ እና Xo (TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

ዛሬ በአዲስ አበባ መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት አካባቢ ከምልክትና #ባንዲራ ቀለም ጋር በተያያዘ መጠነኛ ግጭት ተፈጥሯል፡፡

ቅዳሜ መስከረም 5/2011 ዓ.ም ወደ ሀገር የሚገቡትን የኦነግ አመራሮች ለመቀበል የተዘጋጁ ወጣቶች የአስፓልት ጠርዝን የሚደግፉት ድርጅት መለያ ቀለም በሚቀቡበት ወቅት ነበር ግጭቱ የተቀሰቀሰው፡፡

ድንጋይ መወራወሩ ያለማቋረጥ በመቀጠሉ ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን #አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ህዝብ ግንኙነት ታዬ ደንደአ ዛሬ በፌስ ቡክ ገጻቸው “ስለ ምልክት ሳይሆን ስለ ሀገር ከልብ እናስብ፤ ሀገር ካለች ባንዲራ መስቀል እና ሀውልት መገንባት አይከብድም፤ ሀገር ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻውን ትርጉም የለውም” ብለዋል፡፡

የግንቦት 7 ሊቀ መንበር ብርሀኑ ነጋ (ዶ/ር) ባለፈው እሁድ አዲስ አበባ ሲገቡ ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ልደቱ_አያሌው ስለቅንጅት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መፍረስ በግልጽ ከፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ ጋር ፊት ለፊት ቀርበው መወያየት እንደሚፈልጉ አስታወቁ፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት የ1997 ዓ.ም የምርጫ ሂደትና የቅንጅት መፍረስን አስመልክቶ #በግልጽ በሕዝብ ፊት አልያም በተናጠል ሕዝቡ ያውቀው ዘንድ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ፊት ለፊት ቀርበው መነጋገር እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር #አሚር_አማን የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር አሚር አማን⬇️

"የጅማ ዩንቨርስቲ የቦርድ #ሰብሳቢ በመሆን እንዳገለግል ለተሰጠኝ ዕድል እና ለተጣለብኝ ተጨማሪ #ሃላፊነት አመሰግናለሁ። ከዩንቨርስቲው አመራሮች እና ከመላው የዩንቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ይበልጥ ውጤታማ እንደምንሆን አምናለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ⬆️አዲስ አበባ ከተማን ፍፁም የብጥብጥ አውድማ ለማስመሰል በርካታ ሰዎች በፌስቡክ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ከነዚህም መሀል በአክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድ ስም #የሀሰት ገፅ ተከፍቶ ህዝቡን ለማበጣበጥ የሚሰሩ ሰዎች ስላሉ ጥንቃቄ ይደረግ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ📌Jawar Mohammed ከLTV ጋዜጠኛዋ ቤቲ ጋር ያደረገው ቆይታ ክፍል 2 ዛሬ ማታ 2:30 ይቀጥላል።

Ltv freq👉11512 Symbol Rate 27500 V

©አባቱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሪፖርት📌በ2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት ከዓለም የሚበልጣት ሀገር እንደሌላት ተገለጸ።

በጦርነት የሚታመሱት #የመንና #ሶሪያ እንኳ የኢትዮጵያን ያሕል አልተፈናቀለባቸውም፡፡

ዛሬ ይፋ በተደረገው የ“ኢንተርናሽናል ዲስፕሌስመንት ሞኒተሪንግ ሴንተር” (IDMC) ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1.4 ሚሊየን ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የኖርዌይ ስደተኞች ምክር ቤት የክልሉ ዳይሬክተር ናይገል ትሪክስ 1.4 ሚሊየን ሕዝብ አካባቢውን ጥሎ ሲፈናቀል ዓለም ተገቢ ትኩረት አለመስጠቱን ተችተዋል፡፡ በምዕራብ ጉጂ እና ጌዲዮ በተቀሰቀሰ ግጭት ብቻ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው በተቋሙ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬆️

‹ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ › በሚል ርዕስ አቀባበል እንደሚደረግ የአቀባበል ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ሞላ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ እና #አንዳርጋቸው_ፅጌን ጨምሮ ሌሎች የግንቦት ሰባት አባሎች አርብ ማታ ባሕር ዳር ይገባሉ፡፡

አርበኞቹ ለነፃነት ሲባል ላበረከቱት አስተዋፅኦ የክብር አቀባበል እንደሚደረግ ሰብሳቢው ተናግረው በአቀባበሉ ሥነ-ስርዓቱም "ለአርበኛ ታጋዮች ቅድሚያ ይሰጣል" ብለዋል፡፡

ቅዳሜ መስከረም 5/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአቀባበል ሥነ-ስርአቱ ይካሄዳል፡፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን አቶ ዳዊት ገልጸዋል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia