TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ክፍት የስራ ማስታወቂያ⬆️የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ባሉት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

©En
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ⬇️

አብዲ ኢሌይን በተመለከተ ለENF ከደረሱት አዳዲስ መረጃዎች መካከል⬇️

◾️አብዲ ኢሌ በአሁን ሰአት አዲስ አበባ ውስጥ በቁም እስር (የቤት ውስጥ እስራት) ላይ ይገኛሉ።

◾️በክልሉ ተፈፀሙ በተባሉ ወንጀሎች መነሻነት በአቃቤ ህግ ክስ እየተዘጋጀ ይገኛል።

◾️አዲስ የክልሉ ፕሬዝደንት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ሰሞኑን አብዲ ኤሌይን ተክተው ተሹመው የነበሩት አህመድ አብዲ መሀመድ ይነሳሉ።

©ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምስራቅ ሀረርጌ⬇️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን መዩ ሙሉቄ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ በፈጸመው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱን ለመስማት ተችሏል። በጥቃቱ ሌሎች 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

የዞኑ የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ምስኪ መሐመድ እንደገለፁት፥ ጥቃቱን የፈጸሙት የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች ናቸው ብለዋል፡፡ በጥቃቱ ስጋት ምክንያትም በርካታ ሰዎች ከአከባቢው መሰደዳቸውንም ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር ሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ከአህፓ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ፣ ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡

©OBN
@tsegabwolde
#update አዳማ ግጭት ተፈጥሮ በነበረበት ቦታ አሁን ላይ መረጋጋት አለ። ግጭቱ በተፈናቃዮች እና በአዳማ ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረ ነው።

ይህ አጋጣሚ ተጠቅመው ግጭቱን የብሄር ግጭት ለማስመሰል በፌስቡክ የሚፃፉ ፅሁፎችን እየተመለከትን እንገኛለን ነገር ግን #ማረጋገጥ የቻልነው በአዳማ የተፈጠረው ግጭት ምንም አይነት የብሄር መልክ የያዘ ግጭት እንዳልነበረ ነው። ከዚህ ባለፈም በፌስቡክ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ ተብሎ የሚወራው #ውሸት ነው ምንም ቤተ ክርስቲያን አልተቃጠለም።

*ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ መረጃዎች እየመጡልኝ ስለሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የነበሩ 11 የፖሊስ አባላት በዋስ #ተለቀዋል

ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

በመሆኑም አቶ ግርማ ካሳ የ15 ሺ ብር ሌሎቹ የፖሊስ አባላት ደግሞ ከዘጠኝ እስከ ስድስት ሺ ብር ዋስ በማቅረብ መለቀቃቸው ተገልጿል።

የፖሊስ አመራሮቹ በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው ነበር፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
4ተኛው አመት የTikvah-Eth የትምህርት ቁሳቁስ የማሰባሰብ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።

ሀዋሳ የምትገኙ ተሳተፉ! ከ1 የመማሪያ መፅሀፍ ጀምሮ ለገሱ!

0926429534(ተስፋማሪያም @Physicaltes)
0935932153(ብስራት @EATTB)
0916424992(ጌትነት @Getzone)
0934727411(ዮርዳኖስ)
#update የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ስር መቀላቀሉ ተሰምቷል። ሁለቱ ተቋማት ዛሬ በሂልተን ሆቴል የስምምነት ፊርማ መፈራረማቸውን ከሸገር ራድዮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትላንት አዳማ በነበረው ግጭት 1 ሰው ህይወቱ ማለፉን እንዲሁም ከ15 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን በስፍራው ከነበረ የቻናላችን ተከታይ ማረጋገጥ ችያለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ቅዱስ ጊዮርጊስ⬆️

ጌታነህ ከበደ ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ መዘዋወሩ ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፉሪ⬆️የሚኖሩ ነዋሪዎች ኢፍትሀዊ ድርጊት እየተደረገብን ይገኛል። የመንግስት አካል በአስቸኳይ ይድርስልን እያሉ ይገኛሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ⬇️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎላላ እና ጣራ ወረዳ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው ከቀኑ 6 ሰአት ከ30 ሲሆን ከደብረ ብርሀን የሚመጣ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን ሲጓዝ ከነበረ ኮድ የህዝብ ማመለሻ አይሱዙ ቅጥቅጥ ጋር በመጋጨታቸው መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ወርቅአገኘሁ ሸዋ ለFBC ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኮማንደሩ አደጋው እንደደረሰም የሁለቱን ተሽከርካሪዎች ሾፌሮች ጨምሮ የ12 ሰዎች ህይዎት ወዲያውኑ ሲያልፍ የ 3 ሰዎች ህይዎት ደግም በደብረ ብርሀን ሪፈራል ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይዎታቸው ሊያልፍ ችሏል።

በ4 ሰዎች ላይ ከባድ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን እና ተጎጂዎቹም ደብረ ብርሀን ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን መክትል ኮማንደር ወርቃገኘሁ ሸዋ ተናግረዋል።

ህይዎታቸው ያለፉት ሰዎችም አብዛኞቹ መታወቂያ ያልያዙ በመሆናቸው አድራሻቸውን ማወቅ አለመቻሉን የተናገሩት ኮማንደሩ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረብርሀን ለመጓዝ የወጡ ቤተሰቦች ያሏቸው ሰዎችም ካሉ መረጃው እንዲደርሳቸው አሳስበዋል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቴፒ⬇️

በቴፒ ከተማ ውጥረቱ ዛሬም ቀጥሏል። በዛሬው ዕለት የሰው ህይወት መጥፈቱም ተረጋግጧል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ግጭቱን ለመቆጣጠር እየሰሩ እንደሚገኙም ተሰምቷል።

የደረሱኝ ተጨማሪ መረጃዎችን አጣርቼ አቀርባለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia