" ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥምቅት 30/2017 ወደ ቤታችሁ ግቡ ፤ ይህ ካልሆነ የሽያጭ ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ለቤት ተጠቃሚዎች በዕጣና በጨረታ የሚያስተላልፈው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " በሽያጭ ከተላለፉና ውል ከተፈጸመባቸው ቤቶች መካከል የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ገብተው እየኖሩ አለመሆኑን አረጋግጫለሁ " ብሏል።
" በህጋዊ መንገድ ውል የተያዘባቸው ቤቶች ለህገወጥ ተግባር እየዋሉ ነው " ያለው ኮርፖሬሽኑ ፥ የቤት ባለቤቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በያዙት የሽያጭ ውል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ አስጠንቅቋል።
" በተባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ቤቱ የማይገባ የቤት ባለቤት የሽያጭ ውሉ በህግ አግባብ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " ሲልም ገልጿል።
#AddisAbaba
@tikvahethiopia

#ኢሬቻ2017
የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' እና ' ሆራ አርሰዲ ' በዓልን ለሚያከብሩ ታዳሚዎች ትራንስፖርት መዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።
በአዲስ አበባ በ5ቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶብሶች፣ 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶብሶች መዘጋጀታቸውን ተገልጿል።
ቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል 150 የሚሆኑ ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቢሶች ዝግጁ እንዲሆኑ መደረጉን ተመላክቷል።
በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር 1 ሺህ 457 ተሸከርካሪዎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል።
#AddisAbaba #Bishoftu

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ይህ የሆነው አሁን ከመሸ ከ2:00 በኃላ ነው።
በአንዳንድ ቦታዎችም ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።
የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው ተሰብስበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎች ከባለሙያዎች ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ? " እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ…
#ATTENTION🚨
ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ? መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ ምንድነው ?
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ምን አሉ ?
" ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ።
መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም።
ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ሊመጣ ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።
ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር ነው መሆን ያለበት።
ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር ከመጣ አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው ከመጣ ግን ምን መደረግ ስለለበት ጥንቃቄ ነው።
➡️ የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት ለምን መውረድ ሊከብድ ይችላል ቁልፍ ማክፈትም ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ ኮለኖች አካባቢ መጠጋት።
➡️ ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት።
➡️ ሊፍት አትጠቀሙ። ማንም ሰው በሊፍት ለመውረድ እንዳይሞክር። ያን እንዳትጠቀሙ።
ይሄን ይሄን ጥንቃቄ ማደርግ ያስፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ከባድ ነገር አለ ብለን አንገምትም። "
#Ethiopia #AddisAbaba

Photo
#ለጥንቃቄ🚨
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?
➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
#Ethiopia #AddisAbaba #የእሳትናአደጋስራአመራር

" የቀበሌና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጅተዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር ካሳ እና 100 ሄክታር ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ ፦
➡️ 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣
➡️10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች
➡️ 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500 የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በ8 ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር ቦታ ለማልማት ተቅዷል ብለዋል።
የሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የትኞቹ ናቸው ?
1. ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት 1000 ሄክታር ቦታ ስፋት እና 40.4 ኪሎሜትር ርዝመት ፤
2. ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ የኮሪደር ልማት 128.7 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 7.1 ኪሎሜትር ርዝመት፤
3. ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል የኮሪደር ልማት 146 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 10.8 ኪሎሜትር ርዝመት፤
4. ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት 565 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 15.9 ኪሎሜትር ርዝመት፤
5. አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ ኮሪደር ልማት 16.58 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 3.1 ኪሎሜትር ርዝመት
6. አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል የኮሪደር ልማት 314 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 13.19 ኪሎሜትር ርዝመት
7. የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት 372.5 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 20 ኪሎሜትር ርዝመት፤
8. እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት 274 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 21.5 ኪሎሜትር ርዝመት፤
በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል።
#AddisAbaba #ShegerFM

" ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይታደሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን
ከአዲስ መንጃ ፈቃድና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፤ " ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል " ብሏል።
በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡
አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ተመላክቷል።
ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ባልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ባለቤቶቹ እንዲገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ቤቶቹ “ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸመባቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው።
የቤቱ ባለቤቶች እስከ ተባለው ቀን ድረስ ካልገቡ ቤቶቹ በእጣና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፉ ኮርፖሬሽኑ መግለጹ አይዘነጋም።
ይህን ውሳኔ ተከትሎም የቤት ባለቤቶች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚዲያችን አቅርበዋል።
በተለይም በአራብሳ ሳይት የሚገኙ የቤቶቻቸው መሠረተ ልማት ያልተጠናቀቀላቸው ሰዎች ውሳኔው ብዥታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
የቤት ባለቤቶቹ መሠረተ ልማታቸው ሳይሟሉ እንዴት መግባት እንችላለን? ግዴታ መግባት ነው ወይስ ማከራየት ይቻላል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣
👉 መሠረተ ልማት ባልተሟላባቸው ቤቶች እንዴት መግባት ይቻላል ?
👉ሽየቤቱ ባለቤቶች ግዴታ መግባት ነው ያለባቸው ማከራየት ይችላሉ ?
👉 ክፍት በሆኑ ቤቶች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ምንድን ናቸው?
👉 እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጸመው በተጨባጭ በየትኞቹ ሳይቶች ነው? ሲል ኮርፖሬሽኑን ጠይቋል፡፡
አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ አካል፣ ማስታወቂያው የወጣው መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው ላልገቡ የቤት ባለቤቶች እንጂ መሠረተ ልማታቸው ላልተሟላላቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
“ ያልተሟላቸውን እማ እንዴት ተብሎ!? የማሟላት ግዴታ አለበት መንግስት መሠረተ ልማቱን ” ነው ያሉት፡፡
የኮርፖሬሽኑ በዝርዝር ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ባልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ባለቤቶቹ እንዲገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ ውሳኔው የተላለፈው ቤቶቹ “ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸመባቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው። የቤቱ ባለቤቶች እስከ ተባለው ቀን ድረስ ካልገቡ ቤቶቹ በእጣና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፉ…
#AddisAbaba
“በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው” - ኮርፖሬሽኑ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታችሁ ግቡ " በሚል ባወጣው ማሳሰቢያ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው ?
የኮርፖሬሽኑ ማብራሪያ ፦
“ ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው’ ብለው እኛ ጋ ስለመጡ ነው፡፡
ቤቶቹን ቼክ ስናደርጋቸው ደግሞ እጣ ወጥቶባቸዋል፤ ውል ተፈጽሞባቸዋል፣ ግን ሰው አልገባባቸውም፡፡
ስለዚህ ነዋሪው ተቸግሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተደጋጋሚ ወደኛ ቢሮ የሚመጡ የየሳይቱ የነዋሪዎች ማኀበራት አሉ፡፡
ስለዚህ እነዚህ አካባቢዎች ላይ ያሉ ቤቶች በአግባቡ ቤት የደረሳቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶቹም የተሟሉ፣ ሰው ገብቶ መኖር የጀመረባቸው በመሆናቸው ክፍት መሆን የለባቸውም፡፡ የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ፡፡
ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብት ነው፡፡ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ይኑርበት ነው የኛ ጥያቄ፡፡ አካራይ አታከራይ የኔ መልዕክት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ቤቱን ኦውን ያድረጉ፡፡
ሰው ‘የጸጥታ ስጋት ብሎ ይጠይቀናል’፣ የጸጥታ መዋቅሩም እኛን ይጠይቀናል፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ደግሞ ቤት ደርሶት ያልገባበት ሰውም ጭምር በመኖሩ እጣ ያልወጣላቸውም ሰዎች ጭምር ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡ ‘ይሄው ክፍት ቤት አለ ይላሉ፡፡’
ስለዚህ በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው፡፡
የማኅበራዊ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በተለያዬ መንገድ ኢንተርፕሬት ሊደረግ ይችላል፡፡
ዋናው የመንግስት ኢንቴንሽን ግን ይሄ ነው፡፡
ክፍት ቤቶች ያሉት አብዛኛው ሳይት ላይ ነው የቤቶቹ መጠን ይለያያል እንጅ (አንዳንድ ቦታ ላይ አምስት፣ አንድ ቦታ ላይ ደግሞ አስር ሊሆኑ ይችላሉ)፡፡
ከተነሳው ቅሬታ አንጻር መሠረተ ልማት ያልተሟላባቸው ደግሞ የተወሰኑ ሳይቶች አሉ (እየተሟላባቸው ያሉ ማለት ነው)፡፡
ለምሳሌ በተደጋጋሚ የሚነሳው አራብሳ ሳይት (ፓኬጅ ሦስት) ነው፡፡ ወደ መጨረሻ አካባቢ ከተገነቡት ቤቶች መካከል ነው። አራብሳ ሦስት አብዛኛው መሠረተ ልማት ተሟልቷል፡፡
ለምሳሌ መንገድ አክሰስ ነው፡፡ አክሰስ ተሰርቶለታል፡፡ ወደ ዘላቂ መንገድ ለማስገባት ለሁለት፣ ሦስት ዓመታት ኢኮስኮ የተባለው ኮንትራክተር ቦታውን ይዞት ነበር ከመንገዶች ተረክቦ ለመስራት፡፡
ነገር ግን ሳይሰራው ቆዬ፡፡ ይሄ ጥያቄ በተደጋጋሚ የማህበረሰቡ ጥያቄ ስለሆነ አቅርበን አሁን ተርሚኔት ተደርጎ መንገዶች ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
ክረምቱን በሙሉ አክሰስ ወደ መስራት ዝግጅት ላይ ነው የነበሩት አሁን በተሟላ መልኩ ቋሚ መንገድ ሊሰራ ነው፡፡
የመጠጥ ውሃ ወደየ ሳይቱ፣ ወደዬ ብሎኩ ገብቷል፡፡
ፍሳሽን በተመለከተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ሜጋ ፕሮጀክት እየተሰራ ነው፡፡ በውጭ ካምፓኒ ነው የሚሰራው፡፡ የበጀት እጥረት ገጥሟቸው ጋፕ ነበረ አሁን ግን በተሟላ መልኩ እየተሰራ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ያልቃል፡፡
የአራብሳን አጠቃላይ ችግር ይህ ፕሮጀክት ነው የሚፈታው፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኮሪደር ልማት ተነሽዎች እየገቡ ስለሆነ ሴፍቲ እስታንክ እየተቆፈረ ለጊዜው ፍሳሹ እንዲመጣ፣ ዘላቂው ሲሰራ ደግሞ በቋሚነት እንዲሆን እየሰራን ነው፡፡
አምስትና ስድስት ላይ በተመሳሳይ እየሞከርን ነው፡፡ የተወሰኑ ችግሮች አሉ ሰፈራ የሚባለው አካባቢ የወሰን ማስከበር ችግር አለው፡፡
ለምሳሌ ፍሳሽ፣ የመጠጥ ውሃ በዚያ በኩል ያልፋል ግን የወሰን ማስከበር ችግር አለ፡፡ መፈታት አለበት በሚል ከተማውም ይዞት ለመስራት ጥረት እያደረገ ነው፡፡
የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ቦታዎች እናውቃቸዋለን፡፡ ችግሩ እንዲፈታም ጥረት እያደረግን ነው፡፡ እኛ እያልን ያለነው ይህን አይደለም፡፡
መሠረተ ልማት ተሟቶላቸው በአብዛኛው ነባር ሳይት የሚባሉ፣ ሕዝቡ ገብቶ እየኖረበት ያለ አካባቢ ክፍት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ነው ያነሳነው፡፡
ማስታቂያውን በተዛባ መልኩ ለማስተላለፍ የሚፈልጉ አካላት አሉ፡፡ ‘ቤት ሊነጠቅ ነው፣ ሊወሰድባችሁ ነው’ የሚል መልዕክት ሊያስተላልፉ የሞከሩ አሉ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ነባርና አዳዲስ የቤት ፍላጎቶችን ለማሟላት የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን አጥንቶ ወደ ተግባር በመግባት ላይ ነው ያለው እንኳን የነበረውን ወደዚህ ደረጃ ለማድረስ። ”