TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢንጂነር ስመኘው⬇️

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሰኔ 16 ቀን በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት፣ በኢንጅነር ስመኘው ግድያ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በከባድ ሙስና ወንጅሎች ዙሪያ በ25/12/10 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ይሠጣል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጋምቤላ⬇️

በጋምቤላ ከተማ ከትናንት በስቲያ እኩለ ሌሊት ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው #ጎርፍ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጁሉ ኡኮዝ እንደገለጹት ጎርፉ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰው ሌሊት ለሶስት ሰዓታት የሰህል ያለማቋረጥ የጣለው ከባድ ዝናብን ተከትሎ ነው፡፡

ፖሊስ ባካሄደው የማጣራት ስራ ከ20 በላይ ቤቶች ከንብረታቸው ጋር ከጥቅም ውጪ ማድረጉንና ከ300 የሚበልጡ ቤቶች ደግሞ በጎርፍ እንደተጠለቀለቁ ተናግረዋል።

በከተማው የጎርፍ አደጋ የሚከሰተው የማፋሰሻ ቱቦዎች በአግባቡ ባለመሰራታቸው እና በቱቦዎቹ ላይ ህገ ወጥ ግንባታ በመካሄዱ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሳይመን ቦር በበኩላቸው የህብረተሰቡ ቅሬታ ትክክለ መሆኑንና ወደፊት ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ጠባብ የሆኑ የማፋሰሻ ቱቦች ላይ ጥናት በማድረግ የማሻሻያ ስራዎችን እንደሚያካሂድ ጠቁመው በአሁኑ ወቅትም የተጀመሩ ስራዎች
መኖራቸውንም ተናግረዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የስራ ማቆም አድማ⬆️

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም #አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰራተኞቹ ለኢቢሲ በስልክ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው #ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣ የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ መናር የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ወ/ኪዳን ሰራተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ለአቢሲ አረጋግጠዋል፡፡

ሰራተኞቹ ያቀረቡትን ችግር ለመፍታት ውይይቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ከሰዓት በኃላ የግንባታ ተቋራጩን ጨምሮ በሚደረግ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወሊሶ⬆️

LAMMIIKO BARSISUFUF ANIS NAAN FIGA!!
ወገኔን ለማስተማር እኔም እሮጣለሁ!!

"ፀግሽ ሰላም ነው? Ati እባላለው ከወሊሶ። ከዚ በታች ምትመለከተን ወጣቶች በወሊሶ ከተማ "we are one" በሚባለው የvolunteer association የተለዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመስራት በተለያየ ምክንት መማር እየፈለጉ መማር ያቃታቸውን ከ300 በላይ ተማሪዋች በያመቱ ደብተር እና እስክሪብቶ እንዲዩም ዩኒፎርም በማሰፋት እየረዳን እንገኛለን። ከምንሰራቸው ስራዋች በጥቂቱ ሊስትሮ በመጥረግ፣ የተለያዩ ቦታዋች በማፅዳት፣ ኩፖን በመሸጥ እና ሌሎችም ስራዋች በመስራት ገቢ ስናሰባስብ ከርመናል። አሁን ደሞ በቅርቡ ማለትም መስከረም 6 በወሊሶ ከተማ "ወገኔን ለማስተማር እኔም ሮጣለው" በሚል መፈክር ታላቅ እሩጫ አዘጋጅተናል። T-shirt መግዛት ለምትፈልጉ በነዚ ስልኮች ይደውሉ።
0915962469
0913218438
0913218476

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ አራት ባለሥልጣናት ዛሬ ችሎት ቀርበዋል።

ከአብዲ ኢሌ በተጨማሪ ፍርድ ቤት የቀረቡት፦

📌የቀድሞ የክልሉ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ #ራህማ_ማህድ ሀይቤ፣

📌የቀድሞ የክልሉ የዳያስፖራ ቢሮ ኃላፊ #አብዱረዛቅ_ሳኒ

📌የቀድሞ የክልሉ የመስኖ ልማት ቢሮ ኃላፊ #ሱልጣን_መሐመድ

ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል #ዘርና #ብሔርን ለይተው የክልሉን ወጣቶች #አስታጥቀው ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል እንዲሁም ለሃይማኖት ተቋማት ውድመት ምክንያት ሆነዋል በሚል ነው፡፡

ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀን ጠይቋል፡፡
ሁሉም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀል።

‹‹ፖሊስ ለምርመራ የጠየቀው ጊዜ በዝቷል፣ እስካሁን #ቃላችንን አልተቀበለም፤ ነገር ግን ከተያዘን 48 ሰዓት አልፏል›› ሲሉ ተደምጠዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቴዎድሮስ ካሳሁን⬆️

ለአዲስ አመት #ዋዜማ በሚሊኒም አዳራሽ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት የተስተጓጎለበት #ቴዲ_አፍሮ አሁን መስከረም 5 ቀን 2011 ኮንሰርቱን ለማድረግ መወሰኑ ታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ለሚሊየም አዳራሽ አስፈላጊውን ክፍያ መፈፀሙ ታውቋል፡፡

ቴዲ ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለማቅረብ ጠይቆ አዳራሹ ለሌላ #ፕሮግራም ይፈለጋል ተብሎ #ሳይፈቀድለት መቅረቱ ይታወሳል።

©z
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ #ብሔር_የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የተሻሻለው መመርያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማነዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡

ይህንን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ በክፍላተ ከተሞችና በወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን ያካተተ ሥልጠና፣ ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ብሔርን የሚጠቅስ በመሆኑ፣ ይህም ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎላ ስለሆነ በተገኘው አጋጣሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በያዙ ማግሥት ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደገለጹት፣ የመታወቂያ ጉዳይ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ እየተነሳበት በመሆኑ አሰጣጡን ማስተካከል ይገባል፡፡

በዚህ መሠረት መመርያው የተሻሻለ በመሆኑ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ለውጥ ያመጣል ተብሏል፡፡

የመጀመሪያው በመታወቂያ ላይ ከብሔር ስያሜ ይልቅ #ኢትዮጵያዊ ሲባል፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሰጣጡ ዲጂታል ስለሚሆን ሕገወጦችን መለየት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ በተለይ ሕገወጥ ጥቅም የሚሹ ግለሰቦች፣ በተለያዩ ዘዴዎች መታወቂያ በማውጣት ሲያገኙ የቆዩትን ጥቅም እንደሚያስቀር ታምኗል፡፡

ለአብነት በክልል ከተሞች የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው በሕገወጥ መንገድ  የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ኮንዶሚኒየም ቤት የተቀራመቱትን ዕርምጃ መውሰድ ያስችላል ተብሏል፡፡

የተሻሻለው መመርያ የኮምፒዩተር አመዘጋገብ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ ሒደት፣ የነዋሪዎች መታወቂያ ይዘትና የመሸኛ ጉዳይን በዝርዝር ይዟል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአሰላ⬆️

"ሰላም! ዛሬ በዘነበው ከባድ ዝናብ አሰላ ማልት ፋብሪካ አካባቢ የተከሰተው የመኪና አደጋ በፎቶው የምትመለከተውን ይመስላል። እኔ ባለኝ መረጃ የሞተ ሰው የለም በአደጋው። የተጎዱ ሰዎች ደግሞ በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው አሰላ ሆስፒታል ተወስደዋል። ሰኢድ ከአሰላ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ📌ብዙ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከላይ የሚታየውን መልዕክት ከማዕበራዊ አፆች ላይ በመውሰድ እየላካችሁልኝ የ10ኛ ክፍል ውጤት ስለመውጣቱ እየጠየቃችሁኝ ነው። ውጤት አልወጣም! ከላይ የሚታየው ፅሁፍም ውጤት የሚታይበት አይደለም። ሰዎችን #መሸወጃ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopis