TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ወላይታ ዞን⬆️

የወላይታ ዞን ምክር ቤት ለ2011 በጀት ዓመት 2 ቢሊዮን 950 ሚሊዮን 351 ሺህ 518 ብር በጀት አጸድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

የምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ ጉባኤ የተጀመረው በሀዋሳና አከባቢው በተፈጠረው ግጭት ህይወታቸው ላለፉ ዜጎች የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው፡፡

የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ተድላ ናደው እንዳሉት ጉባኤው በሀገራችንና በክልላችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በተደረገበት ማግሥት መከናወኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡

የተጀመረው የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የሰላም ግንባታና የለውጥ ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የድርሻውን በላቀ ተነሳሽነት ማበርከት አለበት ብለዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች ከአንድ ወር በፊት በተቀሰቀሱ ግጭቶች ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለዘለቄታው ለማቋቋም ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ላደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ #ዶክተር_ጌታሁን_ጋረደውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል፡፡

እንደዚሁም፦

1. አቶ ደገቱ ኩምቤ፡- የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ አክሊሉ መኮንን፡- የፀጥታና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ

3. አቶ ዓለማየሁ ጎልዳ፡- የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ

4. አቶ ሚካኤል ሳኦል፡- የትምህርት መምሪያ ኃላፊ

5. አቶ ዘካሪያስ ፋልታሞ፡- የቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ እንዲሆኑ የቀረበውን ሹመት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌታሁን ጋረደው - በመንግሥት የተበሰረው የይቅርታ፣ የፍቅር፣ የመደመርና የአንድነት ዕሳቤዎች ለሁለንተናዊና ዘላቂ ተጠቃሚነት ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የወጣቶችና የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ህገ ወጥ የህጻናት ዝውውርና የጉልበት ብዝበዛ ለማስቀረት የተቀናጀና ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ አመላክተዋል፡፡

©የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር አብይ አህመድ⬆️

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አደል ቢን አህመድ አል ጁበይር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

#ዶክተሩ_ስራ_ላይ_ናቸው
ፎቶ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬇️

በሃዋሳ ከተማ ባለፉት ጊዚያት በተለያዩ ግጭቶች ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች ተጠልለው የቆዩ ተፈናቃዮች ካሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ መኖሪያ ቀያቸው አየተመለሱ መሆኑ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

📌ተፋናቃዮችን ወደ ቀያቸው ከመመለስ ጎን ለጎን የእርቅ ስራ አየተሰራ ሲሆን፥ #ሰፋ ያለ #የእርቅ ፕሮግራም #በቅርቡ የሚካሄድ መሆኑንም ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓረና⬇️

በትግራይ ክልል የዓረና ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ በአሁኑ “በለውጥ ግዜ” እየተባለም በአባላቶቼ ላይም ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ሲል ገልጿል።

የፓርቲው የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ተኽለዝጊ ወልደገብርኤ በተለይ በቆላ ተምቤን ወረዳ የሚገኙ የፓርቲው አመራርና አባላት እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ችግር እየደረሰባቸው ነው ብለዋል፡፡

የወረዳው የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክብሮም ወልዱ በወረዳው፤ ሰው በፖለቲካዊ አመለካከቱ ጥቃት አይደርስበትም እንደውም ተቃዋሚ
ፓርቲዎች በሚያሰናዱት መድረኮች በወረዳው የፀጥታ አካላት የሚገባ ጥበቃ ይደረግላቸዋል ብለዋል።

©VoA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር የሁላችንም ቤት ናት በጋራ #እንጠብቃት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለማስታወስ ኢትዮጵያ ጀግናውን ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ካጣች ሁለት ሳምንት ሆኗታል። እስከ ዛሬ ድረስ ፖሊስ ስለደረሰበት የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ አላደረገም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
4ኛው አመት የTIKVAH-ETH የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።

ሀዋሳ እና አካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን!

◾️ከ1ኛ ክፍል - 12ኛ ክፍል ያሉ ማንኛውም አይነት የትምህርት መፅሀፍት መለገስ ትችላላችሁ።

.በየትኛውም ቋንቋ የተዘጋጁ መፅሀፍት መሆን ይችላሉ

◾️የተለያዩ የትምህርት ቁሶችን (እስክርቢቶ፣ እርሳስ፣ ደብተር...) መለገስ ትችላላችሁ።

ይህን የሀገር ግንባታ ስራ የሚያስተባብሩት ወጣቶች በየትኛውም ቦታ መጥተው ሊቀበሏቹ ይችላሉ⬇️

*0926429534(ተስፋማሪያም @Physicaltes)
*0935932153(ብስራት @EATTB)
*0916424992(ጌትነት @Getzone)
*0934727411(ዮርዳኖስ)

📌ባለፉት 3 ዓመታት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ላደረጋችሁት መልካም እና ትልቅ ስራ ምስጋና ይድረሳችሁ።

#እስከ ነሀሴ 25
TIKVAH-ETH ከአለን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬇️

"ሰላም ፀግሽ! በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲሱ ገበያ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የምንገኝ ሲሆን አኛ የምንሰራው ደረቅ ቆሻሻ ነው እናም ከዚ በፊት ይከፈለን ከነበረው ደመወዛችን ቢያንስ ከግማሽ ባነሰ እየተከፈለን ነው ያለው፡፡ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ባናውቅም እኛ ግን ስራችንን በተሻሻለ አሰራር በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ ስለሆነም ይሄ መልዕክት አስቸኳይ መፍትሄ ስለሚያስፈልገው ለሚመለከተው አካል ደርሶ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠን ስንል እንጠይቃለን፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬆️

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል።

ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳን ጨምሮ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተገኙ ልዑካንም ይሳተፋሉ።

◾️ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ አስር
ግለሰቦች ከጎንደር እንዲሚገኙ ታውቋል።

©AMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Venture Addis
LinkUp Online Events Listing Magazine, August Issue is Finally here!! High quality design and content. With an exclusive interview with the one and only Betty G. @VentureAddis
Forwarded from Venture Addis
LinkUp Addis August 2018 Edition.pdf
4.6 MB
Linkup Online Events Listing Magazine, August Issue!!!
@LinkupAddis @LinkupAddis