Tikvah-University
323K subscribers
11.7K photos
17 videos
73 files
1.11K links
Download Telegram
#CentralEthiopiaRegion
#8thGradeResult

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ በ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ መደበኛ ተማሪዎች ውስጥ 60.3% የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸው ተገልጿል።

በክልሉ 93,797 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 56,546 ተማሪዎች 50 በመቶና ከዚያ በላይ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ተናግረዋል።

የተመዘገበው ውጤት በ2016 ዓ.ም ከተመዘገበው ውጤት የ37 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ኃላፊው ገልፀዋል።
267 ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎችን ማሳለፍ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

በዓመቱ የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ በመደበኛ ለሁሉም 50% እና በላይ፤ ለአካል ጉዳተኞች 45% እና በላይ መሆኑ ተገለጿል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመውን ሊንክ በመጠቀም የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ።

ውጤት ለማየት 👇 https://ce.ministry.et/

@tikvahuniversity
79😢11🙏6👎5👏4👍2😱2🥰1
Tikvah-University
Photo
በስኬቶች የደመቀችው ተመራቂ 🎓👏

ዶ/ር ቤተልሔም እውነቱ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምህርት ቤት በማዕረግ በዛሬው ዕለት ተመርቃለች። በርካታ አስገራሚ ስኬቶችንም ተጎናፅፋለች።

🏅የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ - CGPA: 3.95
🏆 የፕ/ር ዕደማሪያም ፀጋ አካዳሚክ ልህቀት በሕክምና ተሸላሚ
👩‍🎓 ከ2017 ሴት ተመራቂዎች ሰቃይ
🥇 ምርጥ ኢንተር – ከቀዶጥገና ት/ት ክፍል
🥇 ምርጥ ኢንተር – ከህጻናት ህክምና ትምህርት ክፍል

@tikvahuniversity
👍740👏326282🥰33👎8😱4🙏1
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ!

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይሰጣል፡፡

ሁለት አይነት የ'IELTS' ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) የሚሰጡ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ተጀምሯል።

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts

በአካል ለመመዝገብ 👇
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንጻ ቁ. 130 ቢሮ ቁ. 404

ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ
[email protected] / 0925629589

@tikvahuniversity
80👍11👎11😱1🙏1
በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን ሙሉ የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት የምንሰጠውን ስልጠና ይውሰዱ!

ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ!

🔔 አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Webapp Development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: https://t.iss.one/topinstitutes
TikTok: https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
19👎9
በአማራ ክልል የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች በተቀመጡት ሁለት አማራጮች ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ፦

https://amhara.ministry.et/#/result አድራሻ ላይ በመግባትና የመለያ ቁጥር በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

@emacs_ministry_result_qmt_bot የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

👉 @emacs_ministry_result_qmt_bot
👉 Start የሚለውን ይጫኑ፣
👉 ክፍልዎን ይምረጡ፣
👉 ከዚያ ክልልዎን ይምረጡ
👉 የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስም በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታ ለማቅረብ https://amhara.ministry.et/#/complaint በሚለው አድራሻ ላይ በመግባትና በሚመጣው ቅጽ ላይ የመለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስም በማስገባት Fetch Course የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ። በመጨረሻም Add Complaint የሚለውን በመጫን ቅሬታችሁን ማቅረብ ይችላሉ።

በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
70👍8😢7👏6🙏6😱1
#AdmasUniversity

አድማስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ6,000 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በርቀት የትምህርት መርሐግብር በዲግሪ፣ በዲፕሎማ እና በሰርተፊኬት ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ላለፋት 26 ዓመታት በመደበኛ እና በርቀት የትምህርት መርሐግብር በርካታ ተማሪዎችን አስመርቆ ለሀገሩ የሰው ኃይል ልማት የበኩሉን አበርክቶ እያደረገ እንደሚገኝ የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሞላ ፀጋይ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

10 ካምፓሶች እና የበርካታ የርቀት ትምህርት መስጫ ማዕከላት ባለቤት የሆነው አድማስ ዩኒቨርሲቲ፤ ከኢትዮጵያ ውጪ በሶማሊላንድ እና በፑንትላንድ ትምህርት እየሠጠ ይገኛል።

@tikvahuniversity
137🙏10👍6🥰5😢3👏2
የሁለት ወር የቴክኒካል ስራዎች (Technical Skills) የክረምት ስልጠና ይሰልጥኑ።

የሚሰጡ ስልጠናዎች፦
👉 Building Electrical Installation, CCTV Camera Installation and Security Solutions
👉 Computer Maintenance, Networking, Office Machine Maintenance and Home Appliance
👉 Mobile Maintenance 
👉 Industrial Machine Installation and Maintenance

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://t.iss.one/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
29
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!

@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድ እና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን እኛ ጋር ያገኛሉ።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለብዎትን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን።

🔔 በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እና ለሌሎችም! ሁሉም አሉን!

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram: https://t.iss.one/samcomptech
17
#ጥቆማ

በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ የBSc ስልጠናዎን በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ይከታተሉ።

ስልጠናው የዘመናዊ አውሮፕላን መላፍለጋ (Troubleshoot)፣ ጥገና እና የደኅንነት ደረጃዎችን መጠበቅ ብቁ ባለሙያ ያደርግዎታል።

ለማመልከት 👉 https://eau.edu.et

ለተጨማሪ መረጃ 👇

Email: [email protected] | [email protected]
Phone: +251115174600 / 8598

@tikvahuniversity
15😢1🙏1
Tikvah-University
Photo
#MoH

የብቃት ምዘና ፈተና የሚወስዱ የጤና ባለሙያዎች የኦንላይን ምዝገባ ሐሙስ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ይመዝገቡ👇
https://hple.moh.gov.et/hple

ተመዛኞች የብቃት ምዘና ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉበትን የፈተና ጣቢያ ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ መምረጥ ይኖርባችኋል፡፡

ተመዛኞች ምዝገባችሁን ካጠናቀቃችሁ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር ፕሪንት አድርጋችሁ መያዝ እንዳትረሱ፡፡

@tikvahuniversity
49🙏3
#SSHSBC

ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና እና የቢዝነስ መስኮች ያስተማራቸውን 1,147 ተማሪዎች አስመርቋል።

ኮሌጁ በመጀመሪያ ዲግሪ 992 እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ 115 በድምሩ 1,147 ተማሪዎችን በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል አስመርቋል፡፡

@tikvahuniversity
26
#SidamaEducationBureau

የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ2,800 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በክልሉ ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አካሒዷል።

ለስድስት ሳምንታት በሚቆየው ልዩ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት፣ ከ2,800 በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይሳተፋሉ፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ የመጀመሪያ ቀን ትምህርት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

@tikvahuniversity
91👍8