#update ደቡብ ሱዳን⬇️
የደቡብ ሱዳኑ አማፃ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር በሀገሪቱ ያለውን የእርስ በእርስ ግጭት ፍፃሜ ያበጃል ተብሎ የተጠበቀውን የሰላም ስምምነት ውድቅ ማድረጋቸውን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባለፈው ወር የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ሪክ ማቻር የተኩስ አቁም እና የስልጣን መጋራት እንዲኖር የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።
ሆኖም ሪክ ማቻር አዲስ የተዘጋጀውን የሰላም ስምምነት ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፥ ይህም ወደ ሙሉ ስምምነት ለመድረስ የሚደረገው ጥረት አዳጋች እንደሆነ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አል ዲርዲር መሀመድ፥ ዋነኛው የአማፂ ቡድን መሪ ሪክ ማቻርን ጨምሮ ሌሎች አማፂ ቡድኖች ከተለያዩ ጥቃቶች እንዲቆጠቡ የሚያስችለውን ስምምነት ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
በደቡብ ሱዳን ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ሀገሪቱ ነፃነቷን ከአወጀች ሁለት አመታት በኋላ በፈረንጆቹ 2013 የተጀመረ ሲሆን፥ 12 ሚለየን የሚሆነው የሀገሪቱ ዜጎች ከመኖሪያቸው ቄያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።
ምንጭ፥ ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ታማኝ በየነ⬇️
ለአርቲስት #ታማኝ_በየነ የሚደረገው አቀባበል በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ጠየቀ።
አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ቅዳሜ #ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ጠዋት 1 ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የኃይማኖት አባቶች አቀባበል ያደርጉለታል።
የኮሚቴው አባል አቶ #የሺዋስ_አሰፋ እንደተናገሩት በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ከመንግሥት የፀጥታ አካላት በተጨማሪ ኀብረተሰቡ ራሱንና አካባቢውን በመጠበቅ የአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የዜግነት ግዴታ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ በበኩላቸው የተለያዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱ ሲሆን በዕለቱ ትያትር ቤቶች የባህል ሙዚቃና ውዝዋዜ ያቀርባሉ፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባለው ልዩ የእንግዳ ማረፊያም ታማኝ በየነ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየረ ማረፊያ እስከ ብሄራዊ ትያትር ቤት ድረስ አድናቂና ደጋፊዎቹ የአዲስ አበባና የተለያዩ አካባቢ ሰዎች በሰላማዊ ህዝባዊ ትዕይንት አቀባበል ያደርጉለታል ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል።
በብሄራዊ ትያትር ቤት ጥሪ የተደረገላቸው ከ1 ሺህ በላይ እንግዶች በተገኙበት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እንደሚቀርቡም ገልጸዋል።
እሁድ ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ከተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ሰዎች ንግግር ያደርጋሉ፤ አርቲስት ታማኝ በየነም የምስጋናና አጠቃላይ መልዕክት ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው ዝግጅት 25 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአርቲስቶችን ፍቅር፣ ተስፋ እንዲሁም አንድነትን የሚያበስሩ የጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ወደ አሜሪካ ‘ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ’ በሚል መርህ ተጉዘው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የአርቲስት ታማኝ በየነ ወደ አገር ውስጥ መግባት የድልድዩን መጠናከር የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።
©ኢዜአ

#update አዲስ አበባ⬇️
በአዲስ አበባ 6ኪሎ በሚገኘው አንበሳ ጊቢ ውስጥ አምስት አንበሶች መሞታቸዉ ተረጋገጠ።
ለእድሳት በሚል ተዘግቶ የቆየዉ የ6ኪሎ አንበሳ ግቢ መስከረም 2009 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም 28 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ግንባታዉ ከ22 በመቶ በላይ ማለፍ አለመቻሉን ማወቅ ተችሏል፡፡
በአንድ አመት ዉስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረዉ ግንባታዉ በመንጓተቱ ምክንያትና በእንክብካቤ ማነስ ምክንያት በቅጥር ግቢ ዉስጥ ይኖሩ የነበሩ 15 አንበሶች መካከል አምስቱ መሞታቸዉን #ኢቢሲ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
📌የአዲስ ዙ ፓርክ ማእከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሴ ክፍሌ በበኩላቸዉ በመካነ እንስሳዉ የሞተ አንበሳ የለም ብለዋል፡፡
©ዘሪሁን ግርማ

አቶ ንጉሱ ለአቶ በረከት የሰጡት መልስ⬇️
ሰሞኑን የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በርከትን እና አቶ ታደሰን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ማገዱን ተከትሎ አቶ በረከት ለተለያዩ ሚዲያዎች ውሳኔው:-
=> በስብሰባው ለመታደም ዋስትና ስላልተሰጠኝ መገኘት አልቻልኩም፣
=> ውሳኔው መሰረተ ቢስ ነው፣
=> የኤርትራ መንግስት እጅ እና ፍላጎት ስለላበት በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ የተፈፀመ ነው፤ እኔ እርምጃ የተወሰደብኝ ኤርትራዊ ዘር ስላለኝ ነው፣
=> አቶ ደመቀ ጠቅላይ ሚንስትር እንዳይሆን ስለታገልኩት በቂም ነው፣
=> እኔ ከኦሮሞ አንድ አመራር ወደ ሀላፊነት(ጠቅላይ ሚንስትርነት) እንዲመጣ ፍላጎት ነበረኝ ታግያለሁም፣
=> የአማራ አመራር አቅም የሌለው በመሆኑ የወጣቱን ጥያቄ ስላልመለሰ አቅጣጫ ለማሳት ከሱዳን፣ ከትግራይ እና ከአፋር እያጋጨ ነው፣ ሲሉ ብአዴንን በመክሰስ እና ማንንም ሊያሳምንልኝ ይችላል ያሉትን ሁሉ ጠጠር በመወርወር ላይ ናቸው።
===
ይህንን ሰምተን እና እዳምጠን አቶ በረከትን በዕድሜያቸው አክብረን እውነትን ሲያዛቡ እና በተንኮል መንገዳቸው ሲነጉዱ ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ ጥቂት ነገር ማለት ፈለግን ::
===
አቶ በረከት የጠየቁት ዋስትና የአማራ ወጣቶች እንዳያጠቋቸው በመፍራት እንደሆነ ገልፀዋል። እሳቸውን የመሰለ አድራጊ ፈጣሪ፣ የፈለጉትን አንጋሽ እና አውራጅ ሰው ወደ ዋስትና ጠያቂነት ሲለወጥ ዋስትናውን ከመጠየቅ ለምን ወጣቱ ይህንን አለ፤ ምንስ አጠፋሁ ?
ብሎ ራስን መመርመር የሚበጅ ስለመሆኑ እሳቸውን መምከር "ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች " ስለሚሆን እንተወው። ግን ግን በየወረዳው
መድረክ ፈጥረን ባወያየንባቸው መድረኮች ሁሉ ወጣቱ " በረከት የአማራን መብት አስረግጧል፣ ህዝቡን አስቀጥቅጧል፣ አማራን አንገቱን እንዲደፋ አድርጏል ... ወዘተ "ብሎ ሲሞግተን እኛም ወጣቱን ስንመክር የሚወርድብንን ትችት ቢያዩት አቶ በረከት አመራሩን ባልኮነኑ እንላለን።
===
ውሳኔውን በተመለከተ አቶ በረከት መሰረተ ቢስ ነው አሉት እንጂ እኛ ደግሞ ብአዴንም ሆነ አመራሩ መወቀስ ካለበት ውሳኔውን #በማዘግየቱን እና ከልክ ያለፈ ትዕግስት ማሳየቱ ነው። አቶ በረከት ማዕከላዊ ኮሚቴው ስለ ክልሉ ህዝብ ተጠቃሚነት እንዳይወያይ በማድረግ የንትርክ እና የጭቅጭቅ ኮሚቴ ካደረጉት እኮ ከአምስት አመታት በላይ ሆኗቸዋል:: በብአዴን ውስጥ ብቃት ያለው አመራር እንዳይወጣ እና የአማራ ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ እንዳይነስ ትንሽ ሀሳብ ብልጭ ያደረገን ሰው ከሌሎች ጋር ሆነው "ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ" በማለት አጎብዳጅ እና ተላላኪ ሆነን እንድንኖር ታግለዋል። እሳቸውውን የታገሉትን ህይወታቸው እንዲመሰቃቀልም ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ጥረትንም የተጨመላለቀ የቤተሰብ እና የጏደኛ ጎጆ መውጫ አድርገውታል ተብሎ መገምገሙን በሶስትና አራት ወራት አይረሱትም። ስለሆነም ውሳኔው የዘገየ ከበቂ በላይ ፖለቲካዊ መሠረት ያለው ነው እንላለን። በህግ የመጠይቅን ጉዳይ በተመለከተ ህግ ይየውም እንላለን።
===
"ውሳኔው የኤርትራ መንግስት እጅ አለበት፤ እኔም ኤርትራዊ ስለሆንኩ ነው " ያሉት ነገር እርስ በእርሱ የሚጣፋ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አቶ በረከት ብአዴን በሌላ ውጫዊ አካል የሚታዘዝ ድርጅት ነው እያሉንም ስለሆነ "እሱ አክትሟል፤ እንኳን ከሌላ አገር በብእእዴንም ውስጥ
ባዕድ ሀሳብ ሊጭን ይእሚችል ሀይል የሚሸከም ትከሻ የለም " ልንላቸው እንወዳለን። እኛም ወደ ኤርትራ የሄድንበትን ምክንያት ህዝብ ስለሚያውቀው ውሀ እንደማይቋጥር እሳቸውም አይጠፋቸውም። በነገራችን ላይ የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ልዑክ መስከረም 3 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ኤርትራ ይጏዛል::
===
አቶ #ደመቀን በተመለከተ "ጠቅላይ ሚንስትር እንዳይሆን ስለታገልኩት ነው " ላሉት ደግሞ ምክንያታቸው ደካማው ነው:: ምክንያቱም አቶ ደመቀ በእጩነትም እንዳይያዙ ለምክር ቤት አቅርበው እንደነበረ እና ምክንያታቸውም አዲስ አመራር እንዲመጣ ፍላጎት ስላላቸው መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ከመሆኑም በላይ የአቶ ደመቀን ትልቅነትና አስተዋይነት ያሳየ የወራት ትውስታ ስለሆነ ይህም ውሀ አይቋጥርም። ለነገሩ አቶ በረከት በብአዴን መድረክ የአመራር ሽግሽግ አጀንዳ በማቀንቀን እሳቸው የሚያዙት አሻንጉሊት ሊቀመንበር ለማስቀመጥ አምርረው ታግለዋል፣ ጉዳዩንም እስክ ደምፀ ውሴኔ አድርሰዋል:: ሀሳባቸውም ውድቅ ተደርጏል:: አቶ በረከት ኦሮሞ ወደ ስልጣን ይምጣ ብለው እንደሞገቱ እና እንደታገሉ ገልፀዋል። ነገር ግን ዶክተር አብይ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመረጡ ብአዴን ሲታገል "አብይ ኢትዮጵያንም ኢህአዴግንም አይመጥንም " ብለው የታገሉት አብይ የየትኛው ብሄር እና ድርጅት መሪ መስለዋቸው ይሆን? ምን አልባት በአልባት በሁለቱ ህዝቦችና ድርጅቶች መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር ታስቦ ከሆነ ይሄ አልፎበታል። ለነገሩ ባለፈው አመት በባህር ዳር የኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የጋራ መድረክ ስንፈጥር አቶ በረከት እና መሰሎቻቸው " መርህ አልባ ግንኙነት ነው" ብለው መድረኩ እንዳይካሄድ እስከ ዋዜማው ጥረት ማድረጋቸው እና ትምክህትና ጥበት ያልተቀደሰ ጋብቻ መሰረቱ ብለው እንደወረዱብን ለምናስታውስ ጉዳዩ የቆየ እና ባህሪያዊ ስለሆነ እንደተለመደው እናልፈዋለን።
===
በመጨረሻም የአሁኑ የአማራ ክልል አመራር ደካማ ነው ሲሉ አመራሩን አጣጥለዋል። ለመሆኑ ይሄ አመራር ደካማ ቢሆን ኖሮ እንዴት እሳቸውን ያህል ጉምቱ ፖለቲከኛ እና የተቀናቀኑትን መቀመቅ የሚያወርዱ ሰው ተቋቋመ? እንዴትስ ለእርሶ አላጎበድድም አለ? እንዴትስ ያልተደፈሩትን የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ደፍሮ ተሟገተባቸው? ባለፉ ጥቂት ወራት በነበሩን ስብሰባዎችስ ብአዴን ላይ ተስፋ አለኝ አላሉምን ? አሁን ያለው አመራር የወጣቱን የስራ ዕድል ይፈጠርልኝ ጥያቄ አይመልስም ሲሉ ለመሆኑ ይህ አመራር ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ምን እየሰራ እንደሆነስ ያውቁ የለም ? የአማራ ወጣት ጥያቄ ስራ እና ዳቦ ብቻ ነው እንዴ ? ጥያቄው እኮ ከዳቦ በላይ ነው። ጥያቄው ነፃነት፣ እኩልነት፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት፣ ማንነት ነው። ለነገሩ እነዚህ ጥያቄዎች አማራ ሲያነሳቸው ለእርስዎ ትምክህት ናቸው። እነዚህን ያነሱ የብአዴን አመራሮችን አሳደው መምታትዎትን መናገር እርስዎን መድፈር ስላልሆነ እንናገረዋለን። አመራሩስ ደካማ ቢሆን ማን መራው፣ ማን አሰለጠነው፣ ማን ገመገመው ቢባል ቀዳሚው ሰው አቶ በረከት መሆንዎ አይቀርምና የአመራር አያያዜ ምን ይመስል ነበር ብሎ ራስን መፈትሽ ከእውነት ያስታርቃል።
ታዲያ ይህንን ስል የትንታኔ ብቃቶትን፣ የትግል ድፍረቶትን እና እድሜዎትን በመድፈር አይደለም። ቢያድልዎት ኖሮ ልክ እንደ አንዳንዶቹ የድርጅታችን መስራቾች "ቦታውን የያዘው አመራር በራሱ መንገድ ይምራ፣ እኛ ገብተን አንፍትፍት " ብለው መድረኩን ለባለመድረክ ቢልቁ መልካም ነበር እንላለን። እርሶን ያህል የኢትዮጵያን ሚዲያዎች ያሾር የነበረ ሰው አንድ ድብቅ አላማ ያነገብ እውደድ ባይ ግለሰብ የሚዘውራት እዚህ ግባ ማትባል ቦታ መገኘትዎትም እርስዎን አይመጥንም እና ይቅርብዎት እንልዎታለን።
📌አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ!

ጅግጅጋ⬆️የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ጎብኝተዋል።
©ጋሻው ሲሳይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ጋሻው ሲሳይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ቢኒያም ተወልደ⬇️
በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በከረሙት የቀድሞ የኢትዮጵያ መረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር አቶ #ቢኒያም_ተወልደና በሦስት ግለሰቦች ላይ ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. የሙስና ክስ ተመሠረተ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት በከፈተው ክስ ተከሳሽ አድርጎ የጠቀሳቸው አቶ ቢኒያም ተወልደ፣ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ፣ ወ/ሮ ጽጌ ተክሉና አቶ ይርጋለም አብርሃ ናቸው፡፡
ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ የመሠረተው ስድስት ክሶችን ነው፡፡ በክሱ ላይ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥትና በሕዝብ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አከማችተው መገኘታቸውንና ሌሎችንም ነጥቦች ጠቁሟል፡፡
ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ 881/07 አንቀጽ (1ሐ እና 2) የሙስና ወንጀሎችን ለመከላከል የተደነገገውን በመተላለፍ፣ የሙስና ወንጀል መፈጸማቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡ አቶ ቢኒያም የኢንሳ ምትክል ዳይሬክተርና የሥልጠናና የትምህርት ተቋም ዳይሬክተር ሆነው ሲሠሩ፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተውና ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም መንግሥትንና ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር መፈጸማቸውን ዓቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡ ለራሳቸው ጥቅም ለማግኘትና ለሌላው ለማስገኘት በማሰብም የሚስጥራዊ አገልግሎት ግዥ ወይም ‹ሳይበር ታለንት ማኔጅመንት ፕሮግራም› ግዥ ለመፈጸም፣ ከእስራኤል አፎሜጋ ድርጅት ጋር የተፈጸመን ውል ምክንያት በማድረግ፣ ሥልጠና ላልሰጠ ድርጅት ሥልጣና እንደሰጠ በማስመሰል 32,472,000 ብር ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡
ክፍያው የተፈጸመው ሥልጠና ሊሰጥ የነበረው ድርጅት ሥልጠናውን ሰጥቶ እንዳጠናቀቀ የሚገልጽ ሠርተፊኬት ከኢንሳ እንደተሰጠው በማስመሰል፣ ክፍያው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል መፈጸሙን ክሱ ያብራራል፡፡ የሥልጠና አገልግሎት ግዥ የተፈጸመው በ3,200,000 ዶላር ወይም 72,160,000 ብር ሲሆን፣ ክፍያ ሊፈጸም ስምምነት የተደረገው በሦስት ጊዜ ቢሆንም፣ ተከሳሾች ግን ውሉን ያልጠበቀና ጉዳት የሚያደርስ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡
ሌሎችም ተከሳሾች በመመሳጠርና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት በማፍራት ክሳቸውን ለመስማት ለጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
©ሪፖርተር

#update የትምህርት ፍኖተ ካርታ⬇️
በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የቀረበውን ጥናታዊ ምክረ ሀሳብ ከቋንቋ ጋር ማገናኘት ተገቢ እንዳልሆነ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ ሳይሆን ከመጪው ዓመት ጀምሮ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ #ፈተና አይኖርም ብሎ ተማሪዎችን ማዘናጋትም አይገባም ብሏል ቢሮው።
ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተገኙበት ለመጪው 15 ዓመት የትምህርት ሴክተሩ የሚመራበት ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ለውይይት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ በሰጡት መግለጫ ረቂቅ ፍኖተ ካርታውን ተከትሎ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጠው ትምህርት 6ኛ ክፍል ላይ ሊቆም ነው የሚሉ አሉባልታዎች በስፋት እየተደመጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በመሆኑም የጥናት ምክረ ሃሳቡ ”በዚህ ቋንቋ ይሰጥ ይህ ቋንቋ ይቅር” የሚል ነገር ስለሌለው ከቋንቋ ጋር ማያያዙ ተገቢ አይደለም ብለዋል።
የቀረበው ፍኖተ ካርታ ወደፊት ሲጸድቅ በአንደኛና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት በኦሮምኛ ቋንቋ መማሩ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።
በፍኖተ ካርታው የቋንቋ ጉዳይ ትኩረት እንደተሰጠው የገለጹት ኃላፊው አንድ የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ አንድ አገራዊ ቋንቋና አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ለሁሉም መሰጠት አለበት የሚለው ነው #እንደሐሳብ የተነሳው ብለዋል።
እነዚህ ቋንቋዎች እነማን ናቸው? የሚለው ጥያቄ ወደ ፊት የሚታወቅ እንጂ በቀረበው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ የተገለጸ አለመሆኑን ህዝቡ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባው ዶክተር ቶላ ገልጸዋል።
የጥናት ቡድኑ ያቀረበው አዲሱ ፍኖተ ካርታ በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ላይ ውሎ የአስረኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ያስቀራል የሚሉ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የቀረበው ረቂቅ ጥናት ዓላማው ምክረ ሃሳብ ማቅረብ እንጂ የተወሰነ ጉዳይ እንዳልሆነ የገለጹት ዶክተር ቶላ ”ገና ሰፊ ወይይት ይፈልጋል፣ ስምምነት ላይ ከተደረሰም በኋላ ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የሙከራ ጊዜ ያስፈልገዋል” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የቀረበው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ከቋንቋ ጋር የተገናኘ ነገር የለውም ማለታቸው የሚታወስ ነው።
በአዲሱ ፍኖተ ካርታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ሲሆን ዝቅተኛ መካከለኛ ደግሞ 7ኛና 8ኛ ክፍል እንዲሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ስር ይጠቃለላል እሱም ገና ለውይይት እየቀረበ ነው።

#update ሶማሌ ክልል⬇️
የሱማሌ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ኡመር ለሱማሌ ልዩ ፖሊስና ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ ሀላፊዎች መሾማቸው ተሰማ።
#ሙሃመድ_አብዲ_መዋስር የልዩ ፖሊስ አዛዥ፣ አብዲ ሀሰን ሙሴ ምክትል አዛዥ ሁነው ተሹመዋል።
#ሙሀመድ_ሀሰን_አሊ (ሞሀመድ ያሬ) የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል። እንዲሁም ሙሀመድ አብዲ ጉሬ ምክትል ኮሚሽነር በመሆን ተሹመዋል።
በሌላ በኩል የጅግጅጋ ከተማ አዲስ ከንቲባ አግኝታለች አቶ ጋራድ ኡመር የከተማዋ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።
©R
@tsegabwolde @tikvahethipia

#update ሜቴክ⬇️
የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተሰጠው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ኮንትራት እስካሁን አለመቋረጡን፣ የፕሮጀክቱ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ #ኤፍሬም_ወልደኪዳን (ኢንጂነር) ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ መንገዶች እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች የተሳሳተ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሆኑን የገለጹት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ልምድ ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች የንዑስ ተቋራጭነት ውሎችን ከሜቴክ ጋር በመዋዋል በርካታ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን እንዲያከናውኑ መደረጋቸው አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በተመለከተ ስምምነት ያለው ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር ስለሆነ፣ አሁንም ይኼንን ውል በተመለከተ የተለወጠ ነገር አለመኖሩን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ
ገልጸዋል፡፡
ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ኮንትራትን ማቋረጥም ሆነ አዲስ ውል መዋዋል ቀላል ተግባር አይደለም፡፡ እስካሁንም ሜቴክ ዋና ኮንትራክተር ነው፤›› ሲሉም ተደምጠዋል።

#update በህዳሴ ግድብ ሥራ ላይ የተሰማሩት የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ። ሠራተኞቹ አድማውን የመቱት በቂ ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ነው። ሳሊኒ ከሠራተኛ ተወካዮች ጋር እስከምወያይ ድረስ ወደ ሥራ ተመለሱ ብሏል።
©ዘሀበሻ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ዘሀበሻ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ አብዲ ፍርድ ቤት ቀረቡ⬇️
የሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ_ሙሐመድ_ዑመር በዛሬው እለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ቀረቡ። አቶ አብዲ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ነው።
📌አቶ አብዲ ሙሀመድ ዑመርን ጨምሮ ሌሎች 4 ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
©fbc

#update ኢንጂነር ስመኘው⬇️
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሰኔ 16 ቀን በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት፣ በኢንጅነር ስመኘው ግድያ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በከባድ ሙስና ወንጅሎች ዙሪያ በ25/12/10 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ይሠጣል፡፡
©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሰኔ 16 ቀን በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት፣ በኢንጅነር ስመኘው ግድያ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በከባድ ሙስና ወንጅሎች ዙሪያ በ25/12/10 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ይሠጣል፡፡
©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጋምቤላ⬇️
በጋምቤላ ከተማ ከትናንት በስቲያ እኩለ ሌሊት ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው #ጎርፍ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የከተማው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጁሉ ኡኮዝ እንደገለጹት ጎርፉ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰው ሌሊት ለሶስት ሰዓታት የሰህል ያለማቋረጥ የጣለው ከባድ ዝናብን ተከትሎ ነው፡፡
ፖሊስ ባካሄደው የማጣራት ስራ ከ20 በላይ ቤቶች ከንብረታቸው ጋር ከጥቅም ውጪ ማድረጉንና ከ300 የሚበልጡ ቤቶች ደግሞ በጎርፍ እንደተጠለቀለቁ ተናግረዋል።
በከተማው የጎርፍ አደጋ የሚከሰተው የማፋሰሻ ቱቦዎች በአግባቡ ባለመሰራታቸው እና በቱቦዎቹ ላይ ህገ ወጥ ግንባታ በመካሄዱ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የጋምቤላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሳይመን ቦር በበኩላቸው የህብረተሰቡ ቅሬታ ትክክለ መሆኑንና ወደፊት ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ጠባብ የሆኑ የማፋሰሻ ቱቦች ላይ ጥናት በማድረግ የማሻሻያ ስራዎችን እንደሚያካሂድ ጠቁመው በአሁኑ ወቅትም የተጀመሩ ስራዎች
መኖራቸውንም ተናግረዋል።
©etv