TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያስገነባ መሆኑን ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከለኩ ወጣቶች የመጣ መልዕክት⬇️

በ19/12/2010 በዕለተ ቅዳሜ በሲዳማ ዞን በለኩ ከተማ ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ የደም ልገሳ በማድረግ ልንደርስላቸው ለሚገቡን ለመድረስና ለዘመን መለወጫ በጣም የተቸገሩ እና ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋዊያንን ለመመገብ እየተሯሯጥን እንገኛለንና ሁሉም ይህን ቀና አላማ በመደገፍ ከጎናችን እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ለወገን ደራሹ ወገን ነው!

የለኩ ከተማ ወጣቶች-0919687777
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ተግባር-ከአ.አ ወጣቶች⬆️

"በትላንትናው ዕለት ከነበረው ጫወታ በፊት በሙዳይ በጎ አድራጎት ግቢ ውስጥ በመገኘት የተለያዩ አልባሳት እና የብር ድጋፍ አድርገናል። ኳስን ከመዝናኛ አልፎ ለበጎ ተግባር ብናውለው ጥሩ ነው ሄደው እንዲጎበኙ መልክት አስተላልፍልኝ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዳማ⬇️

"ፀግሽ የአዳማው ግጭት እኛ ሰፈር ነው። የግጭቱ ምክንያት ተፈናቃዮቹ ከመምጣታቸው በፊት የድንጋይ ካባ ነበር በቦታው እና አሁን ድንጋዩ የኛ ነው በማለታቸው ነው ግጭቱ የተፈጠረው። በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ፖሊስ ተበትኗል። አሁን #የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ናቸው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገራችንን ሰዎች የፌስቡክ አጠቃቀም እንዴት አገኛችሁት??
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የውሸት ዜና⬆️ባለፉት ቀናት በፌስቡክ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ (ትግራይ ክልል) ገብተዋል ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ዜና ውሸት መሆኑ ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ አረጋግጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ተግባር-ከአ/አ ወጣቶች⬆️

በኢትዮጵያ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ትላንት በሸበሌ ሆቴል ለወገናቸው ድጋፍ አድርገዋል። ወጣቶቹ ኳስ ከማየት ባለፈ ለወገኖቻቸው የመማሪያ ቀሳቁሶችን አሰባስበዋል። ሁሉም ምስጋና ይገባቸዋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወዳጆቼ ሁሌም ማለት እችላለሁ የራሴን የግል እይታ ወደህዝብ ለማድረስ አልፈልግም። ቤታችን የብዙ ሰው ስለሆነ በገለልተኝነት ማገልገሉን መርጫለሁ። ዛሬ ግን ፍቃዳችሁን ጠይቃላሁ? ሰሞኑ ወደ ፌስቡክ ጎራ ስል የማየው ነገር ሁሉ ልቤን እየሰበረው ነው። ሰው ወዴት እያመራ እንደሆነ ግራ ገብቶኛል። ትንሽ የተሰማኝን ልተንፍስ ??

ፍቃደኞች ናችሁ
አይደለንም

ይህ የሁላችንም ቻናል ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይገርማል ከወር በፊት ስለፍቅር፣ አድነት እና መደመር ሲያወራ የነበረ ሁሉ ዛሬ ተከፋፍሎ በፌስቡክ መሰዳደብ፣ መጠላላት ጀምሮ ሳይ አዘንኩ። ፌስቡክ የጥላቻ መድረክ የስድብ አውድማ ሆኗል። #አንዳንዱ ወጣት ፌስቡክ ላይ ተጥዶ በብሄር፣ በሰፈር፣ በመንደር፣ በክልል ተከፋፍሎ ጥላቻን የሰብካል፤ ይሳደባል። አንዳንዱ የአብይን ጥሪ የቀብሎ ወሳን ሳይገድበው በበጎ ፍቃድ ሀገር ያገለግላል፤ እየዞረ ለዜጋው ደሙን ይሰጣል።
.
.
አንዳንዱ የራሱን ዘረኝነትና ጎጠኝነት ስሜት በፅኑ ሳይዋጋ ደርሶ ስለዘረኝነት ክፋት ይሰብካል፤ ሠዎችን ዘረኛ እኔ ነኝ የኢትዮጵያ ጠበቃ ይላል።
.
.
ጎበዝ....እንሰልጥን እጂ! ብዙዎቹ የፌስቡክ አርበኞች ከሀገር ውጭ ናቸው። እስኪ ስለመከባበር፣ ስለነፃነት፣ ስለህግ ወጣቱን ቢያስተምሩት።

ሁሉም አክቲቪስት፤ ሁሉም ተንታኝ፤ ሁሉም ነፃ አውጪ፤ ሁሉም ጋዜጠኛ ሆኖ አርፎታል።

በኢትዮጵያ #ተስፋ አንቆርጥም!
ተስፋችን #በፈጣሪ እንጂ በሰው አይደለም!
.
.
ዶክተር ዐብይ ከጎንህ ነኝ!
#Tsegabwolde-አስተያየት እቀበላለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈጣሪ እዚህ ስለሰበሰን ደስ ብሎኛል! ሁሌም እዚህ ቤት ስውል ነው ውስጤ በተስፋ የሚሞላው - በመቶዎች የሚቆጠሩ አስተያየቶችን ከሁሉም ክልል አንብባያለሁ አዳምጫለሁ እስካሁን - እውነት ለመናገር #አንድም ሰው አልተሳደበም፣ አላንቋሸሸም፤ አልተራገመም። የዚህ ቤት 100,000 ሰው ነገ ምርጥ ሀገር ተረካቢዎችን ያፈራል።

ወጣቶች እያለቀሱ ስለሀገራቸው አውርተውኛል። ሰው መሆነ የሚቀድምባቸው ብዙ የቤተሰባችን አባላት በእንባ ታጅበው ስለሀገራቸው አውርተዋል።

በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም!
ፈጣሪ ቤታችንን ይጠብቅልን!
TIKVAH-ETHIOPIA(ተስፋ-ኢትዮጵያ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ሁለተኛው የሆሄ የስነ-ጽሑፍ ሽልማት ባማረ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡ በአርቲስት አለማየሁ የመድረክ አጋፋሪነት ዛሬ ነሐሴ 7 ቀን 2010 ዓ.ም በብሔራዊ ቴያትር በተከናወነው የሽልማት ስነ-ስርዓት አሸናፊዎቹ ታውቀዋል⬇️

*በህጻናት መጽሐፍ ዳንኤል ወርቁ(ቴዎድሮስ መጽሐፍ)
*በግጥም መጽሐፍ በእውቀቱ ስዩም(የማለዳ ድባብ)
*በረጅም ልብወለድ ዘርፍ አለማየሁ ገላጋይ (በፍቅር ስም)

©ሚልኪያስ ጌታቸው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለመሰናበቻ ዶክተር አብይ ጠ/ሚ ከመሆኑ በፊት (የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር) እያለ የተናገረውን ወደናተ ላድርስ።

📌ይህ የዶ/ር ንግግር ከዚህ ቀደም በቤታችን ተለጥፎ ነበር(ጠ/ሚ ከመሆኑ በፊት)

"ታሪክ መማሪያ ሲሆን፣ ለነገ ድልድይ የምንሰራበት ሲሆን ጠቃሚ ነው፡፡ ታሪክ ዛሬን የሚያበላሽ ከሆነ ግን አደገኛ ነው፡፡ አሁን ያለው የኢትዮጵያን ፖለቲካም ሲታይ በአብዛኛው መልካም ነገርን የሚደምር አቅም ሳይሆን ያለችውን ትንሽ ስንክሳር፣ ያለችውን ትንሽ ጥፋት የሚያጎላና የበለጠ ችግር ለመፍጠር የሚታትር ሆኖ ይታያል፡፡ ይሄ አደገኛ ነው፡፡ በተለይ ወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ ማስተዋል የሚገባው ነገር ከታሪክ ተምሮ ራሱን ለመለወጥ ራሱን ለማሻሻል የማይጠቀምበት ከሆነ ታሪክ የጥፋት ምንጭ ከሆነ ታሪክ አይደለም፡፡ አሁን ያለው ወጣት ሌላ አገር የለውም፡፡ አሁን ያለው ወጣት ሌላ የሚያስባት አገር ካለች ለመማር፣ ገንዘብ ለማግኘት ይሆናል እንጂ የመጨረሻ ማረፊያው የራሱ አገር ናት፡፡ ይቺን አገር በትክክል አሁን መቀበል፣ መረከብ፣ መስራት በዚያም መገልገልና መልሶም ለሚቀጥለው ማስረከብ ግዴታው መሆኑን ማሰብ አለበት፡፡ ወጣቱ በምክንያት የሚሞግት፣ ነገሮችን በምክንያት የሚያይ… ባልታመነ መረጃ፣ ባልታመነ ዳታ ለፀብ ራሱን የሚያዘጋጅ ሳይሆን እውነተኛ መረጃም ቢመጣ ሁለት ሶስት አመራጮችን አይቶ ለተሻለ ነገር ራሱን ማዘጋጀት አለበት፡፡ ሁልጊዜ ወደኋላ መለስ ብለን የምናየው ነጋችንን ለመስራት መሆን አለበት፡፡ ነጋችንን የሚያበላሽ ኋላ ተገቢ ስላይደለ፣ መሆንም ስለሌለበት ወጣቶች ከማንም በላይ ይሄ አገር የእነሱ ነው፤ መጠበቅ ያለባቸው፣ መንከባከብ ያለባቸው እነሱ ናቸው፤ ያላቸውን ጉልበት በመደመር ለልማት፣ ለሰላም፣ #በጣም_ውብ ለሆነች #አገር ቢገለገሉባት ጠቃሚ ነው የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡"

◾️ዶክተር አብይ አህመድ (የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ሰኔ 16 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ላስመዘገቧቸው ለውጦች በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በሚል ምርምራ እየተካሄደባቸው የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ #ዋስትና ተፈቀደላቸው።

አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።

የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል።

ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ገብረስላሴ ታፈረ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄና ኮማንደር አንተነህ ዘላለምን ጨምሮ ሌሎች የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው የነበሩ ግለሰቦች ከ6 ሺህ ብር እስከ 9 ሺህ ብር በሚደርስ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል።

በዚህም የዋስትና ጉዳይን የሚመለከተው መዝገብ መዘጋቱን ነው ፍርድ ቤቱ ያስታወቀው።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia