TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ታዲያስ አዲስ📌አቶ ንጉሱን ለማናገር ስልክ ቢደውልም አየር መንገድ ስለነበሩ ድምፅ አልሰማ ስላላቸው ምላሻቸው ሳይቀርብ ቀርቷል።

"ዛሬ ማታ በሚኖሩት የኢትዯ ፌም ፕሮግራሞች ላይ ወይ ነገ ታዲያስ አዲስ ፕሮግራም ላይ ምላሻቸውን ይዘን እንቀርባለን ባህርዳር እስኪደርሱ እየጠበቅን ነው።"(9:45)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ያለመከሰስ_መብት?⬇️

«ያለመከሰስ መብት»ን በተመለከተ በበርካታ የህግ መዝገበ ቃላት ላይ የሚደጋገመው ትርጓሜ «አንድ ግለሰብ ወይንም አካል የህግ ጥሰት የፈፀመ መሆኑ እየታወቀ ለወንጀሉ ተጠያቂ እንዳይሆን የሚደረግለት ህጋዊ ከለላ» ከሚለው ጋር የሚስተካከል ነው።

የዚህ «ልዩ ከለላ» ተጠቃሚዎች ከሆኑት መካከል የህዝብ #እንደራሴዎች#የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና #የዳኝነት አካላት ይገኙበታል።

የመብቱ የጀርባ አመክንዮ ግለሰቦቹን እና አካላቱን በመክሰስ ወይንም ለፍርድ በማቅረብ ከሚገኘው ጠቀሜታ ይልቅ ካለ ክስ እና #ተጠያቂነት በማለፍ የሚሳካው ማህበረሰባዊ ግብ የላቀ ነው ከሚል ዕምነት ጋር ይያዛል።

ሆኖም ይሄ የከለላ መብት #ተነስቶ ግለሰቡ ወይንም አካሉ ላይ ክስ የሚከፈትባቸው አግባቦች ፈፅሞ የሉም ማለት አይደለም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ህገ- መንግስት እና የክልል ህገ-መንግስታት ይሄንን መብት ከሰጣቸው ወገኖች መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተጠቃሽ ናቸው።

ለአብነት የህዝብ ተወካዮችን በሚመለከተው የአፌዲሪ ህገመንግስት #አንቀፅ 55 (6) ላይ የአለመከሰስ መብትን እና መብቱ የሚነሳበትን
አግባብ እንደሚከተለው ደንግጓል።

«ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፣ በወንጀልም አይከሰስም።»

ይሄን መሰረት አድርጎ #ያለመከሰስ መብታቸውን ከተነጠቁት የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና የቀድሞው የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ዓለማየሁ ጉጆ ይጠቀሳሉ።

ከሰሞኑ ደግሞ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና ስድስት የክልሉ ምክር ቤት አባላት በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ውሳኔ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

እንደ ኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ሁሉ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ህገ -መንግስት አንቀፅ 48 (6) ላይ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ
መብት የሚነጠቅበት አግባብ መቀመጡን ልብ ይሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! የደቡብ ሱዳኑ የአማፂ ቡድን መሪ #ሪክ_ማቻር  የሀገሪቱን ሰላም  ለመመለስ የሚያስችለውን የተሻሻለውን ስምምነት #ለመፈረም ፍቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

📌የአማፂ ቡድን መሪው ሀገሪቱ ሊኖራት በሚገባው የክልል #መጠንና #የደንበር ጉዳይ በነበራቸው ቅሬታ ማሻሻያ የተደረገበትን ሁለተኛ ስምምነት ለመፈረም ፍላጎት አልነበራቸውም።

▪️ሆኖም #ከሱዳን መንግስት ጋር በተደረገ ከፍተኛ #ድርድር ሪክ ማቻር የመጨረሻውን የሰላም ስምምነት ለመፈረም መዘጋጀታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አል ዲርዲር መሀመድ ተናግረዋል።

©CGTN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከካዛንቺስ⬆️

"ካዛንቺስ መናኸሪያ አካባቢ ወጣቶች ለአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች አቀባበል ለማድርግ የሰቀሉት ባነር ነው። ቃል ከካዛንቺስ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን 96 ሰዎች መገደላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል #ዘይኑ_ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት ቀውሱ በተነሳበት የመጀመርያው ቀን #ሐምሌ 27፣ 2010 ዓ. ም. ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች #ግድያው መፈጸሙን ተናግረዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት #በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑን ተናግረው፤ ሀይማኖትና ብሔርን ለይቶ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ አክለዋል።

"ከዘር #ጭፍጨፋ አይተናነስም" ብለዋል። መነሻው የክልሉ አመራሮች አቅደው፤ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎች አሰልጥነውና አሰማርተው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

እስከ አሁን የክልሉን የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኡመርን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

'ሄጎ' በመባል የሚታወቀው ቡድን በግድያው እጁ ስለመኖሩ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "በዋናነት በግጭቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት #ሄጎ በሚባለው ቡድን አባላት ናቸው። ሄጎ የሚባለውን #የፈጠሩ፣ እቅዱን ያቀነባበሩ የክልሉ የፖለቲካ #አመራሮች፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ #ባለስልጣኖችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራን ነው" ብለዋል።

ልዩ ፖሊስ በግድያው ተሳትፎ ስለመሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ማን በምን ደረጃ ተሳተፈ የሚለው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በጅግጅጋ የሚኖሩ የተለያዩ አካባቢዎች ተወላጆች ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ጄኔራል ዘይኑ፤ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የክልልሉን ዋና ዋና ከተማዎች መቆጣጠሩ አንጻራዊ ሰላም ማስፈኑን ገልጸዋል።

በአሁን ወቅት አዲሱ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ አካባቢው መመለስ ቀጣዩ ስራ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተባበራቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ደባርቅ⬆️

መኖሪያ ቤት ውስጥ የገባው ነብር 19 በጎችን ገደለ፡፡ ነብሩ ጥቃት ያደረሰው በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ቀበሌ 03 አዲስ ዓለም ተብሎ በሚጠራው መንደር ነው፡፡

በጥቃቱ ንብረትነታቸው የአቶ ሙሉ ፀጋው የሆኑ 19 በጎች ተገድለዋል፡፡ ከሞቱት በተጨማሪም 9ኙ ከባድ ጉዳት፣15ቱ ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

#ጥቃቱ የደረሰው ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በበጎች ማደሪያ(ጋጥ) ውስጥ ነው፡፡

ከአሁን ቀደም በነብር ተመሳሳይ ጥቃት ይደርስ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ.ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ አቡሃይ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት ነብሩ በሰዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ #ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ከነበሩት 45 በጎች ውስጥ 2 በጎች ብቻ ናቸው ጉዳት ያልደረሰባቸው፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvhethiopia
#update በደቦ ፍርድ ሰው ተገደለ⬇️

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ቤተ ክርስቲያ ግቢ ውስጥ በተፈጸመ የደቦ ፍርድ የአንድ ግለሰብ ሕይወት #አለፈ፡፡ ግድያው የተፈጸመው ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት መሆኑን ሪፖርተር ከፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ከቡሬ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የእሳት ጭስ መታየቱን፣ እሳቱን ለማጥፋትም ከቤተ ክርስቲያኑ በቅርብ ርቀት ከሚገኘው የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞችን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መትመማቸውን፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ዋና ኢንስፔክተር አበበ አጥቁ አረጋግጠዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኑ #ማህሌት ተብሎ ከሚጠራው ክፍል ሳይነሳ እንዳልቀረ የተገመተው እሳትም፣ በሕንፃው ላይ ብዙም ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል፡፡

በቦታው የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች እሳቱ ሆን ተብሎ በሰው የተነሳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ያሉ የአብነት ተማሪዎችን ማጠያየቅ እንደጀመሩ፣ ከዚያም በቤተ ክርስቲያኑ ተጠልሎ ነበረ የተባለን ግለሰብ ጥያቄ መጠየቅ መጀመራቸውን #ከቡሬ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የሚማሩ የአብነት ተማሪዎች ግለሰቡን እንደሚያውቁት ሲጠየቁ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ከመጣ ቀናት እንደተቆጠሩና የእግዜር እንግዳ መሆኑን መናገራቸውን ገልጸዋል ሲሉ፣ የቡሬ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ቡድን መሪ ወ/ሮ ጉዳይ መለሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሟችን ‹ፀጉረ ልውጥ› በማለት እንደያዙትና ጥቃት እንደሰነዘሩበት የቡድን መሪዋ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ በበኩሉ መጀመርያ ላይ ሦስት አባላቱን ወደ ቦታው አንቀሳቅሶ እንደነበር ዋና ኢንስፔክተር አበበ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይህ ችግር እንዳለ 12 ሰዓት አካባቢ ነው ሪፖርት የተደረገልን፤›› ብለዋል፡፡

ነገር ግን በሰዓቱ ግለሰቡን ‹ፀጉረ ልውጥ› ነው ብለውና ቃጠሎውን እንደፈጸመ አድርገው ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በድንጋይ ቀጥቅጠው መግደላቸውን ከዓይን እማኞች ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹አባላቶቻችን በጥቃቱ ጊዜ ወደ ላይ በመተኮስ ግለሰቡን ለማዳን ሞክረው ነበር፤›› ያሉት ዋና ኢንስፔክተር አበበ፣ ‹‹የነበረው የሰው ብዛት ግን ከአቅማችን በላይ ነበር፤›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ‹‹መጀመርያ ሦስት የፖሊስ አባላት ወደ ቦታው ተልከው ነበር፡፡ በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያኑ ካህናት መስቀል አውጥተው ለመገዘትና ጥቃቱን ለማስቆም ሞክረው ነበር፤›› ያሉት ዋና ኢንስፔክተር አበበ፣ ይህም ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል፡፡ ‹‹ሌላው ቢቀር ሟችን መቃብር ቤት ውስጥ አስገብቶ ለመደበቅ ሁሉ ተሞክሮ ነበር፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ግድያው ከተፈጸመ በኋላ መረጃ ለመሰብሰብ መሄዳቸውን፣ ከቃጠሎው በፊትም ሆነ በኋላ ሟች  አብሯቸው እንደነበር የቤተ ክርስቲያኑ የአብነት ተማሪዎች እንደ ነገሯቸው ወ/ሮ ጉዳይ አስረድተዋል፡፡

‹‹በቦታው የነበረው #በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች (በአብዛኛው ወጣቶች) ነበሩ፡፡ በሻሸመኔ ተደርጎ እንደነበረው ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም፣ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ደግሞ #የሟችን አስከሬን ተሸክመው ለመውሰድ ተሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ ከዞኑ በተላከ ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ድርጊቱን #ማስቆም ተችሏል፤›› ሲሉ በሥፍራው ተገኝተው የነበሩት የከተማው የብአዴን የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ግዛቸው ካሳዬ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቱ እንዴት ተነሳ ለሚለው በመጣራት ላይ መሆኑን፣ አስከሬኑን ተሸክመው ለመውሰድ ከሞከሩት ውስጥ ሁለት ወጣቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ #ግድያውን ያስተባበሩትን ለመያዝ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ዋና ኢንስፔክተር አበበ አስታውቀዋል፡፡ 

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬇️

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ የተመራው የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ኮሚቴው በስብሰባውም የተለያዬ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት፦

1. የአገር ውስጥ የግል ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ለሚገዙት "27% ቦንድ" ብሄራዊ ባንክ የሚከፍላቸው ወለድ አሁን ካለው ከ3% ወደ 5% ከፍ እንዲል፣

2. የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በአገር ውስጥ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚያስቀምጡት የ50,000 የአሜሪካን ዶላር ገደብ እንዲነሳ፣

3. የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸውን 30% ለብሄራዊ ባንክ የሚሸጡበት ተመን በመግዢያና በመሸጫ መካከል ባለ (አማካይ) ዋጋ እንዲሆን፣

4. በውጭ ምንዛሪ ክፍያ እንዲቀበሉ የተፈቀደላቸው የንግድ ድርጅቶች በስራ ላይ ካለው ዝርዝር በተጨማሪ:-

* በኤርፖርት ውስጥ የሚሰጥ የቴሌኮም አገልግሎት፣
* ለውጭ ቱሪስቶች የቻርተርድ አገልግሎት የሚሰጡ የግል አየር መንገዶች፣
* የውጭ ዜጎችን የሚያስተናግዱ የእንግዳ ማረፊያዎች፣
* የውጭ ዜጎችን የሚያስተናግዱ ልዩ ክሊኒኮች እና
* የውጭ ዜጎችን የሚያስተናግዱ ሆስፒታሎችን እንዲጨምር ኮሚቴው መወሰኑን አቶ ፍፁም ተናግረዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update አዳማ⬆️

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ "ሕገወጥ ነው" ያለውን አካባቢ ለማፍረስ በሄደበት ወቅት ከነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች #መቁሰላቸው ተገልጿል።

በተፈጠረው ችግር እጃቸው አለበት ያላቸውን ሰዎች ፖሊስ #በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

©voa amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ ሊቆም ነው የተባለው የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት #ውሸት ነው ብሏል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር። በነገው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ሊጣል ነው የተባለውም ውሸት መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ቢሮ አዲስ ስታንዳርድ ሰማሁት እንዳለው የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት ሊቆም መሆኑና የመሰረት ድንጋይ ነገ ይቀመጣል መባሉም #ውሸት መሆኑን አረጋግጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ልሳነ አማራ⬆️

ጋዜጠኛ እና አክቲቪስቱን #ሙሉቀን_ተስፋውን ጨምሮ የልሳነ ዐማራ አባላት የአማራ ብዙኃን
መገናኛ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ የድርጅቱን #ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ያዩት ጎብኝዎቹ ዘመናዊ እና የተደራጀ ተቋም አይተናል ብለዋል። ድርጅቱ የአማራን ብሄርተኝነት ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ ‹‹የአማራ ብሄርተኝነት ለኢትዮጵያዊነት ዋስትና እንጅ የሚጣረስ አይሆንም፡፡›› ሲል ጋዜጠኛ እና አክቲቪስቱ ሙሉቀን ተስፋው ተናግሯል።

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia