TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.3K photos
1.55K videos
215 files
4.25K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከራያ ቆቦ⬆️

"ፀግሽ በራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ከተማ መግቢያ ላይ ጎርፍ በሚስከትለው ደለል ምክንያት መኪናዎች ለማለፍ ይቸገራሉ። ይህ ቦታ ላለፍት 2 አመታት ተመሳሳይ ችግሮችን አስከትሏል። የሚመለከተው አካል ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላቂ መፍትሄ እዲሰጠን እንጠይቃለን። Desta"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች በስራ አስፈፃሚነት ሲያገለግሉ የቆዩት ባለሥልጣናት እስከ መጪዉ ዕሁድ ድረስ ከስልጣናቸዉ #እንደሚሰናበቱ የከተማዉ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ተናግረዋል።

በዛሬ እለትም የሚሰናበቱትን የማወያየት፣ አዲስ የሚሾሙትን ደግሞ ስለ ተልኮዉ ግልፅ የማድረግ ስራ ላይ እንደምገኙም ወይዘሮ ዳግማዊት አስታዉቀዋል።

መስተዳድሩ በመቀጠልም በ117 ወረዳዎች ለህዝብ ፍላጎት ተገቢ መልስ ሊሰጡ የሚችሉትን አመራሮች እንደሚያደራጁ ምክትል ከንቲባዋ ጠቅሰዋል።

©ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ⬆️

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን በፍቅር ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን የቅበላ ኮሚቴዉ አስታወቀ፡፡

ለአቀባበሉ የተዋቀረዉ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ አቀባበል ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል ብሏል፡፡

ታማኝ በየነ በኪነ ጥበቡ ዙሪያ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማነቃቃት፣ የመድረክ ፈርጥ ሆኖ ሌሎች ተከታዮቹን በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል፡፡

ለረጅም ዓመታት #አንድነትን#ፍቅርን#መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን በተሰጠዉ መግለጫ ተገልጿል፡፡

ይህ ኢትዮጵያዊ #ጀግና ነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የሥራ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ብለዋል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ ዕለት ተገኝተዉ በፍቅር እጃቸዉን ዘርግተዉ እንዲቀበሉት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀርመን ልማት ትብብር ሚኒስትር ገርድ ሙለር የሀገራቸው ትልቁ የቴሌኮም ኩባንያ “ደች ቴሌኮም” ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር መስራት እንደሚፈልግ አሳውቀዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ #የቮልስዋገን መኪናዎች መገጣጠም እንደሚጀመር ጠቁመዋል፡፡ ዛሬ ጧት በአስመራ ከፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር የተወያዩት ሚኒስትሩ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተው ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትር
ዶክተር አብርሀም ተከስት ጋር እንዲሁም አመሻሹን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ተነጋግረዋል፡፡

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! ብአዴን አቶ #በረከት_ስምዖን እና አቶ #ታደሰ_ካሳን በጥረት ኮርፖሬሽን በፈጠሩት ችግር ምክንያት በመጪው መስከረም አጋማሽ እስከሚካሄደው ጉባኤ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ውሳኔ አስተላልፏል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሰበር_ዜና⬆️አቶ #በረከት_ስምዖን እና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ታገዱ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብአዴን⬆️

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ #በረከት_ስምኦን እና አቶ #ታደሰ_ካሳ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት #ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት #ታግደዋል፡፡

ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያም #ተሽሯል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር #አይሳተፍም፡፡

📌ማዕከላዊ ኮሚቴው የሁለት ቀን ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬇️

"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ? ባለፈው አቃቂ መሿለኪያ ደርሶ ስለነበረው ነገር ሁላችንም እናስታውሳለን አሁን ላይ አደጋው አጥልቶባቸው የነበሩት ሰዎች ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም በሰላም ወደቤታቸው ተመልሰዋል አንዷ ግን አሁንም ህክምና ላይ ነች ከሁሉም ውሃ ውስጥ ብዙ ቆይታ ነበር በሆዷም ውሃ ገብቷል። ሌላው ድርጅቱ ቸሬአልያ ማለት ነው ይህንን አስመልክት ነገ ቅዳሜ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ እንኳን ተረፋችሁልኝ ለማለት ዝግጅቱን ጨርሷል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዶክተር ኤልያስ ገብሩ የተፃፈው "ኤቶዮጵ" መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል። በአንባቢ ጥያቄ መሠረት የመፃፉ መሸጫ ዋጋ ከ150 ወደ120 ብር ዝቅ ብሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብአዴን ውስጥ ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያ #ተሽሯል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር #አይሳተፍም፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia