TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️ከላይ ያሉት ፎቶዎች ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ባህር ዳር በሄዱበት ወቅት በአቶ ተስፋየ መኖሪያ ቤት በመገኘት ቤተሰቡን ሲያፅናኑ የሚያሳይ ነው።

©የበ.ኢ(K)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትግራይ መገናኛ⬇️

የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ #ብርሀኑ_አባዲ በሕወሐት ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔ ከኃላፊነት ተሰናበቱ፤ ብርሀኑ የሚመሩት ተቋም በሚገባው ፍጥነት እየተጓዘ አለመሆኑን የገለጸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ ከኃላፊነት እንዲነሱ የተደረገው በድርጅቱ መሰረታዊ ለውጥ በማስፈለጉ መሆኑን ጠቅሶ፣ ውጤታማ ሆነው በሚሰሩበት ቦታ ሊመደቡ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች(በተለይ ደግሞ የቤተሰባችን አካላት) እንኳን ለአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር እና የመተሳሰብ #ይሁንልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኮንትሮባንድ⬇️

በ2010 በጀት ዓመት በወጪና በገቢ እቃዎች ላይ በተካሄደ ጸረ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን አስታውቋል።

የኢትዮያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም መኮነን ለFBC እንደተናገሩት የወጪውም ሆነ የገቢ ኮንትሮባንዶች በቁጥጥር ስር ባይውሉ መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን የታክስና ቀረጥ ገቢ ከማሳጣትም በላይ በህዝብ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ናቸው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ አልባሳት፣ ምግብና መጠጥ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

ጫት፣ የቀንድ ከብት፣ ጤፍና ምስርም ሌሎች በህገ ውጥ መንገድ ሲወጡ የተያዙ ምርቶች ሲሆኑ፥ የኢንዱስትሪ ጥሬ እቃ ፋቃድን ሽፋን በማድረግ ያልተፈቀዱ እቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ ሲገቡ ተይዘዋል ተብሏል።

በገቢ ኮንትሮባንዶች ላይ ትልቁን ድርሻ የያዙት አልባሳት፣ ምግብና መጠጥ፣ ጦር መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስና መለዋወጫ እቃዎች እንደሆኑም ነው የተጠቆመው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2010 ዓ.ም አሰራሩን በማሻሻል የተለያዩ ባለድርሻ አካላቶችን በማሳተፉ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ያመላከቱት ዳይሬክተሩ የሀገር አቀፍ የጸረ ኮንትሮባንድ ግብረ ሀይል ወደ ታችኛው መዋቅር እንዲወርድ መደረጉን እና በየደረጃው እራሱን የቻለ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አስረድተዋል።

በዚህም በጥቂት ጊዚያት #ሚሌና #ጅግጅጋ ላይ ከ315 ሚሊየን ብር፣ #ሞያሌ#ሀዋሳና #ድሬዳዋ ላይ 300 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ግምት ያለውን ንብረት በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ነው የተናገሩት።

አሁን ላይ በጸረ ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው ለተገኘው ውጤት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ ሚና አንዳለው የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ይህ ተግባር በ2011 ዓ.ም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል።

©FBC
@tsegbwolde @tikvahethiopia
#update አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥማችሁ የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለጋችሁ በስልክ ቁጥሮች፦

• 011-5- 52-63-03
• 0115-5- 52- 40-77
• 011-5- 52- 63-02
• 011-1- 11-01-11 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደምትችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

#አዲስ_አበባ-እንኳን አደረሳችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የራያ ዩኒቨርስቲ በ2011 የትምህርት ዘመን የሚቀበላቸው ተማሪዎች ቁጥር በእጥፍ እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡ ለዚህም ዩኒቨርስቲው ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ 370 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ አዳዲስ የግንባታ ስራዎች እያካሄደ ይገኛል፡፡

©EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የትምህርት_ፍኖተ_ካርታ ሰነድ⬆️

አንድ የቻናላች ወዳጅ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት መምህር #ዳንኤል_መኮንን በትምህርት ፎኖተ ካርታው ላይ ያወጣውን መረጃ ተመልከተው በሚል ልኮልኛል። እኔም መምህሩን በቻናሉ ስም በማመስገን መረጃውን እንደወረደ አቅርቤላችኋለሁ።

የትምህርት ፍኖተ ካርታ በጥቂቱ⬇️

◾️የዩኒቨርስቲ ቆይታ #ሶስት አመት የነበረው ወደ 4 አመት ከፍ ያለ ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች በመጀመሪያ አመት ተማሪ ሲሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ሳይንስ ኮርሶች ማለትም እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሶሎጂ፣ስነ ምግባር የመሳሰሉ ኮርሶችን በመውሰድ ማህበረሰባቸውን እንዲያውቁ ይደረጋል። የመጨረሻ አመት ተማሪ ሲሆኑም ከ4 ወር እስከ 8 ወር ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ አገልግሎት ይሰጣሉ (ኢንተርንሺፕ)።

◾️የመምህራን ጥቅማ ጥቅም በተገቢው መልኩ ይከበራል።

◾️አጠቃላይ ፈተና በ6ኛ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ይሰጣል።

◾️ፍኖተ ካርታው ለ12 አመት ያገለግላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Venture Addis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
The long awaited concert! Happening this Saturday at Kana Studio, @Rophnan presents, MY GENERATION!
Regular tickets 250,
At the Gate 350
Tickets Available soon @VentureAddis
#update የ10ኛ ክፍል ውጤት⬇️

የ12 ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ እና የ10ኛ ክፍል ዉጤት ከነሐሴ 25 እስከ 30 ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል፡፡

የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብን ለመወሰንም የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑን ነው የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ደሳለኝ የገለጹት፡፡

የ10ኛ ክፍል ውጤትም የእርማት ስራው #መጠናቀቁን እና አሁን ላይ ስራውን የማጥራት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው ዶክተእ ዘሪሁን የተናገሩት። እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ የ12 ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ እና የ10ኛ ክፍል ዉጤት ከነሐሴ 25 እስከ 30 ባሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መግቢያ ነጥብ⬇️

የ12 ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ከነሐሴ 25 እስከ 30 ባሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ⬆️1439ኛው የአረፋ በዓል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር⬆️1439ኛ አረፋ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia