TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ክሳድ ዒቃ⬆️

ከ60 በላይ የትግራይ ክልል #ራማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ትናንት መረብን ተሻግረው የኤርትራ ከተማ በሆነችው ክሳድ ዒቃ ከኤርትራውያን ጋር ውለው ተመልሰዋል።

©VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደሴ⬆️1439 ኛው የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በደሴ ተከብሯል።

©Awol
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር⬇️

"ኢድ በጎንደር ለሱማሌ ክልል ተፈናቃዮች የገንዘብ ድጋፍ በመሰብሰብ አሳልፈናል እስካሁንም እስከ 59200 ብር ተሰብስቧል!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስታወቂያ በ2010 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለወሰዳቹተማሪዎች⬇️

መቐለ ዩኒቨርስቲ፣ መቐለ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት (MU-MIT) በተመረጡ የኢንጅነሪንግ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የትምህርት እና የምርምር ዘርፎች የልህቀት ማእከል የመሆን ራእይ ይዞ የተቋቋመና፥ የሃገራችን የመረጃና የመገናኛ ምህንድስናና ቴክኖሎጂ የተማረ የሰው ሃይል ፍላጎት በሟሟላት የላቀ ኣስተዋጻኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው። ኢንስቲትዩቱ ሃገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስድዉ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በመግቢያ ፈተና አወዳድሮ በማስገባት በሚከተሉት የትምህርት ዘርፎች በ5 ዓመት የድግሪመርሃ ግብር ያስተምራል።

📌ኬሚካል ምህንድስና (Chemical Engineering )

📌ኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና (Computer Science and Engineering )

📌ኤሌክትሮኒክስና ኮሚኒኬሽን ምህንድስና (Electronics and communication Engineering)

📌ኤሌክትሪካል ምህንድስና (Electrical Engineering)

📌ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (Information Technology)

📌ማተርያል ሳይንስና ምህንድስና (Material Science and Engineering)

ስለሆነም በ2010 ዓ/ም ሃገር ኣቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደዉ ኢንስቲትቱ ያወጣው የመመዝገቢያ መስፈርት  ማለትም ውጤታቸዉ ከ 425 (ለወንዶች)፣ 400 (ለሴቶች) በላይ ለሆኑት በሚከተለዉ የመመዝገበያ መንገድ አንዱን በመጠቀም ከነሓሰ 09 – ጳጉሜን 02፣ 2010 ዓ/ም መመዘገብ ይችላሉ። 

በኢንስቲትቱ ድህረ ገፅ mitethiopia.edu.et. የሚል ገብታቹ Register የሚል ሊንክ በመጫን ወይም ( https://www.mitethiopia.edu.et/index.php/2018/08/11/entrance-exam-registration/#comment-1260 )

የተመዝጋቢዉ ሙሉ መረጃ ማለት
◾️ሙሉ ስም ፣
◾️የ12ኛ መመዝገበያ ቁጥር Registration ID)፣
◾️የ12ኛ ውጤትና
◾️ስልክ ቁጥር ወደ [email protected] ኢ-መይል በመላክ

ወደ ከታች ከተዘረዘሩትን ስልክ ቁጥሮች በመደወል

ሀ) 0345 59 4309,     
ለ) 0348 40 9872,    
ሐ) 0932 05 2216 
መ) 0911 83 2294       
ሠ) 0912 08 1941          

በኣካል ወደ ኢንስቲቱት ቴክኖሎጂ መቐለ ሬጅስትራር በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ።

መመዝገብያ ቀን፡ ከነሓሴ 09-ጳጉሜን 02፣ 2010 ዓ/ም ብቻ!!

የፈተና ቀን፡ ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 03, 2010 ዓ/ም

የመፈተኛ ቦታ፡ በቅርብ ቀን በሬድዮ እና በድህረ ገፅ ይነገራል.

ምንጭ:- ከ MIT ድህረ-ገፅ

©Qene Tata
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቆማ LTV⬆️ዛሬ ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ የዘንድሮውን የአረፋ በዓል ከእንግሊዝ የሙስሊም ኮሚኒቲ አባላትና ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ጋር በኡስታዝ አቡበከር ቤት።

◾️የኢድ አል አድሀ (አረፋ) ባዕል ሀይማኖታዊ ትርጉም የኡስታዝ አቡበከር ሀይማኖታዊ አስተምህሮት እና የቤተሰብ ህይወት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የሚደረግ የባዕሉ ቅድመዝግጅት እና መገለጫዎች አረፋ በመደመር ወቅት(አንድ የመሆን እሳቤ) እና በ ሀገሪቷ አዲስ ምዕራፍ ሲከበር የእንገሊዝ ሀገር ሙስሊም ኮሙኒቲ ባዓል አከባበርና ሌሎችንም እንጫወታዎች።

ከ8፡00 ጀምሮ በኤል ቲቪ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቆማ FanaTv! ዓረፋን በአስመራ ልዩ የበዓል ዝግጅት እየተላለፈ ይገኛል መከታተል ትችላላችሁ።

መልካም በዓል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ⬆️ተጨማሪ ፎቶዎች በመቐለ ከተከበረው 1439ኛው ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል!

©Ab
@tsegabwolde @tikvahethiopia