#update አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ⬆️
አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን በፍቅር ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን የቅበላ ኮሚቴዉ አስታወቀ፡፡
ለአቀባበሉ የተዋቀረዉ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ አቀባበል ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል ብሏል፡፡
ታማኝ በየነ በኪነ ጥበቡ ዙሪያ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማነቃቃት፣ የመድረክ ፈርጥ ሆኖ ሌሎች ተከታዮቹን በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል፡፡
ለረጅም ዓመታት #አንድነትን፣ #ፍቅርን፣ #መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን በተሰጠዉ መግለጫ ተገልጿል፡፡
ይህ ኢትዮጵያዊ #ጀግና ነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የሥራ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ብለዋል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ ዕለት ተገኝተዉ በፍቅር እጃቸዉን ዘርግተዉ እንዲቀበሉት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የጀርመን ልማት ትብብር ሚኒስትር ገርድ ሙለር የሀገራቸው ትልቁ የቴሌኮም ኩባንያ “ደች ቴሌኮም” ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር መስራት እንደሚፈልግ አሳውቀዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ #የቮልስዋገን መኪናዎች መገጣጠም እንደሚጀመር ጠቁመዋል፡፡ ዛሬ ጧት በአስመራ ከፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር የተወያዩት ሚኒስትሩ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተው ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትር
ዶክተር አብርሀም ተከስት ጋር እንዲሁም አመሻሹን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ተነጋግረዋል፡፡
©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር አብርሀም ተከስት ጋር እንዲሁም አመሻሹን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ተነጋግረዋል፡፡
©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! ብአዴን አቶ #በረከት_ስምዖን እና አቶ #ታደሰ_ካሳን በጥረት ኮርፖሬሽን በፈጠሩት ችግር ምክንያት በመጪው መስከረም አጋማሽ እስከሚካሄደው ጉባኤ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ውሳኔ አስተላልፏል።
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብአዴን⬆️
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ #በረከት_ስምኦን እና አቶ #ታደሰ_ካሳ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት #ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት #ታግደዋል፡፡
ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያም #ተሽሯል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር #አይሳተፍም፡፡
📌ማዕከላዊ ኮሚቴው የሁለት ቀን ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡
©AMMA

ከአዲስ አበባ⬇️
"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ? ባለፈው አቃቂ መሿለኪያ ደርሶ ስለነበረው ነገር ሁላችንም እናስታውሳለን አሁን ላይ አደጋው አጥልቶባቸው የነበሩት ሰዎች ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም በሰላም ወደቤታቸው ተመልሰዋል አንዷ ግን አሁንም ህክምና ላይ ነች ከሁሉም ውሃ ውስጥ ብዙ ቆይታ ነበር በሆዷም ውሃ ገብቷል። ሌላው ድርጅቱ ቸሬአልያ ማለት ነው ይህንን አስመልክት ነገ ቅዳሜ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ እንኳን ተረፋችሁልኝ ለማለት ዝግጅቱን ጨርሷል።"

#update በዶክተር ኤልያስ ገብሩ የተፃፈው "ኤቶዮጵ" መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል። በአንባቢ ጥያቄ መሠረት የመፃፉ መሸጫ ዋጋ ከ150 ወደ120 ብር ዝቅ ብሏል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብአዴን ውስጥ ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያ #ተሽሯል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር #አይሳተፍም፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጥረት ኮርፖሬት⬆️
▪️ጣና ኮሚኒኬሽን
▪️ዳሽን ቢራ
▪️አምባሰል የንግድ ስራዎች ድርጅት
▪️ጥቁር አባይ ትራንስፖርት
▪️ዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅት
▪️እሸት የእስታርች ውጤቶች ማምረቻ
▪️በለሳ ሎጅስቲክ
▪️BDC ኮንስትራክሽን
▪️TT ኢንጂነሪንግ
▪️አዚላ ኤሌክትሮኒክስ
▪️ዋሊያ ቆርኪ ፋብሪካ
▪️ተክራርዋ የፕላስቲክ ማምረቻ
▪️የትመን የጅብሰም ውጤቶች ማምረቻ
▪️ጎንደር ብቅል ማምረቻ ፋብሪካን ጨምሮ ከ20 የሚበልጡ ድርጅቶችን በስሩ ያስተዳድራል።
እንዲሁም፦ ጥረት ኮርፖሬት በወጋገን ባንክ፣ በአባይ ባንክና ኢንሹራንስ፣ በአፍሪካ ኢንሹራንስ፣ በፋና ብሮድካስቲንግና በሌሎች ድርጅቶች ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ አለው።
አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በጥረት ኮርፖሬት ውስጥ በሰሩት #ጥፋት ነው እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲታገዱ የተደረገው፡፡
📌አቶ በረከት ስምዖን የጥረት ኮርፖሬት ቦርድ ሰብሳቢ ነበሩ እንዲሁም አቶ ታደሰ ካሳ የጥረት ኮርፖሬት ስራ አስፈጻሚ ነበሩ።
#TIKVAHETHIOPIA

#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬆️
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ማምሻውን በድንገት በሽራተን ሆቴል ተገኝተው በእሳቸው ጥያቄ በቻይና የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝተው የሚሄዱ የረጅም እና የአጭር ጊዜ ሰልጣኞችን በማግኘትና መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላቸው በመመኘት #ሽኝት
አደረጉላቸው።
ተማሪዎቹም 50 የሁለተኛ (masters) እና የሶስተኛ (PhD) ዲግሪ፣ 100 የበትረ-ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 50 ከዓመቱ የወርቅ ሜዳሊያ ተመራቂዎች የተመረጡ፣ እንዲሁም 50 ከኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተመረጡ በድምሩ 250 ሲሆኑ፣ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ቻይና እንደሚያቀኑ ይጠበቃል። ይህም የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ትስስር እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።
©አቶ ፍፁም አረጋ