TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትዝብት📌የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን ከ12 ሰዓት ጀምረው ማየት እንደሚችሉ በትልልቅ የመንግስት እና የግል መገናኛ ብዙሀን አሰራጭቷል። ይህ በተባለበት ሰዓት ተማሪዎች ውጤት ይታይባታል በተባለበት ድረገፅ እና የSMS ቁጥር ያለማያቋረጥ ሙከራ ቢያደርጉም ምንም ውጤት ለማየት አልቻሉም። ዝግጅት ካልተደረገበት እና ሲስተሙ በአግባቡ የማይሰራ ከሆነ ለምን ለህዝብ ይፋ ተረገ?? ይህን መሰሉ አሰራር የተቋሙን ታማኝነት ያሳጣዋል። በሌላ በኩል ተቋሙ ውጤት ማይታይበት ችግሩ ምን እንደሆነና ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ በመግለፅ ህዝቡን ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባው ነበር። ብዙ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በአሰራር ክፍተት #ማስጨነቅ ፍፁም ተገቢ #አይደለም። ሊታረም ሊስተካከል ይገባዋል።

ህዝብ ይከበር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነገ ጀምሮ📌አፋን ኦሮሞ እንማር! ቃንቄ ገዳ! QAANQEE GADAA!
.
.
በመጀመሪያው ዙር አፋን ኦሮሞ እና ትግርኛን እንማራለን! ለዚህም ዝግጅት ተጠናቋል!

1:00 ምሽት እንገናኝ!
@tikvahethedu ቻናል ተቀላቀሉ ሼር!
ቅምሻ!

📌የቁቤ ፊደላት ለምንና መቼ ይደጋገማሉ??

▪️አናባቢዎች ለምን እና መቼ ይደጋገማሉ?
▪️ተነባቢዎች ለምን እና መቼ ይደጋገማሉ?
.
.
NAGAA GAAFACHUU(ነጋ ጋፈቹ)
የሰላምታ አቀራረብ

▪️Akkam bulte?(አከም ቡልቴ?)
እንደምን አደርክ? እንደምን አደርሽ?
▪️Nagaadha.Fayyaadha(ነጋዳ ፈያደ)
ደህና ነኝ
.
.
እደጅማሬ አስፈላጊ የተባሉትን ጉዳዮች እንምለከታለን።

ነገ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በ @tikvahethedu እንገናኝ!

ብዙ ብዙ እንማራለን!
ብዙ ብዙ እናውቃለን!
ቀጠሮ📌ነገ ቅዳሜ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ #ንፁ አከባቢን ለመፍጠር የአዲስ አበባ ከንቲባው በተገኙበት አከባቢን የማፅዳት ቀን ይጀመራል። ይሄን አከባቢ የማፅዳት ቀን በፊት #አውራሪነት የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ነው። እናም 1 ሰዓት ላይ ፒያሳ መዘጋጃ በር ላይ ሁሉም አንዳንድ መጥረጊያ ይዞ እንዲገኝ ክለቡ ጥሪ ያቀርባል። ስት መጡም የክለቡ ደጋፊዎች ክለቡን የሚገልፁ ነገሮችን ይዛችሁልኝ ተገኙም ብሏል።

📌 ከፒያስ መዘጋጃ ጀምሮ እስከ ስታድየም ለኛ ተሰጥቷል ብሏል ክለቡ።

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች!
@tsegabwolde @tikvahethipia
#update አርበኞች ግንቦት 7⬇️

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ #መቀሌ#አዳማና #አዲስ አበባን ጨምሮ በ32 ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተገለጸ፡፡

ከአቀባበል ኮሚቴ በተገኘው መረጃ እሁድ ጳጉሜ 4/2010 ብርሀኑ ነጋን (ፕ/ር) ጨምሮ አመራሮቹ ኢትዮጵያ እንደገቡ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሕዝቡ ንግግር ያደርጋሉ፤ የስታዲየሙ ንግግር በኢሳትና ሌሎች ቴሌቪዥን ጣቢያዎች #በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል፡፡ በስታዲየሙ የሚገኘውን የሕዝብ መጨናነቅ ለመቀነስ በመስቀል አደባባይ በስክሪን ንግግሩ ይተላለፋል፡፡

መስከረም 6 እና 7 በባሕርዳር እና ጎንደር፣ መስከረም 12 በአዳማ አመራሮቹ የሚገኙበት ሕዝባዊ ትዕይንት ከተካሄደ በኋላ በተከታታይ ቀናት #በመቀሌ#ወልዲያ#ደሴ እና #አምቦ ተመሳሳይ ፕሮግራም ይኖራል፡፡

ንቅናቄው አቀባበሉን በተመለከተ ትናንት በሰጠው መግለጫ “በዕለቱ ሥነ ሥርዓት ለማስከበርና የሕዝብን ደሕንነት ለመጠበቅ ከተሰማሩ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ታሪካዊ የአቀባበል በዓሉ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካሄድ” ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጳጉሜ 2 - የፍቅር ቀን

#በፍቅር ተደምረን፤ #በይቅርታ እንሻገር!

ክፉ አያግኛችሁ! ሰላም እደሩልኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ10ኛ ክፍል ውጤት መታየት ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውጤታችሁን ለማየት📌

በrtn 8181 እና በፈተናዎች ኤጄንሲ ድረገጽ https://app.neaea.gov.et/Home/Student ተጠቀሙ።

መልካም ዕድል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከገርጂ⬆️

"Hi Tsega እጅግ በጣም ከባድ የመኪና አደጋ አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ ከኮካብ ህንፃ ወደ አንበሳ ጋራዥ በሚወስደው መንገድ አንድ አፈር የጫነ Sino Truck ከአድ የVitz መኪና ላይ ወጠቶባታል ባሁን ሰዓት መኪናውን ለማንሳት ጥረት እየተደረገ ነው። ደሬ"

📌የጉዳት መጠንን በተመለከተ የተረጋገጠ መረጃ ሲደርሰኝ አቀርባለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia